Home Blog Page 436

ፊፋ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን አገደ

0

ፊፋ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን አገደ

 

ፊፋ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን አገደ

ፊፋ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ሊካሄድ የነበረውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ምርጫ ፌዴሬሽኑ አስፈላጊ መረጃዎችን አላከልኝም በማለት አገደው፡፡

በፊፋ የአሠራር ደንብ መሠረት የዚህ ዓይነቱ ምርጫ ከመካሄዱ ከአንድ ወር በፊት የአስመራጭ ቦርድ አባላትን የሚመለከቱ መረጃዎች ለፊፋ መላክ ነበረባቸው፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይህንን ሳያደርግ ስለቀረ ነው ፊፋ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ያገደው፡፡

ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር አቶ ተካ አስፋው ከአማራ ክልል፣ አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) ከደቡብ ክልል፣ አቶ አንተነህ ፈለቀ ከኦሮሚያ ክልልና አቶ ዳግም ምላሸት ሀኞክ ከጋምቤላ ክልል በእጩነት ቀርበው ነበር፡፡

ከአሁን በፊት የሩዋንዳ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አስፈላጊውን መረጃ ለፊፋ ባለማሳወቁ የተነሳ በፊፋ ታግዶ ለአራት ወራት መራዘሙ ይታወሳል፡፡

ለበለጠ መረጃ ይህን ይጫኑ

በቀይ ሽብር በበርካታ ወጣቶች ግድያ የተጠረጠሩት አቶ እሸቱ ዓለሙና በዘ ሄግ ያስቻለው ፍርድ ቤት

0

በቀይ ሽብር በበርካታ ወጣቶች ግድያ የተጠረጠሩት አቶ እሸቱ ዓለሙና በዘ ሄግ ያስቻለው ፍርድ ቤት

በቀይ ሽብር ዘመቻ ወቅት በበርካታ ሰዎች ግድያ “እጃቸው አለበት” በሚል የተጠረጠሩት የኔዘርላንድ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያዊ ጉዳይ በዘ ሄግ እየታየ ነው።

ባለፈው ሰኞ ባስቻለው ችሎት ጉዳያቸው መታየት የጀመረው የስልሳ ሶት ዓመቱ የቀድሞ የደርግ አባል አቶ እሸቱ ዓለሙ “ፈጽመዋል” በተባለው ወንጀል በጊዜው ታስረው ከሞት የተረፉና እንዲሁም የቤተሰብ አባሎቻቸው የተገደሉባቸው በዩናይትድ ስቴትስ እና በሌሎች አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑ ሰባት ኢትዮጵያውያን ዛሬ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1970ዎቹ በጎጃም ክፍለ ሃገር በደብረ ማርቆስ ከተማ “ተፈጽሟል” በተባለውና 75 ወጣቶች የተገደሉበት ወንጀል ነው ተጠርጥረው ከፍርድ ቤቱ የቀረቡት።

የያዛችሁት “የተሳሳተ ሰው ነው” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ የመለሱት ተጠርጣሪ አቶ እሸቱ ዓለሙ “የእኔ ድርሻ የፕሮፖጋንዳ ሥራ ብቻ ነበር” ቢሉም፤ “የዚያ ክፉ ጊዜ ዘግናኝ በደል ሰለባዎች ነን” ያሉት ወገኖች ግን የምሥክርነት ቃላቸውን ለመስጠት የኔዘርላንድ መንግስት መቀመጫና የበርካታ የዓለም አቀፍ ችሎቶች መናሃሪያ ወደ ሆነችው ዘ ሄግ ከተማ አቅንተዋል።

አቶ አብረሃም ብዙነህ ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ የምትገኘው የቨርጂኒያዋ የፎልስ ቸርች ከተማ ነዋሪ ናቸው። በተጠርጣሪው አቶ እሸቱ ትዕዛዝ ከተገደሉት ወጣቶች አንዱ ታላቅ ወንድማቸው መሆናቸውን ይናገራሉ።

ራስን የማጥፋት ሃሳብ ያለው ሰው በህክምና ተለይቶ ማወቅ ይቻላል- ጥናት

0

 

የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው፥ በየዓመቱ 800 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በዓለም ዙሪያ ራሳቸውን ያጠፋሉ።

በ34 ሰዎች ላይ ተደርጎ ይፋ የሆነ ጥናት እንደሚጠቁመው ሰዎች አእምሯቸውን ኤም አር አይ በመሰለ የህክምና መሳሪያ በማንበብ ራስን ስለ ማጥፋት እያሰቡ መሆኑን ማወቅ ይቻላል።

“የዚህ አዲስ ጥናት ትኩረቱ፥ አንድ ሰው ከሞት ጋር የተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮችን በሚያስብበት ጊዜ እራሱን ለመግደል እያወራ መሆኑን የሚያሳይ ነው” በማለት የጥናት ቡድኑ መሪ ማርሴል ጀስት ተናግረዋል።

ይህን ጥናት ለማረጋገጥ ተመራማሪዎቹ 34 ተሳታፊዎችን የተመለከቱ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 17 የሚሆኑት ራሳቸውን የመግደል ሐሳብ እንደነበራቸው ተረጋግጧል።

በዚህ የጥናት ምርምር እያንዳንዱ ሰው ከተለያዩ ስሜቶች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተከታታይ ቃላትን እያሳየ ሳለ የአንጎሉ ምስል፥ መግነጢሳዊ ምስልን በሚይዝ መሳርያ አማካኝነት ታይተዋል።

በዚህም መሰረት ለሙከራ ምርምር ከቀረቡት ሰዎች በአእሙሮአቸው ከሚያስቡት አሥር ቃላት አዎንታዊ ስሜታዊ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆኑ፥ አሥር ቃላት ደግሞ አሉታዊ እንደነበሩ እንዲሁም አሥር አስከፊ እና በተስፋ ማጣት ስሜት ራስን የማጥፋት ድርጊቶች የሚያስከትሉ መኖራቸው በጥናቱ ተጠቁሟል።

በዚህም ተመራማሪዎቹ ራስን ለመግደል እያሰቡ ባሉ ተሳታፊዎች ላይ አምስት የአንጎል ክልሎችን እና ስድስት ራሳቸውን እንደሚገድሉ የሚያመለክቱ ቃላት መለየታቸው ተነግሯል።

ቀጥሎም ተመሳሳይ ነገር ለመለየት የሚያስችል አንድ ስልተቀመር በመጠቀም፥ ከ17 ታካሚዎች 15ቱ የራሳቸውን ሕይወት ሊያጠፋ የሚያስችል ሀሳብ እንዳላቸው ተለይቷል።

ይህን መሰረት በማድረግ ስልተ ቀመሩ የራሳቸውን ሕይወት ለማጥፋት ሙከራ ካደረጉ ተሳታፊዎች መካከል 94 በመቶ መገኘታቸው ማሳየቱን ነው የተገልፀው።

የጥናት ቡድኑ ተባባሪው ዴቪድ ብሬንት እንዳሉት፥ ይህ ዘዴ በግለሰቦች ውስጥ ያለ የመግደል ዝንባሌን የመተንበይ ችሎታን ለመወሰን የሚያስችል ነው።

ስለዚህ ለወደፊቱ ሐኪሞች እንዲህ አይነት ችግር ያለባቸው ሰዎች ለመለየት፣ ለመከታተል እና ምናልባትም እራሳቸውን የመግደል ፍላጎት ባላቸው ግለሰቦች ላይ የተዛባ አስተሳሰብን ለመለየትና ለማዳን ሊረዳ ይችላል ብለዋል።

ምንጭ፦ ፎክስ ኒውስ

የትምህርት ሚኒስቴር የኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች የ1ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ ላይ ለውጥ አደረገ

0

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2010 የትምህርት ዘመን የ1ኛ ዓመት ተማሪ በመሆን ከኦሮሚያ እና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች በኢትዮጵያ ሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የአዲስ ተማሪዎች ምደባ ለውጥ ተደረገ።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የምደባ ለውጡን በዛሬው እለት ለተማሪዎች ይፋ ማድረጉን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በሁለቱ ክልሎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የነበሩ አዲስ ተማሪዎች ምደባውን በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ድረ ገጽ www.app.neaea.gov.et ላይ መመልከት እንደሚችሉም አስታውቋል።

የ1ኛ ዓመት አዲስ ተማሪዎች ለውጥ በተደረገበት ምደባ መሰረት ወደ ተመደቡበት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመሄድ ትምህርታችውን እንዲከታተሉም ነው ያሳሰበው።

ለአማርኛ ቋንቋ ተቆርቋሪዋ ኒዤሪያዊት የፊልም ባለሞያ

0

ለአማርኛ ቋንቋ ተቆርቋሪዋ ኒዤሪያዊት የፊልም ባለሞያ

ፊልሟ ውስጥ አማርኛ ጽሑፍ በማስገባት ለአማርኛ ቋንቋ መቆርቋሯን አሳይታለች ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያ ራማቱ ኪየታ፤ አማርኛ የአፍሪቃ ኅብረት ይፋዊ ቋንቋ እስኪሆን ጥረቴን አላቋርጥም ትላለች። ኒዤሪያዊቷ የፊልም ዳይሬክተር በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ በመሳተፍ ለአማርኛ ቋንቋ መሟገቷን ቀጥላለች።

የምዕራብ አፍሪቃዊቷ የፊልም ባለሞያ ራማቱ ኪየታ አማርኛ ቋንቋ ከአፍሪቃ ኅብረት ይፋዊ የሥራ ቋንቋዎች መካከል አንዱ እንዲሆን ጥረት ማድረግ ከጀመረች ሰነባብታለች። ጥረቷን ለማሳካትም የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንሥትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ በአፍሪቃ ኅብረት የተለያዩ ባለሥልጣናትን አነጋግራለች። አሁን ደግሞ  «የጋብቻ ቀለበቱ» የተሰኘው ረዥም የፍቅር ፊልሟን ርእስ እና የፊልም ባለሞያዎች ዝርዝር ከፊልሟ መጀመሪያ እና መጨረሻ ላይ በአማርኛ ቋንቋ እንዲጻፍ አድርጋለች። «ይህ ጅማሮ ለጥረቴ መሳካት በግል የማደርገው አንዱ አካል ነው» ያለችው ኒዤሪያዊቷ የፊልም ዳይሬክተር በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ በመሳተፍ ለአማርኛ ቋንቋ መሟገቷን ቀጥላለች።

ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ራማቱ ኪየታ የኒዤር ተወላጅ ጸሐፊና የፊልም ዳይሬክተር ናት።  በእንግሊዝኛ „The wedding ring“  የሚል ስያሜ የሰጠችው ፊልሟን በምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት በሚነገረው የሐውሳ ቋንቋ «ዝናሪያ» ብላዋለች። ይህን ፊልም ታዲያ ራማቱ ሲኒማ ቤቶች ውስጥ ስታሳይ ርእሱን ወደ አማርኛ «የጋብቻ ቀለበቱ» በሚል ቀይራዋለች።

በፍቅር ታሪክ ላይ ያጠነጠነው የራማቱ ፊልም አንዲት አውሮጳ ውስጥ ዲግሪዋን ያገኘች የፉላኒ ወጣት አፍሪቃ ውስጥ በሳህል የገዢ መደብ ሥር ወደሚገኘው የዚንደር ሱልጣን ትመለሳለች። እዚያም በባሕላዊ መንገድ ለባል ልትሰጥ ስትል በሚኖረው ውጣ ውረድ ላይ ይሽከረከራል ፊልሙ።  በዋናነት ግን መሽኮርመም የዳሰሰው ፍቅር በአፍሪቃ ምን እንደሚመስል ለማሳየት ጥረት ያደርጋል።

ይህ የራማቱ ኪዬታ ፊልም አምስተርዳም ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል (World Cinema Amsterdam) ላይ አምስተርዳም ከተማ ውስጥ ከመታየቱ በፊት እዛው ሆላንድ ሮተርዳም የተሰኘው ሌላ ከተማ ውስጥም ለእይታ በቅቶ ነበር።

ፊልምሽን እዚህ ሆላንድ ከተማ ሪያልቶ ሲኒማ ቤት ውስጥ ለእይታ ከቀረቡ ሌሎች ፊልሞች ለየት የሚያደርገው አንድ ነገር ተመልክቻለሁ፤ ያ ምን እንደሆነ ለአድማጮቻችን ብትገልጪላቸው ስል ጠየቅኳት ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያን።

Niederlande Amsterdam - Rahmatou Keita The wedding Ring in World Cinema Amsterdam 2017 (DW/M. Sileshi )ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያ በስተቀኝ በኩል ሻሽ ያሰረችው

«ፊልሙ የፍቅር ታሪክ ነው። ምናልባት አንተ ኢትዮጵያዊ ስለሆንክ የምታወራው የፊልሙ ባለሞያዎች ዝርዝር በአማርኛ መጻፉን ነው። ፊልሙ ሲጀምር እና ሲጠናቀቅ የፊልም ባለሞያዎቹ ዝርዝር ሙሉ ለሙሉ በአማርኛ ቀርቧል።»

የራማቱ የፍቅር ፊልም ከመጀመሩ በፊት ለፊልሙ ድጋፍ ያደረጉ ተቋማት ዝርዝር በአማርኛ እና በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ቀርቧል። ራማቱ የአማርኛ ጽሑፉን በደማቅ ብርቱኳንማ ቀለም ጽፋ ከፈረንሳዪኛው በላይ ነው ያሰፈረችው።

ለፊልሙ ድጋፍ ካደረጉ ተቋማትና ሃገራት መካከልም በቅድሚያ «የኒጀር ሪፐብሊክ» የሚለው ከመሀከል ብቅ ይላል። ከዚያም በተከታታይ «የኮንጎ ብራዛቪል ሪፐብሊክ»፤ «የአልጀሪያ ሕዝባዊ  ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ»፤  «የሩዋንዳ ሪፐብሊክ»፤ «የዩጋንዳ ሪፐብሊክ»፤ «የሞሮኮ ንጉሣዊ መንግሥት» እንዲሁም «የፓን አፍሪቃ ባህል ፌስቲቫል አልጀርስ -2009» የሚሉ ጽሑፎች በአማርኛ ይነበባሉ።

«መታሰቢያነቱ ሞያውን ለአወረሰኝ ለእናቴ ወንድም አጎቴ ሳማሪ ኤል-ሀዲ ሐሪንታ ጂቤ ዲያሎ (=1934 -2015)» የሚል የአማርኛ ጽሑፍ ከተነበበ በኋላ ደግሞ ጥንታዊ ህንጻ ውስጥ የተሰባሰቡ ወንዶች ይታያሉ።

ሙዚቃ እና የአካባቢው ድባባዊ ድምጽ ይሰማል። ግቢ ውስጥ መሬት ላይ ተቀምጠው በአንድ ትሪ ላይ በጋራ የሚመገቡ ሴቶች ይታያሉ። ግንባሯ ላይ የተነቀሰችው ቆንጅዬዋ የፊልሙ ዋና ገጸ ባሕሪ ቲያ ግን ተክዛ አቀርቅራለች።

ቲያ በሚቀጥለው ትእይንት ጓደኛዋ ጠጠር ቆጣሪ ዘንድ ይዛት ስትሄድ እሷ እውጭ አቧራማ ሜዳው ላይ ተቀምጠው ገበጣ የሚጫወቱት ልጆች ጋር ታመራለች። ጠጠር ቆጣሪው ጋር የገባችው ጓደኛዋ ተመልሳ በመውጣት ቲያ አብራት እንድትገባ ትጠይቃለች። ቲያ ግን «የእሱ ርዳታ የሚያሻው ለአንቺ እንጂ ለእኔ አይደለም። ደሞ አንቺን እንጂ እኔን ሊረዳ አይችልም» ትላታለች።

ጓደኛዋ በሩን በኃይል ዘግታ ወደ ውስጥ ስትመለስ «የጋብቻ ቀለበቱ» የሚለው የፊልሙ ርእስ በአማርኛ ይነበባል። ከዚያም ዝናሪያ የሚለው የሐውሳ ርእስ እና የእንግሊዝኛው„The wedding ring“  ይከተለዋል።  አሁንም በደማቅ ቡኒ ቀለም የተጻፈው የአማርኛ ጽሑፍ ነው ቀድሞ የሚነበበው።

Niederlande Amsterdam - Rahmatou Keita The wedding Ring in World Cinema Amsterdam 2017 (DW/M. Sileshi )

ራማቱ ባህላዊ አልባሳትና ቁሳቁሶች ፊልሙ ውስጥ ጎልተው እንዲወጡ ለማድረግ ሞክራለች። ቲያ የምትለብሰው በእደ ጥበብ ባለሞያ በእጅ ስፌት የተሠራው ባህላዊ የሙሽራ ቀሚስን ለማጠናቀቅ ብቻ አንድ ዓመት ያህል ጊዜ መውሰዱንም ገልጣለች።  ከባህላዊ አልባሳቱና ቁሳቁሱ በተጨማሪ ራማቱ ፊልሟ ውስጥ የተለያዩ የአፍሪቃ ቋንቋዎችንም አካታለች።
በአፍሪቃ በእርግጥም «እጅግ በርካታ ቋንቋዎች አሉ» የምትለው ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያ በሐውሳ ቋንቋ «ዝናሪያ» የሚል ርእስ የሰጠችው ፊልሟ ሦስት የአፍሪቃ ቋንቋዎች ይነገሩበታል፤ ሐውሳ፣ ሶንጎይ እንዲሁም ፉላኒ። ራማቱ የፊልም ባለሞያዎች ዝርዝርን በአማርኛ መጻፉን የመረጠችው አማርኛ ቋንቋ በአፍሪቃ«ልዩ ስለሆነ እና እንክብካቤ ስለሚያስፈልገው ነው» ትላለች።

«የፊልም ባለሞያዎች ዝርዝርን በአማርኛ ለመጻፍ የመረጥኩበት ምክንያት፤ አማርኛ እጅግ ጥንታዊ ከሆኑ የዓለማችን የጽሑፍ ቋንቋዎች አንዱ በመሆኑ ነው። በዓለም እንዲህ አይነት ቋንቋዎች ጥቂት ናቸው። ይህ ውብ ፊደላት ያሉት ቋንቋ በኢትዮጵያ እና በጥቂት ሰዎች በኤርትራ ይነገራል። ከመቶ ሚሊዮን አይበልጥም ተናጋሪው፤ ያ ምንም ማለት ነው። ወደ ዐሥር ቢሊዮን እየተጓዘ በሚገኘው የዓለም ቋንቋ ያን ማድረግ እጅግ በጣም ወሳኝ ነው።»

በዓለም ዙሪያ የሚነገሩ እና በመጥፋት ላይ ያሉ ቋንቋዎች መረጃን ያሰባሰበው «ስነ-ሰብ የዓለም ቋንቋዎች» (Ethnologue: Languages of the World) የተሰኘው ድረ-ገጽ ሰባት ሺህ ግድም ቋንቋዎች በዓለማችን እንደሚገኙ ይጠቅሳል።
7.6 ቢሊዮን ግድም ነዋሪዎች ባሏት ዓለማችን የቻይና ማንዳሪን ቋንቋ በ898 ሚሊዮን ተናጋሪዎች በቀዳሚነት ይገኛል። ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያ ራማቱ ኪዬታ 1.2 ቢሊዮን ተናጋሪዎች ባሏት አፍሪቃ አማርኛ ቋንቋ ተገቢውን ሥፍራ አላገኘም ባይ ናት።

«ትግሌ ውብ ባሕላችን ተጠብቆ ለትውልድ እንዲሸጋገር ማድረግ ነው፤ ባሕላችንን ካልተንከባከብን እየደበዘዘ ለመክሰም ጊዜ አይፈጅበትም» ያለችው ራማቱ፦ በተጓዘችበት ሥፍራ ሁሉ አማርኛ ከአፍሪቃ ኅብረት ይፋዊ መግባቢያዎች አንዱ እንዲሆን መወትወቷን አታቋርጥም።

«አፍሪቃ ውስጥ በኛ በፓን አፍሪቃ ፊልም ሠሪዎች ፌዴሬሽን አባልትም ኾነ በአፍሪቃ ኅብረት መካከል ስብሰባ በሚኖርበት እና ጉዞ በማደርግበት ጊዜ አማርኛን ይፋዊ የመግባቢያ ቋንቋቸው አድርገው እንዲጨምሩ እንደወተወትኩ ነው። ብዙውን ጊዜ ታዲያ ይስቁብኛል።»

ራማቱ ሰዎች ሳቁብኝ ብላ ግን ጥረቷን በእንጭጩ አልቀጨችም። ከታዋቂ ሰዎች እስከ ሀገር መሪዎች ድረስ ባገኘችው አጋጣሚ ውትወታዋን አልተወችም። በአንድ አጋጣሚ እንደውም የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንሥትር መለስ ዜናዊን አዲስ አበባ ውስጥ በዚሁ ጉዳይ አነጋግራ እንደነበር ገልጣለች።

«ራህማቱ ሙሉ በሙሉ ትክክል ነሽ አሉኝ። ግን ሠነዱ  ጽሑፍ ውስጥ የለም አሉኝ።  እናም እኔ ክቡር ጠቅላይ ሚንሥትር ፅሑፉን እኛ ነን የምናበጀው አልኳቸው።»

Niederlande Amsterdam - Rahmatou Keita The wedding Ring in World Cinema Amsterdam 2017 (DW/M. Sileshi )የፊልም አፍቃሪዋ ፊዮና ፎሪክ በአምስተርዳም ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫል

ራህማቱ የጀመረችውን ጥረት ከዳሩ ለማድረስ «ቋልፉ በእጃችን ነው» ትላለች። እናም «እኛው ጀምረን ካላሳየን ሌላው ሊከተለን አይችልም» በማለት እንደ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ እና አቶ ሰለሞን በቀለ ከመሳሰሉ አንጋፋ እና ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የፊልም ሠሪዎች ጋር በመነጋገር ፊልሟ ውስጥ የአማርኛ ቋንቋን ለመንደርደሪያ ያህል በጽሑፍ አስገብታለች። ወደፊት ተባባሪ ካገኘች ሙሉ ፊልሟን በአማርኛ ቋንቋ አስተርጉማ ኢትዮጵያ ውስጥም የማሳየት ዕቅድ ነድፋለች።
«ይህን ፊልም ሙሉ በሙሉ በአማርኛ አስተርጉሜ ኢትዮጵያ ውስጥ ማሳየት እፈልጋለሁ።» ያን ለማድረግም በኢትዮጵያ የባህል ሚንሥትርን ማነጋገር እፈልጋለሁ ብላለች። ራማቱ ከአማርኛ ቋንቋ ባሻገር ፊልሟን በዓረቢኛ እና ኪስዋሒሊ ቋንቋዎችም ማስተርጎም ትፈልጋለች። ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያ አፍሪቃውያን ቋንቋ እና ባህላቸውን እርስ በእርስ መተዋወቅ እና መለዋወጥ ያስፈልጋቸዋል ስትልም አስረግጣ ትናገራለች።

«አፍሪቃ በጣም ውብ ናት።  እናም ያን ውበቷን ማሳየት አለብን።  ያን እኛ ካላደረግን ማንም አያደርም። ባህላችንን እንዴት እርስ በእርስ ማስተዋወቅ እንዳለብንም ማጤን ያሻል። እኔ ወደ ኢትዮጵያ ስሄድ ሁሉም በአማርኛ ነው የሚያናግሩኝ። እኔ ግን ኢትዮጵያዊ አይደለሁም። አንዳንድ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የጸጉር አሠራሩ ራሱ ከሀገሬ ጋር ተመሳሳይ ነው።» 

«የጋብቻ ቀለበቱ» በተሰኘው ፊልም ውስጥ ዋናውን ገጸ ባሕሪ የምትጫወተው ተዋናዪት የአዘጋጅዋ ልጅ ናት። የፉላኒ ቋንቋውን ከፊልም ዳይሬክተር እናቷ ነው የተማረችው። ግንባሯ ላይ የተነቀሰችው ምስል እና መልኳን ላየ ኢትዮጵያዊት ናት ብሎ ሊሳሳት ይችላል። ተወልዳ ያደገችው ግን ፈረንሳይ ውስጥ ነው።

«እኛ በምዕራብ አፍሪቃ የምንገኝ ሰዎች እናንተ ስለእኛ ከምታውቁት በተሻለ ስለእናንተ እናውቃለን። ያ ለምን እንደሆነ እንጃ። ግን እኛ ስለእናንተ ታሪክ፤ ለነፃነት ስላደረጋችሁት ተጋድሎ፤ ስለ ንጉሦቻችሁ እና ታሪካችሁ በአጠቃላይ እናውቃለን። እናንተ ግን ስለ እኛ አታውቁም። ለአብነት ያህል ትልልቅ ጥንታዊ ከተሞች እንዳሉን፤ በፊልሜ ውስጥ እንዳየኸው አይነት ቤተ-መንግሥቶች እንዳሉን፤ ስለ ውብ ሥነ-ሕንጻዎቻችንም አታውቁም። ስለዚህ ያን ማሳየት አለብን። ማንነታችንንም ለእራሳችን እና ለዓለም ማሳየት አለብን። ሌላው ዓለም ስለ አንተ እንዲያሳይ አትጠብቅ።  እነሱ ብዙውን ጊዜ እኛን የሚወዱ አይደሉም። አንተ ማን እንደሆንክ እነሱ ብቻ እንዲነግሩህ አታድርግ።»

ሆላንድ ውስጥ በአምስተርዳም ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ያገኘኋቸው የሲኒማ አፍቃሪዋ ፊዮና ፎሪንክ ላለፉት አምስት ዓመታት በፌስቲቫሉ የቀረቡ ፊልሞች አምልጧቸው አያውቅም። መሰል የፊልም ፌስቲቫሎች ስለ አፍሪቃ እና የአኅጉሪቱ ነዋሪዎች የበለጠ ለማወቅ ይረዳል ይላሉ።

Niederlande Amsterdam - Rahmatou Keita The wedding Ring in World Cinema Amsterdam 2017 (DW/M. Sileshi )

የፊልም አፍቃሪው ኡቱንግ ቡተር በአምስተርዳም ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫል

«አፍሪቃን እንደ አንድ ሀገር መመልከቱ አስቂኝ ነው። አፍሪቃ የ,ራሳቸው ባህልና ማንነት ያላቸው በርካታ ሃገራት የሚገኙባት ግዙፍ አኅጉር ናት። በአንዳንድ ሃገራት እንደውም በርካታ ጎሳዎች ይገኛሉ። አፍሪቃ በርካታ ባህል ቢኖራትም እኛ የምናየው ድህነት እና ረሐብ ብቻ ነው። የምናየው ያን ነው እንጂ በዚህ ፌስቲቫል እንደቀረበው አይነት የበለጸገ ባህሏን አናይም። ስለዚህ ፌስቲባሉ የእያታ አድማሴን አስፍቶታል።»

በአምስተርዳም ከተማ ነዋሪ የሆኑት ኡንቱንግ ቡተር የራማቱ ኪየታን «የጋብቻ ቀለበቱ» ፊልም መመልከታቸው ስለ አፍሪቃ ባህል የበለጠ እንዲያውቁ አድርጓቸዋል።
«የትም ሳትጓዝ የተጓዝክ ያህል ዕድል ይሰጥሃል። የዘንድሮው ፌስቲቫል በተለይ የሌላኛው ዓለም ክፍል ምን እንደሚመስል በበርካታ ሃገራት ውክልና አሳይቷል። ለምሳሌ ትናንት አንድ የኒዠር ፊልም ተመልክቻለሁ። ቀደም ሲል ስለ ሀገሪቱ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም። ንጉሣዊ ሥርዓት እንደነበራቸውም አላውቅም ነበር።  ስለዚህ ፌስቲቫሉ ሌሎች ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩ ምን እንደሚሠሩ የማወቅ ዕድሉን ይሰጥሀል። የሌላ ሀገር ባህልን ከማስተዋወቅም ባሻገር ይበልጥ ቀርበህ እንድትመለከተው ያደርግሀል። ያ የፊልም ውበት ነው።»

«የጋብቻ ቀለበቱ» የተሰኘው የራህማቱ ኪየታ ሁለተኛ ረዥም ፊልም እንደ ቶሮንቶ ባሉ ተለቅ ያሉ ፌስቲቫሎች ላይም ለእይታ ቀርቧል። ራህማቱ «የጋብቻ ቀለበቱ»ን ከመሥራቷ በፊት ቀደም ሲል አሊሲ የተሰኘ በካን ፊልም ፌስቲቫል ላይ ለእይታ የበቃ ዘጋቢ ፊልም ሠርታለች። ራህማቱ በሁለተኛ ፊልሟ ወደ ፊቸር ፊልም ብትዞርም ፊልሙ በአብዛኛው የዘጋቢ ፊልም ላይ በጉልህ የሚስተዋለው እውነታን እንዳለ የማቅረብ ስልት ጠንከር ብሎ ይታይበታል። ኒዠር፤ ቡርኪናፋሶ እና ፈረንሳይ ውስጥ የተሠራው የራህማቱ ፊልም ጀርመን ውስጥ በኮሎኝ እና በሐምቡርግ ከተሞች የታየ ሲሆን በተለያዩ የፊልም ፌስቲቫሎች ለእይታ ይበቃል። እንደ አማርኛ ቋንቋ አምባሳደር በየሀገሩ የምትዘዋወረው ራህማቱም ለአማርኛ ቋንቋ እድገት የጀመረችውን ጥረት መቀጠሏን አታቋርጥም።

 

Source: DW Amharic

የወገን ደራሽ ወገን ወገን ነው!

0

የወገን ደራሽ ወገን ወገን ነው!

አርቲስት መላኩ ቢረዳ በጠና ታሟል። አርቲስት መላኩ ቢረዳ አሁን በስልጣን ያለውን ስርዓት በቃወም “ወያኔ” የሚል የጉራግኛ ዘፈን በመዝፈኑ ምክንያት ብዙ እንግልትና ድብደባ ደርሶበት፣ ሀብትና ንብረቱ ተዘርፎ ከአገር እንዲወጣ መገደዱ የሚታወቅ ነው። አርቲስቱ በደረሰበት ድብደባ እጁ ከመሰበሩም አልፎ ብዙ የጤና እክሎች እንዲደርስበት ምክንያት ሆኗል። አሁን ላይ በተሰደደበት አገር በጠና ታሞ ህክምናውን በመከታተል ላይ ነው። ህክምናው ከባድ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ የሁላችንም እርዳታ ይፈልጋል። አርቲስት መላኩ ቢረዳ ከአገር ከተሰደደበት ከአንድ አመት በፊት ጀምሮ ማንንም ላለማስጀገርና የሰው ፊት ላለመቅረብ ህክምናውን በራሱ ወጪ እየሸፈነ ሲታከም ቆይቷል። ዛሬ ሁላችንም አለንልህ ልንለው ይገባናል።

አርቲስት መላኩ ቢረዳ ከአገር ከመሰደዱ በፊት “ትዊስት በጉራግኛ”፤ “ሟን ተሟን ያርስ” ና “ወያኔ/ተሳንዴ ጉራጌ” የተሰኙ ሶስት አልበሞች ለህዝብ በማቅረብ ከሦስቱም አልበሞች የሚገኘው ገቢ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንዲሆን አበርክቷል። ከአገር ከተሰደደም በኋላ ድምፃ አልባ ለሆነው ህዝባችን በማህበራዊ ድረ-ገፅና በሌሎች ሚዲያዎች ድምፁን ሲያሰማ ቆይቷል። የዚህን ሰው ወዳድ፣ አክባሪ፣ አዛኝና ታጋይ ወንድማችን ጤና ይመለስ ዘንድ ሁላችንም የበኩላችን እንድናደርግ ጥሪያችን እናቀርባለን።  ጓደኞቹ

እርዳታ ለመድረግ የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ: GoFundMe

በሸበጥ ጫማ ማራቶን የሮጠው ኢትዮጵያዊ አትሌት አሞኘ ሰንደቁ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል

0

በሸበጥ ጫማ ማራቶን የሮጠው ኢትዮጵያዊ አትሌት አሞኘ ሰንደቁ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል
ኢትዮጵያዊው አትሌት አሞኘ ሰንደቁ በቻይና በተካሄደ የማራቶን ውድድር ላይ በሸበጥ ጫና ሮጦ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል።
አትሌት አሞኘ በመካከለኛ የቻይና ግዛት በተካሄደው የሶንግሻን ሻዎሊን ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር ላይ ነው በሸበጥ ጫማ ሮጦ ውድድሩን በአንደኝነት ማጠናቀቅ የቻለው።
የማራቶን ውድድሩን ለማጠናቀቅም 2 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ እንደፈጀበትም ተነግሯል።
በዚህም አሞኘ የ20 ሺህ የቻይና ዩዋን እና የወርቅ ሜዳለሊያ አሸናፊ መሆን ችሏል።
አትሌት አሞኘ ሰንደቁ ከሳምንት በፊት በቻይና ጋንሱ ግዛት ጂጉዋን ዓለም አቀፍ  ማራቶን ላይ በመካፈልም በሸበጥ ጫማ ሮጦ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል።

ምንጭ፡-ኤፍ.ቢ.ሲ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

0

 

አቶ መለስ ዓለም ዛሬ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሕገ ወጥ መንገድ ዛምብያ ገብተዋል የተባሉት ስደተኞች ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ጉዳይ ላይ ከዛምብያ መንግሥት ጋር ድርድር እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

ዛምቢያ የሚገኙ የታሰሩ 118 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የመሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሕገ ወጥ መንገድ ዛምብያ ገብተዋል የተባሉት ስደተኞች ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ጉዳይ ላይ ከዛምብያ መንግሥት ጋር ድርድር እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። ቃል አቀባዩ ኤች አር 128 በሚል ስያሜ ተዘጋጅቶ ለአሜሪካን ምክር ቤት ስለቀረበው እና ኢትዮጵያን ስለተመለከተው ረቂቅ ሕግ ለቀረበላቸው ጥያቄም መልስ ሰጥተዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኅይለ ጊዮርጊስ ተከታትሏል።

ጌታቸው ተድላ ኅይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

የጣፊያ ካንሰር፤ መንስኤ፣ ምልክቶችና ህክምና…

0

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጣፊያ ካንሰር ሰዎችን በብዛት ለሞት ከሚዳርጉ የካንሰር ህመም አይነቶችው ውስጥ አንዱ እንደሆነ ይነገርለታል።

ምክንያቱ ደግሞ በሽታው ከፍተኛ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ መታየት አለመቻሉ ነው ይባላል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2014 በእንግሊዝ ብቻ 9 ሺህ 600 ሰዎች በህመሙ መያዛቸው በህክምና የታወቀ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ ከ8 ሺህ 800 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።

የጣፊያ ካንሰር ስሙ እንደሚያመለክተው ከሰውነታችን ክፍል አንዱ የሆነውን ጣፊያችንን የሚያጠቃ የበሽታ አይነት ነው።

የጣፊያ ስራ ኢንዛይሞችን ማምረት ሲሆን፥ ኢንዛይሞቹም ምግብ ለመፍጨት እና በደማችን ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር የሚረዱ ናቸው ተብሏል።

የጣፊያ ካንሰር ምልክቶች

በብዛት ከሚስተዋሉ የጣፊያ ካንሰር ምልክቶች ውስጥ አንዱ የላይኛው የሆዳችን ክፍል አካባቢ የሚስተዋል ህመም ሲሆን፥ ህመሙ አንዳንዴ ወደ ጀርባችን ዞሮም ሊሰማን ይችላል።

የህመሙ ስሜት መጀመሪያ ላይ ይከሰትና ወዲያው እንደሚጠፋ የተነገረ ሲሆን፥ ምግብ ከተመገብን በኋላ በምንተኛበት ጊዜ ግን ከፍተኛ የሆነ የህመም ስሜት ይሰማናል ነው የተባለው።

ሌላው ምልክት ደግሞ ድንገተኛ የሆነ የሰውነት ውፍረት (መጠን) መቀነስ፣ የሰውነት ቆዳ ቀለም ወደ ቢጫነት መቀየር ሲሆን፥ የሰገራ ቀለም መለዋወጥ እና የሽንት ቀለም ወደ ደማቅ ቢጫነት አሊያም ብርቱካናማነት መቀየርም የህመሙ ምልክት ሊሆን ይችላል።

ከዚህ በተጨማሪም፦

  • ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ
  • ከፍተኛ የሰውነት ትኩሳት እና ማንቀጥቀጥ
  •  ምግብ አለመፈጨት
  • የደም መርጋት
  • ከመጠን ያለፍ የሰውነት መዛል ወይም ድካም

እንዲህ አይነት ምልክቶች በብዛት የሚስተዋልብን ከሆነ በአፋጣኝ ወደ ህክምና ማእከላት በመሄድ የጤና ባለሙያዎችን ማማከር እንዳለብን ነው የሚመከረው።

የጣፊያ ካንሰር ምንስኤ

ምንም እንኳ የጣፊያ ካንሰር ይህ ነው ተብሎ ግልፅ ሆኖ የተቀመጠ ነገር ባይኖርም፤ የህመሙን ተጋላጭነት የሚጨምሩ ምክንያቶች ግን ይታወቃሉ።

ከእነዚህም ውስጥ እድሜ፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ውፍረት (ክብደት) እና የመሳሰሉት የጣፊያ ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚያሰፉ ነው የሚነገረው።

የጣፊያ ካንሰር ህክምና

የጣፊያ ካንሰር ህክምና በህመሙ አይነት እና ከካንሰሩ የሚገኝበት ስፍራ እንዲሁም የሚገኝበት ደረጃ ላይ ተመስርቶ እንደሚለያይ ነው የጤና ባለሙያዎች የሚያብራሩት።

ዋናው ኢላማ የካንሰር እጢውን ከሌሎች የካንሰር ህዋስ ጋር ሙሉ በሙሉ ጠርጎ ማስወጣት ሲሆን፥ ይህ ካልሆነ ግን የካንሰር እጢው እንዳያድግ የሚከላከል ህክምና ይሰጣል።

የጣፊያ ካንሰርን ለማከም ሶስት አይነት ይህክምና መንገዶች እንዳሉ የሚያብራሩት የህክምና ባለሙያዎቹ፥ የመጀመሪያው ህክምና በቀዶ ጥገና የካንሰር እጢውን ሙሉ በሙሉ ማስወደግ ነው ይላሉ።

ሌሎቹ የህክምና መንገዶች ደግሞ የካንሰሩ መጠን እንዳይሰፋ የሚያደርግ እና የህመም ስሜቱ እንዲቀንስ የሚረዱ የኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ ህክምናዎች መሆናቸውንም ያብራራሉ።

በመዲናዋ ለሸማች ህብረት ስራ ማህበራት እየተከፋፈለ ነው የተባለው ስኳር እስካሁን ህብረተሰቡ ዘንድ አልደረሰም

0

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በአዲስአበባከተማ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ለሸማች ህብረት ስራ ማህበራት እየተከፋፈለ ነው የተባለዉ ስኳር ዛሬም ህብረተሰቡ ዘንድ ሙሉ በሙሉ መሰራጨት አልጀመረም።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተዘዋውሮ ቅኝት ባደረገባቸው አንዳንድ የሸማች ማህበራት ስኳሩ መግባት የጀመረ ሲሆን፥ ተጠናቆ ወደ መጋዝን ባለመግባቱ በሚል ምክንያት ስርጭት አለመጀመሩን አረጋግጧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በበኩሉ፥ ወርሃዊ መዲናዋ ፍጆታ የሆነው 120 ሺህ ኩንታል ስኳር በመረከብ ለሸማች ህብረት ስራ ማህበራት መከፋፈል መጀመሩን አስታውቋል።

ሁሉም የሸማች ህብረት ስራ ማህበራትም ወርሃዊ ፍጆታቸን ከጅንአድ እንዲረከቡ ጥሪ ማቅረቡንም ነው ቢሮው ያስታወቀው።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በመዲናዋ አንዳንድ ስፍራዎች ባካሄደው ቅኝት እስከዛሬ ድረስ ስኳር ያልደረሳቸው የተወሰኑ የሸማች ማህበራት መኖራቸውን መመልከት ችሏል።

የተሰወኑ ስፍራዎች ላይ ደግሞ ለህብረተሰቡ በነፍስ ወከፍ ከሶስት ኪሎ ጀምሮ ሲከፋፈልም ታይቷል።

አንዳንድ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ደግሞ ለወርሃዊ ፍጆታ የሚያስፈልገው ስኳር ሙሉ በሙሉ አልገባም በሚል ለሸማቹ ስኳር ማቅረብ አልጀመሩም።

እነዚህ ማህበራት ከነገ ጀምሮ ለቸርቻሪ ነጋዴዎች እና ለህብረተሰቡ ማሰራጨት እንደሚጀምሩም ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ወልደሰንበት፥ ስኳሩ በትክክል ህብረተሰቡ ጋር መድረሱን የሚከታተል የቁጥጥር ግብረ ሀይል መቋቋሙን ተናግረዋል።

ሁሉም የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ስኳር ከማከፋፈያ የወሰዱትን እና በእጃቸው የሚገኘውን ስኳር ማከፋፈል እንዲጅመሩ ይደረጋልም ብለዋል።

 

 

በትዕግስት ስለሺ