Home Blog Page 435

መሐመድ አል-አሙዲን ጨምሮ ሳዑዲ አረቢያ 38 ሰዎችን አሰረች

0

ሳዑዲ አረቢያ በጸረ-ሙስና ዘመቻ 11 ልዑላን፣ አራት በሥልጣን ላይ ያሉ ምኒስትሮች እና በርካታ የቀድሞ ሹማምንትን አሰረች። ሮይተርስ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የሳዑዲ ባለሥልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው መሐመድ አል-አሙዲ ከታሰሩት መካከል አንዱ ናቸው። ኪንግደም ሖልዲንግ የተባለው የመዋዕለ-ንዋይ ኩባንያ ባለቤት ልዑል አልዋሊድ ቢን ታላል ከአስራ አንዱ ልዑላን መካከል ይገኙበታል። የሳዑዲ አረቢያ ብሔራዊ ዘብ አዛዥ የነበሩት ልዑል ሚተብ ቢን አብዱላሕ ታስረው ከሥልጣናቸው ሲሻሩ በልዑል ኻሊድ ቢን አያፍ ተተክተዋል። 38 ልዑላን፣ ሚኒሥትሮች እና እውቅ ባለወረቶች ትናንት ቅዳሜ የታሰሩት ንጉስ ሰልማን በልጃቸው ልዑል መሐመድ የሚመራ የጸረ-ሙስና ኮሚቴ መቋቋሙን ካስታወቁ በኋላ ነው። ኮሚቴው የእስር ማዘዣ የመቁረጥ፣ የተጠርጣሪዎችን ሐብት እንዳይንቀሳቀስ የማገድ እና የጉዞ ማዕቀብን የመጣል ጨምሮ በርካታ ስልጣኖች ተሰጥተውታል። የ32 አመቱ አልጋወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን አልሳዑድ ሙስናን ለመታገል ቃል ገብተው ነበር።

ሳዑዲ በ500 ቢ. ዶላር ግዙፍ ከተማ ልትቆረቁር ነው

0

የከተማው ስፋት የኒውዮርክ ሲቲን 33 እጥፍ ያክላል ተብሏል

ሳዑዲ አረቢያ 26 ሺህ 500 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ያለውና ከኒውዮርክ ሲቲ 33 እጥፍ ያህል የቆዳ ስፋት የሚኖረውን ኒኦም የተሰኘ እጅግ ግዙፍ ከተማ፤ በ500 ቢሊዮን. ዶላር ወጪ ልትቆረቁር መዘጋጀቷን ከሰሞኑ ይፋ አድርጋለች፡፡
በሰሜን ምዕራባዊ የሳዑዲ ግዛት የቀይ ባህርን ዳርቻ ታክኮ የሚቆረቆረው አዲሱ ከተማ ኒኦም፤ ለኑሮ፣ ለንግድና ለመዝናኛ በአለማቀፍ ደረጃ ቀዳሚ ተመራጭ ከተማ እንዲሆን ለማድረግ ሰፊ እቅድ ተይዞ ወደ ስራ መገባቱን የዘገበው ሮይተርስ፤ ከተማው የሚቆረቆርበት ስፍራም ለእስያ፣ አውሮፓና አፍሪካ አገራት በቀላሉ ተደራሽ መሆኑን አመልክቷል፡፡
ራዕይ 2030 የተባለውና የአገሪቱን ኢኮኖሚ ወደተሻለ ለውጥ በማሸጋገር ለዜጎች ተጨማሪ የስራ ዕድሎችን የመፍጠር ግብ ያስቀመጠው ዕቅድ አካል የሆነው ይህ ግዙፍ ከተማ፤የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከል ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሳዑዲው ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን አስታውቀዋል፡፡
ከተማው እጅግ የተዋበ፣ በረቀቀ ቴክኖሎጂ የተሟላ፣ ሙሉ ለሙሉ በታዳሽ ሃይል አቅርቦት የሚሰራ እንደሚሆንና ራሳቸውን የቻሉ በጣም ሰፋፊ የቢዝነስና የኢንዱስትሪ ዞኖች አንደሚኖሩት የጠቆመው ዘገባው፤ የግንባታው የመጀመሪያ ምዕራፍ በ2015 ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚገመትም አመልክቷል፡፡
የአለማችን ቁጥር አንድ ነዳጅ አምራች የሆነቺው ሳዑዲ አረቢያ፣ የነዳጅ ዋጋ ከቀነሰበት ከ2014 አንስቶ በኢኮኖሚዋ ላይ ከፍተኛ መቀዛቀዝና የፋይናንስ እጥረት መታየቱን ያስታወሰው ዘገባው፤ የአገሪቱ መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከልም ከመጪው ጥር ወር ጀምሮ የተጨማሪ እሴት ታክስ ለማስከፈል ማቀዱ እንደሚገኝበትም አክሎ ገልጧል፡፡

 

 

ምንጭ: አዲስ አድማስ

የማር ዘርፈ ብዙ የጤና በረከቶች

0

ማር በተፈጥሮ ብዙ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

1. ንጹህ ማር በቫይታሚን እና በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ ሲሆን እነዚህ ቫይታሚኖች እና ንጥረ ነገሮችም ሰውነታችንን ከባክቴሪያዎች ይከላከላሉ፡፡

• ማር የሰውነታችንን የበሽታ መከላከል አቅም ይጨምራል፡፡

• ጉንፋን ሲይዘን እና የሚያስለን ከሆነ አንድ ወይም ሁለት የሻይ ማንኪያ ማር በትኩስ ውሃ ውስጥ መበጨመር አንዲሁም የተወሰነ ሎሚ እና ቀረፋ በማድረግ መጠቀም ይቻላል፡፡

2. ማርን በትኩስ ውሀ ውስጥ ከሎሚ ጋር በመጨመር ጠዋት ምግብ ከመውሰዳችን በፊት ከወሰድን በሰውነታችን ውስጥ የሚገኝ ቆሻሻን እና ቅባትን ያስወግዳል፣ የሰውነት ክብደትንም እንዲንቀንስ ይረዳል፡፡

3. ማርን ከቀረፋ ጋር በመደባለቅ የምንወስድ ከሆነ የሰውነታችንን የኮሌስትሮል መጠን በ10 በመቶ መቀነስ የምንችል ሲሆን  በሚገባ ከወሰድን ለልብ በሽታ ያለንን ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡

• አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ቀረፋ ጋር በትኩስ ውሃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣት፡፡

4. በሀይል ሰጪነቱ ከፍተኛ ጥቅም ያለው ማር ከቡና ባልተናነሰ ሰውነታችን ያነቃቃል፡፡

5. ማር ለቆዳችን ልስላሴ እና ጥራት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

• ማር ባክቴርያን እና ፈንገስን መከላከል ስለሚችል ለበርካታ የቆዳ ችግሮች መፍትሄ የሚሆን የምግብ አይነት ነው፡፡

• በተጎዳው ቆዳ ላይ በመቀባት አንድ ሌሊት ማሳደር እና ጠዋት ጠዋት በንጹህ ውሃ መታጠብ ፡፡ ይህንን በተደጋጋሚ የምናደርግ ከሆነ ለስላሳ እና ንጹህ ቆዳ እንዲኖረን ይረዳናል፡፡

6. የምግብ አለመፈጨትን ይቀንሳል ፡፡

አንድ ወይም ሁለት የሾርባ ማንኪያ ማር ከበድ ያሉ ምግቦችን ከመመገባችን በፊት ብንወስድ አሊያም ምግብ ተመግበን የመክበድ ስሜት ከተሰማን በኋላ መውሰድ የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል፡፡

ምንጭ: FBC

የኦሮሞና የአማራ ህዝቦች የትስስር መድረክ ዛሬ በባህር ዳር እየተካሄደ ነው

0

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2010(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ የጋራ የምክክር መድረክ ዛሬ በባህር ዳር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፥ የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ከጋብቻ እስከ ጉዲፈቻ በደም እና በባህል የተሳሰሩ ናቸው ብለዋል።

በዚህም “የኢትዮጵያውያን አብሮነት እና አንድነት እያበበ እና እየጠነከረ የሚሄድ እንጂ እንደ እንፋሎት የሚተን፣ እንደጉም የሚበን አይደለም” ሲሉም አቶ ገዱ ገለጸዋል።

“የሁለቱን ህዝቦች የጠበቀ አንድነት ለመሸርሸር እና በመካከላቸው ግጭት ለመፍጠር የሚጥሩ ሃይሎች በሁለቱ ህዝቦች ትብብር ክፉ ድርጊታቸው ይመክናል፤ እየመከነም ነው” ብለዋል።

“በሁለቱ ህዝቦች መካካል ያለው ትስስር የትኛውም የፖለቲካ አካል ከሚያውቀው እና ከሚገምተው በላይ ጥብቅ እና ጥልቅ ነው” ያሉት አቶ ገዱ፥ በሁለቱም ክልሎች የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ተከባብሮ እና ተዋዶ የመኖር እሴት እንዳላቸውም አንስተዋል።

“ወጣቱ ትውልድ ንፋስ አመጣሽው የልጅነት ሃሳብ እና የፈጠራ አጥፊ ቅስቀሳን ወደ ጎን በመግፋት፥ የኖረ እና የነበረ አባቶቹን ያወረሱትን አንድነት እና አብሮነት ሊጠብቅ ይገባዋልም” ነው ርእሰ መስተዳድሩ።

“የአማራ ክልል ህዝብ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራስያዊ አንድነት፣ ሁሉም ዜጎች እኩል የሚኖሩባት አዲሲቷ ኢትዮጵያን የመገንባት ጥረት ከሌሎች የአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ጋር ተባብሮ ከዳር ለማድረስ ቁርጠኛ ነው” ብለዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው፥ ኩራት የሆነ ኢትዮጵያዊ ማንነት ሊጠበቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።

 

 

መድረኩ “አብሮነታችን ለሰላማችን፤ ሰላማችን ለአብሮነታችን!” በሚል መሪ ቃል የሁለቱ ህዝቦች የምክክር መድረክ እየቀጠለ ነው።

ኮንፍረንሱን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ እና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋችዉ በጋራ ይመሩታል።

ndr.jpg

Dance_1.jpg

Bahir_Dar.jpg

በዚህ የትስስር መድረክ ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉ ተብለው ይጠበቃል፡፡

ምሁራን ከየዩኒቨርሲቲዎቻቸው ሀሳባቸውን ያጋራሉ፤ ሲምፖዝየም እና የኪነጥበብ ስራዎች መርሀግብሮችም ተሰናድተዋል።

መድረኩ “አብሮነታችን ለሰላማችን፤ ሰላማችን ለአብሮነታችን!” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ ነው የተመለከተው።

በኮንፍረንሱ ላይ የሚሳተፉ ከ20 የኦሮሚያ ዞኖች እና ከ18 ከተሞች የተወጣጡ ከ250 በላይ የሚሆኑ የኦሮሞ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና አርቲስቶች ተገኝተዋል።

በአጠቃላይ በመድረኩ ከ1500 በላይ ተሳታፊዎች በመታደም ላይ ይገኛሉ።

ምንጭ ፋና

ሰላማዊ ሰልፈኞች በኤርትራ ተገድለዋል ተባለ

0

 

በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ በተካሄደ ተቃዉሞ ሰዎች መገደላቸዉና መጎዳታቸዉ ተነገረ። የሟቾቹ ቁጥር በገለልተኛ ወገን ባይጣራም 28 መድረሱን የተለያዩ የዜና አዉታሮች የመንግሥት ተቃዋሚ አካላትን በመጥቀስ ዘግበዋል።

አስመራ ከተማ የሚገኝን አንድ የግል ትምሕርት ቤት መንግሥት ወደ ህዝብ ትምሕርት ለመቀየር ያለውን እቅድ በመቃወም ባለፈው ማክሰኞ በትምህርት ቤቱ የተቃውሞ ሠልፍ መካሄዱን የተለያዩ ዘገባዎች አመልክተዋል። በዚህም የተነሳ የትምሕርት ቤቱን የበላይ ጠባቂ ሀጂ ሙሳ ኑርን ጨምሮ  በርካታ የትምሕትር ቤቱ የኮሚቴ አባላት መታሠራቸውን ነዋሪነታቸው ለንደን የሆነ የኤርትራ ሰብዓዊ መብት አቀንቃኝ አቶ አብዱራህማን ሠይድ ለዶቼቬለ ገልጸዋል። የተቃውሞ ሠልፉን የሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው « መጠነኛ እና የሠው ህይወት ያልጠፋበት »ሲሉ ቢገልጹትም ቆይተው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግን ሠዎች መገደላቸውን እየገለጹ ነው። አዣንስ ፕሬስ የዜና ወኪል አንድ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ መሪን ጠቅሶ እንደዘገበው የሟቾች ቁጥር 28 ደርሷል። የሠብዓዊ መብት አቀንቃኙ አቶ አብዱራህማን ሠይድ  በበኩላቸው ከአስመራ ደረሰኝ ባሉት መረጃ መሠረት ይህንኑ ያጠናክራሉ። ላለፉት 5 ዓመታት መኖሪያውን ኖርዌይ ያደረገው ኤርትራዊው ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አቶ ደሳለኝ በረከት የሠው ህይወት በመጥፋቱ ቢስማማም ትክክለኛ የሟቾችን ቁጥር መግለፅ ግን አስቸጋሪ ነው ይላል።ይህ በመንግሥት በኩል እየተወሰደ ያለው እርምጃም አድማው በድጋሚ እንዳይካሄድ ለማስፈራራት የተደረገ ነው ሲል አቶ አብዱራህማን ይናገራል። እንደ አቶ አብዱራህማን ገለጻ በአስመራ ከተማ ሆያ ትምሕርት ቤት የተካሄደው የተቃውሞ አመጽ ጊዜያዊ ሳይሆን ባለፉት 25 ዓመታት በህዝቡ ይደርስ የነበረው ጭቆና ውጤት ነው። በመሆኑም የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት ሰጥቶ የሀገሪቱን ህዝብ ሊደግፍ ይገባል ሲየሰብዓዊ መብት አቀንቃኙ አቶ አብዱራህማን አሳስበዋል። ጉዳዩን በተመለከተ ኤርትራ አዲስ አበባ እና ብራሰልስ የሚገኙትን የኤርትራ መንግሥት ተወካዮች በስልክ ለማነጋገር በተደጋጋሚ ብንሞክርም ሊሳካልን አልቻለም።
ምንጭ ዶቼቬሌ አማርኛ

የደም አይነታችን ስለኛ ብዙ እንደሚናገር ያውቃሉ

0

 

 

የደም አይነታችን ስለኛ ብዙ እንደሚናገር ያውቃሉ?

አራቱ የደም አይነቶች “ኤ”፣ “ቢ”፣ “ኤቢ” እና “ኦ” በተለይም ስለ ጤንነታችን በርካታ ጉዳዮችን እንደሚናገሩ ነው ባለሙያዎች የሚገልፁት።

ለአብነትም የደም አይነታቸው “ኤቢ” የሆኑ ሰዎች አርቀው የሚመለከቱ እና በነገሮች ላይ ተስፋ የሚጥሉ እና ለልብ ህመም የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል።

“ኦ” የደም አይነት ያላቸው ሰዎች ደግሞ ለጭንቀት ቦታ የሌላቸው እንደሆኑ የሚነገር ሲሆን፥ በሆድ ህመም የመጠቃት እድላቸው ደግሞ የሰፋ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በርካታ ጥናቶች እያንዳንዱ የደም አይነት የራሱ በጎ እና መጥፎ ጎኖች እንዳሉት አመላክተዋል።

በመሆኑም የደም አይነታችን ማወቅ ጤናችንን የበለጠ ለመጠበቅ እንደሚረዳ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት።

እርግጥ ነው እድሜ፣ ጾታ፣ በራሂዎች (ጂኖች) እና ሌሎችም ምክንያቶች በተለያዩ ህመሞች የመጋለጥ እድላችን የማስፋት ወይም የማጥበብ አቅም ይኖራቸዋል።

ጤናማ አመጋገብና የኑሮ ዘይቤ ከተለያዩ እክሎች በፍጥነት ለመውጣት እንደሚያግዙም ሊዘነጋ አይገባውም።

ከዚህ በታችም የደም አይነታችን ከጤንነት ሁኔታችን ጋር እንዴት ይያያዛል? የሚለውን እንመለከታለን።

“ኤ” የደም አይነት

ባለሙያዎች እንደሚሉት “ኤ” የደም አይነት ያላቸው ሴቶች ለበርካታ አመታት ልጆችን መውለድ ይችላሉ።

ይህ አይነት የደም አይነት ያላቸው እንስቶች ለረጅም አመታት የዘር እንቁላሎችን የማፍራት አቅም አላቸው ተብሏል።

በመሆኑም እነዚህ ሰዎች “እድሜዬ ሳይገፋ በፍጥነት መውለድ አለብኝ” በሚል ሊጨነቁ አይገባም ነው የሚሉት ተመራማሪዎች።

“ኤ” የደም አይነት ያላቸው ሰዎች አልኮል የተለያዩ የህመም ስሜቶችን በቀላሉ ያባብስባቸዋል።

ለሆድ ካንሰር የመጋለጥ እድላቸውም ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል።

“ቢ” የደም አይነት

ስፖርትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የምታዘወትሩ እና የምታፈቅሩ “ቢ” የደም አይነት ያላችሁ ሰዎች በጣም እድለኞች ናችሁ ተብላችኋል።

ይህ የደም አይነት ሰውነታችን በተለይም ጡንቻዎቻችን ለአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ዝግጁ እንዲሆኑ ያደርጋል።

የምግብ መፈጨት ሂደት እንዲቀላጠፍም ያግዛል።

ይሁን እንጂ የደም አይነታቸው “ቢ” የሆኑ ሰዎች ለጣፊያ ካንሰርና ለሆድ ህመም የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።

ለከፍተኛ የመርሳት በሽታ (አልዛይመር) እና ከፍ ሲልም ለአዕምሮ መሳት ሊዳርግ እንደሚችል ነው የሚነገረው።

“ኤቢ” የደም አይነት

ይህ የደም አይነት ያላቸው ሰዎች በሰውነታቸው ውስጥ ኮርቲሶል የተሰኘ ሆርሞን ለረጅም ጊዜያት በተመሳሳይ ሁኔታ መገኘት ከጭንቀት ነፃ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።

ለበርካታ ስዓታት ያለ ድካም የመስራት ብቃት የማላበስ ባህሪ እንዳለውም ይነገራል።

የደም አይነታቸው “ኤቢ” የሆኑ ሰዎች የማስታወስ ችግር ይሰተዋልባቸዋል ይላል በጆርናል ኒዮሮሎጂ ላይ የወጣ ጥናት።

በተለይም እድሜያቸው የገፋ ሰዎች በዚህ ችግር የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል።

ኤቢ የደም አይነት ያላቸው ሰዎች ደም የመርጋት ችግር ያጋጥማቸዋል፣ ከፍተኛ የፕሮቲን መጠንም በደማቸው ውስጥ ይኖራል ነው የሚሉት፥ በአሜሪካ ቬርሞንት ዩኒቨርሲቲ የህክምና መምህር የሆኑትና ጥናቱን ካደረጉት ተመራማሪዎች አንዷ ሜሪ ኩሽማን።

ይህም እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ የማሰብ እና የማስታወስ ችግር እንደሚያስከትልባቸው ኩሽማን ገልጸዋል።

“ኦ” የደም አይነት

ተመራማሪዎች እንደሚሉት “ኦ” የደም አይነት ያላቸው ሰዎች ጭንቀትን በሚጨምሩ ሁኔታዎች እንኳን ሰውነታቸው የደስታና ሀዘን ስሜትን የሚቆጣጠረው ኮርቲሶል ሆርሞን መጠን የተረጋጋ ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል።

በዚህም ምክንያት በራስ ምታትና እንቅልፍ እጦት የመሰቃየት እድላቸው ዝቅተኛ ነው።

ይህ የደም አይነት የራሱ መጥፎ ጎኖችም አሉት፤ በተለይም ወንዶች በከፍተኛ ደረጃ ክብደት እንዲጨምሩ የማድረግ እድል አለው።

ሴቶችም የሚያመርቷቸው አነስተኛ እና ጥራታቸው ዝቅተኛ የሆኑ የዘር እንቁላሎች የማርገዝ እድላቸው ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ሊያደርግ ይችላል።

ይህ የደም አይነት ያላቸው ሰዎች በሆድ ህመም የመጠቃት እድል አላቸው።

የደም አይነታቸው “ኤቢ” የሆኑ ሰዎች “ቢ” እና “ኦ” የደም አይነት ካላቸው ሰዎች ለሆድ ካንሰር ተጋላጭነታቸው በ26 በመቶ ይጨምራል።

የአሜሪካ ጆርናል ኦፍ ኢፒደሚዮሎጂ ጥናት እንደሚያሳየው “ኤ” የደም አይነት ያላቸው ሰዎችም ከ“ቢ” እና “ኦ” ጋር ሲነፃፀር ለሆድ ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው በ20 በመቶ ከፍ ያለ ነው።

በአጠቃላይ ከላይ የተመለከትናቸው የደም አይነቶች እንዲሁም መልካም እና መጥፎ ገፅታዎቻቸውን መቀየር የሚቻል ባይመስልም፥ የኑሮ ዘይቤን ማስተካከል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ጭንቀት አለማብዛት እና በየጊዜው የጤና ምርመራ ማድረግ ጤናችን ለመጠበቅ ይረዳሉ።

 

ምንጭ፦ኤፍ.ቢ.ሲ

ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ህጻናት የማሰብ ችሎታቸው የላቀ ነው -ጥናት

0

 

 

ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ህጸናት ከሌሎች አንጻር ባህሪያቸውን መቆጣጠርና የተሻለ ትኩረት ማድረግ እንደሚችሉ በአሜሪካ ኦሪጎን ዩኒቨርስቲ የተደረገ አመልክቷል᎓᎓

ህጻናቱ የዕውቀት ደረጃቸውም ከፍ ያለ መሆኑንም ጥናቱ አረጋግጧል፡፡

ዕድሜያቸው አራት አመት እና ከዚያ በታች የሆኑ ሁለት ቋንቋ የሚናገሩ ልጆች ሌላ ቋንቋን ለመማር ፈጣን መሻሻሎችን እንዳሳዩ ነው የተደረገው ጥናት ያመለከተው᎓᎓

እንደ ጥናቱ ውጤት ከሆነ ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ህጻናት የመቆጣት ስሜትን የመቆጣጠር ችሎታቸው ከፍ ያለ መሆኑና ለመግራት ቀላል መሆናቸውን ጥናቱ ይጠቁማል፡፡

የህጻናቱ የማሰብ ችሎታውም የላቀ መሆኑን በኦሪጎን ዩኒቪርስቲ የተደረው ጥናት ያመለክታል፡፡

ምንጭ:EBC

Ethiopia | የጉሎ ዘይት ለፊትና ቆዳ ጤንነት

0

 

የጉሎ ዘይት ቢጫ ቀለም የያዘ የአትክልት ዘይት ሲሆን፥ ይህም የተለያዩ የሕክምና ሁኔታዎችን በተለይም በትንሽ አንጀት ውስጥ በሪሲኖሌክ አሲድ (ricinoleic acid) አማካኝነት ምግብ የመፍጨት ሂደት ያፋጥናል፥ እንዲሁም ለፊት እና ለቆዳ አንዳንድ ጥቅም እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት የጉሎ ዘይት ጥጥን በመጠቀም በቀላሉ ቆዳን መቀባት ይቻላል።

በዚህም በቆዳ ላይ የሚወጣ ሽፍታን ለመከላከል፣ ተሕዋሳትን ለማጥፋት እና የሰውነት ቆዳ እንዳይደርቅ ለማድረግ ይረዳል።

የጉሎ ዘይት ለፊት የሚሰጣቸው ጥቅሞች

 የቆዳ ሽፍታን ለመከላከል፦ የጉሎ ቅባት ባለው የመከላከል ባህሪ ምክንያት በፊት እና በቆዳ የሚወጡ ሽፍታ እና ተሕዋሳትን ይከላከላል።

 በፊት ላይ የሚታይ ሸካራነትን ለመከላከል፦ የጉሎ ዘይት የፊት ቆዳ ልስላሴን የሚጨምሩ አሲዶች የበለጸገ በመሆኑ የፊት ሸካራነትን ይከላከላል።

 የተጎዳ የፊት ቆዳ ለመመለስ፦ በጉሎ ዘይት ውስጥ ያሉት ቅባታማ አሲዶች ጤናማ የቆዳ ሕዋሳት እድገትን በማፋጠን የተጎዳ የፊት የቆዳ ክፍል ወደ ነበረበት ይመልሳል።

የጉሎ ዘይት ለቆዳ የሚሰጠው ጥቅሞች

 ፀረ ሽፍታ በመሆን ያገለግላል፦ የጉሎ ዘይት የቆዳ መቆጣት ባህሪ በመከላከል በቆዳ ላይ የሚታዩ የማሳከክ ባህሪ ያላቸው የቆዳ ሽፍታን ለማስታገስ ይረዳል።

 አንቲማይክሮብያል፦ በቆዳ ላይ ባክተርያ የሚደርስ ኢንፌክሽንን ይከላከላል።

 ቆዳን ልስላሴ ያላብሳል፦ ይህ የዘይት ዓይነት በውስጡ በያዘው ትሪገልይሰሪድስ አማካኝነት በቆዳ ውስጥ ያለውን ልስላሴ ለማቆየት እና ደረቅ ቆዳን ለማለስለስ ጠቀሜታ አለው።

man-in-front-of-mirror-inspecting-face-and-moisturizing-skin.jpg

 ቆዳን ለማፅዳት፦ በዘይቱ ውስጥ ያሉ ትራይግሊሰሪዶች በቆዳ ውስጥ የሚገኝ ቆሻሻን በየቀኑ ለማስወገድ ይረዳሉ።

በአጠቃላይ የጉሎ ዘይት በመጠቀም የቆዳ እና የፊት ጤንነት ለመጠበቅ ጠቀመታ ያለው ነው። በተጨማሪም የፊት ቆዳ ለማስዋብም ሆነ ልስላሴን ለመፍጠር ጠቃሚ ነው ሲሉ ባለ ሙያዎች ይመክራሉ።

ስልክዎን አጠገብዎ አድርገው የሚተኙ ከሆነ ይህን ምክር ያንብቡ

0

ወደ እንቅልፍ እያመራን በዚያው የሞባይል ስልካችንን ባትሪ እየሞላን እና እየተጠቀምን የምንተኛ ሰዎች ጥቂት አይደለንም።

በዩናይትድ ስቴትስ የተደረገ ጥናት እንደሚጠቁመው 53 በመቶ የሚሆኑ ታዳጊዎች ወይም በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ስልካቸውን ባትሪ የሚሞሉት አልጋቸው ላይ ጋደም ብለው እየተጠቀሙ በእንቅልፍ ሰዓት ነው።

በዚያው ባትሪ እየሞሉ ያሉትን ስልኮች አልጋ ላይ ትቶ ወይም ትራስ ውስጥ ወሽቆ መተኛት የተመለመደ ነው።

ይህም ሁኔታ ስልኩ ባትሪው እንዲሞላ በኤሌክትሪክ ላይ በመሰካቱ የሚለቀው ሙቀት እንዳይወጣ እና ባትሪው እንዲግል ያደርጋል።

እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ስልኩን ሊያቃጥለው እኛንም ለጉዳት ሊዳርግ ይችላል።

እናም ከእንደዚህ ዓይነት አደጋ ለመጠበቅ የመጀመሪያው ምክር የሞባይል ስልክን ባትሪ እንዲሞላ ኤሌክትሪክ ላይ ተሰክቶ የሚቀመጥበት ቦታ ከወትረው የተለየ ሙቀት የሚፈጥር ሊሆን አይገባም የሚለው ነው።

በጣም በሞቀ ወይም በጣም በቀዘቀዘ ስፍራ የስልክ ባትሪን ከመሙላት መቆጠብ እንደሚገባም ይመከራል።

በአጠቃላይ ግን ትክክለኛ እና በስልኩ አምራች ኩባንያ የሚታወቅን “ቻርጀር” መጠቀም ይገባል ተብሏል።

 

የአገር ጉዳይ:- በኢትዮጵያ የሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ያስከተለው ውጥረትና መጪው ጊዜ

0

 

“የአገር ጉዳይ” በሚል ርዕስ በራዲዮ መጽሔት እየተሰናዳ በሚቀርበው ልዩ ተከታታይ ፕሮግራም የተጀመረ ውይይት ነው።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚጻፉ፥ የሚታዩና የሚሰሙ ዜናዎችና ዘገባዎች የሚቀርቡባቸው የአራት መደበኛና የአካባቢ መገናኛ ብዙኃን መድረኮች አዘጋጆችና ባለቤቶች ናቸው።

የኢትዮ-ሚድያው ዋና አዘጋጅ አብረሃ በላይ፤ የኢሳት ራዲዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞች አዘጋጅና አቅራቢው ሲሳይ አጌና፥ የአዲስ አበባው Horn affairs የተሰኘ የኦንላይን መጽሔት አዘጋጅ ዳንኤል ብርሃኔ እና እንዲሁም በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ፤ በኢንተርኔትና በስልክ በሌሎች አካባቢዎችም ጭምር የሚሰማው “አዲስ ድምጽ” የተባለው የማሕበረሰብ ራዲዮ አዘጋጅና አቅራቢ አበበ በለው ናቸው።

የፖለቲካ ቀውስና በኃይል የታጀቡ እንቅስቃሴዎች እንደምን ባለ ላፊነት ይዘገባሉ? … አሳሳቢ ሁኔታዎች በሚታዩበት የዛሬዋ ኢትዮጵያስ የመገናኛ ብዙኃን ሚናና ኃላፊነት ምንድ ነው?