Home Blog Page 4

Ethiopia |ለጀርባ ህመም የሚዳርጉን የየእለት ተግባራት

0

የታችኛው ጀርባ ክፍል ህመም በአለም አቀፍ ደረጃ ለአካል ጉዳተኝነት የሚዳርግ ሲሆን፥ ለጊዜው የህመም ማስታገሻ መዳሀኒት ከመውሰድ ባለፈ ተገቢው የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ሌሎች ህክምናዎች እንደማይደረግላቸው አንድ ጥናት አመላክቷል።

ህሙማኑ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ የቀዶ ህክምና፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያደረጉና መርፌዎችን የወሰዱ ቢሆንም ከህመማቸው እንዳላገገሙ በጥናቱ ተረጋግጧል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የተደረገው ጥናት የአውስትራሊያ አገር አቀፍ ጤና፣ የጤና ምርምር ምከር ቤት እና የኒውዚላንድ “ማስኩሎ እስኬለተል” የጥናት ውጤት ተመሳሳይ እንደሆነ ዘገባው አስረድቷል።

በአለም አቀፍ ደረጃ በጀርባ ህመም ምክንያት ከ540 ሚሊየን ህዝብ በላይ ለአካል ጉዳተኝነት የተጋለጠ ሲሆን፥ ከፈረንጆቹ 1990 በኋላ ችግሩ 50 በመቶ እንዳደገ ታውቋል።

ባለፉት አመታት ለበሽታው ህክምና የሚጠይቀው ወጪም እየጨመረ እንደመጣም ተጠቁሟል።

ከእድሜ መግፋትና ከአልተፈለገ የሰውነት ክብደት ጋር ተዳምሮ ችግሩ የበለጠ እየተስፋፋ እንደሆነም ተመላከቷል።

ከዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ትክክለኛው የህክምና ዘዴ የሚታዘዝ እንደሆነ ቢታወቅም ለበሽተኞቹ የሚሰጠው ህክምና የህመም ማስታገሻ ከመስጠት የዘለለ አይደለም ተብሏል።

በአሜሪካ ሀገር ከ60 በመቶ በላይ የሆነው ህዝብ በታችኛው የጀርባ ክፍል ህመም የሚሰቃይ እንደሆነም ታይቷል።

በብሪታኒያ ከሊ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ተመራማሪ የሆኑት ናዲኔ ፎስተር ለኤን ቢ ሲ እንደተናገሩት፥ በበርካታ ሀገራት የጀርባ ህመም ላለባቸው በሽተኞች የህመም ማስታገሻዎች ይታዘዛሉ።

የህመም ማስታገሻ መድሀኒቶችን ከሚወስዱ ህሙማን መካክል ከግማሽ በላዩ የጀርባ ህሙማን ናቸው ተብሏል።

እነዚህ መድሀኒቶች በአካል እንቅስቃሴ ህክምና ፈንታ ለህሙማኑ ስለሚሰጡ ህሙማኑ ከበሽታው ጋር ለረጅም ጊዜ እንዲኖሩ ወይንም ለአካል ጉዳት እንዲዳረጉ አድርጓል።

ጃማ እንተርናል ሜዲስን በተባለ የጥናት ቡድን በፈረንጆቹ 2016 ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው፥ የህመም ማስታገሻ መዲሃኒቱን የወሰዱ 8 ሺህ ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ህመማቸውን ከማስታገስ ያለፈ መፍትሄ አላገኙም።

ከባድ የአካል እንቅስቃሴ የሚጠይቅ ስራ ላይ የተሰማሩ፣ ከፍተኛ የጤና እክል ያለባቸው፣ አጫሾችና ላልተፈለገ የሰውነት ክብደት የተጋለጡ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ለጀርባ ህመም የተጋለጡ ናቸው ተብሏል።

ለህሙማኑ የሚመጥን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የስነ ልቦነ ምክር አግልግሎት ማግኘት፣ መታሸትና ሌሎች ጎጂ ያልሆኑ ህክምናዎች ለውጥ የሚያመጡ እንደሆነ ጥናቱ ያስረዳል።

ጃማ እንተርናል ሜዲስን የተባለ የጥናት ቡደን በ2016 በወጣው ጥናት መሰረት ተከታታይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ትምህርት አደጋውን እስከ 45 በመቶ ያህል መቀነስ ያስችላል ተብሏል።

Ethiopia |10 ህይወታችንን ሊቀይሩልን የሚችሉ ልምዶቻችን

0

በአንድ ሳምንት ውስጥ ጥርት ያለ ቆዳን ለመጎናፀፍ የሚያስችሉ 5 ዘዴዎችን እንሆ።
1.አንድ ንፁህ ፎጣ ያዘጋጁ፣ ውሃ ያሙቁና ፎጣውን በመንከር ፊትዎን ለተወሰኑ ደቂቃዎች ይሸፍኑበት።ይህም በፎጣው ላይ ያለው ውሃ እና እንፋሎት በቆዳዎ ቀዳዳዎች ላይ ያለውን ቆሻሻ ለማፅዳት ይጠቅማል።ነገርግን ውሃው የፊትዎን ቆዳ እንዳይጎዳ ከሚፈለገው መጠን በላይ መፍላት የለበትም።

2.በመቀጠል እጅዎን አንቲባዮቲክ ሳሙናን በመጠቀም በሚገባ ያፅዱ ፤ ይህም በእጅዎ ላይ የሚገኙ ጀርሞችን ለማስወገድ ያግዛል፤ ፊትዎን በሚገባ ባለፀዱ እጆች ለማፅዳት መሞከር ከጥቅሙ ጉዳቱ ያይላልና ጥንቃቄ ያድርጉ።\ፎጣውን ከፊትዎ ላይ በማንሳት የፊት ማፅጃ ካለዎት እርሱን በመጠቀም ለብ ባለ ውሃ ይታጠቡ፥ አልያም ፀረባክቴሪያ ሳሙናዎችን መጠቀም ይችላሉ።

3.ሁለት ማንኪያ ስኳርና ሁለት ማንኪያ የሞቀ ውሃን በትንሽ ሳህን ያዋህዱና በደንብ ከተዋሃደ በኋላ ተጨማሪ አንድ ማንኪያ ስኳር ይጨምሩበት፣ መልሰው ስኳርና ውሃውን በደንብ ያዋህዱት።ዚያም እጅዎን በንፁህ ውሃ ካረጠቡ በኋላ የቀላቀሉትን የስኳርና ውሃ ውህድ ፊትዎን በደንብ ይቀቡት።ከተቀቡ በኋላ ጉንጭዎን፣ ግንባርዎን እና መላ ፊትዎን ክብ እየሰሩ ለአንድ ወይም ለሁለት ደቂቃ ይሹት፣ ከዚያም ለብ ባለ ውሃ ያለቅልቁት።

4.ፊትዎን ታጥበው ሲጨርሱ 10 ማንኪያ ሎሚ እጅዎ ላይ በመጭመቅ ፊትዎን ለ10 ሰከንድ ያህል ያዳርሱት፣ ይህም በፊትዎ ቀዳዳ ላይ የቀሩ ቆሻሻዎችን ሙልጭ አድርጎ ለማስወገድ ፍቱን ነው፣ ይህ የማቃጠል ስሜት ስለሚኖረው ለተወሰኑ ሰከንዶች መታገስ ይኖርብዎታል፤ ይህም የቶነር አገልግሎትን የሚተካ ይሆናል።

5.በመጨረሻም ቀዝቃዛ ውሃን በመጠቀም ፊትዎ ላይ በመርጨት እንደቀድሞው ክብ እየሰሩ ለተወሰኑ ሰከንዶች ይሹት ፤ይህ ሂደትም ፊትዎ ላይ የሚገኙ ባክቴሪያዎችንና ቆሻሻዎችን በማስወገድ ንፁህ ፣ ለስላሳ እና ጥርት ያለ ቆዳ እንዲኖርዎት ያደርጋል።ይህንን በየቀኑ ለአንድ ሳምንት በማድረግ ውጤቱን ማየት ይችላሉ።

ምንጭ፦FBC

በዋሺንግተን ዲሲ የሁለቱን ሲኖዶሶች ለማስታራቅ አዲስ አበባ ለመጡት አባቶች የተደረገ አቀባበል

0

ዛሬ ዛሬ አንድ ሕንፃ ጀምሮ ለማጠናቀቅ ዘለግ ያሉ ዓመታትን መጠበቅ ግድ የሆነ ይመስላል፡፡ መሰረታቸው ወጥቶ፣ ምሰሶዎች ቆመው፣ ግድግዳዎች ተገንብተው የማጠቃለያ ሥራቸው ተከናውኖ ለአገልግሎት እስኪበቁ አስር ዓመታት የሚያስቆጥሩ ረጃጅም ህንፃዎች የመኖራቸውን ያህል፤ በአጭር ጊዜ ሊጠናቀቁ የሚችሉ ግንባታዎችም በሰበብ አስባቡ እየዘገዩ ‹‹ቆሞ ቀር›› የሚለው ስያሜ ሲሰጣቸው ይስተዋላል፡፡
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በማህበራዊ ድረ ገፁ ያሰፈረው መረጃ ለዓመታት የ ‹‹እናቴ መቀነት አደናቀፈኝ›› በሚል ሰበብ ሳይጠናነቀቁ ለሚቆዩ ህንፃዎች ትምህርት የሚሰጥ ይመስላል፡፡ እንደ ዘገባው ኢጣልያ አገራችን ላይ ወረራ ፈጽማ ለአምስት ዓመታት በቆየችበት ዘመን አንድ ህንፃ በአንድ ቀን ተጠናቅቆ ለአገልግሎት በቅቷል፡፡
ህንፃው በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በቆራሄይ ዞን በሻይጎሽ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን፤ የወራሪው ሠራዊት የጦር መሪ ለነበረው ማርሻል ግራዚያኒ በፅህፈት ቤትነት እንዲያገለግል መሰራቱ ይነገራል፡፡ የኢጣሊያን ኃይል ኢትዮጵያን ለመውረር ባደረገው እንቅስቃሴ ከምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል የኢትዮጵያ ሶማሌ አካባቢን ተቆጣጥሮ በስፍራው በቆየበት ወቅት፤ ለአስተዳደር እንዲያመቸው የተለያዩ ግንባታዎችን እንዳከናወነ ይታወቃል። ከእነዚህ አንዱ የሆነው በአንድ ቀን የተጠናቀቀ ህንፃም ማርሻል ግራዚያኒ በፅህፈት ቤትነት ለተወሰነ ጊዜ እንደተገለገለበት ዛሬም በህይወት ያሉ የአካባቢው ሽማግሌዎች ያወሳሉ።
በወቅቱ በወራሪዊ የኢጣልያ መንግሥት በሻይጎሽ ወረዳ የተሰራው ህንፃ በ24 ሰዓት መጠናቀቁን የሚገልፁት የሀገር ሽማግሌዎቹ፤ በዚህ አጭር ጊዜ ተሠርቶ ሊጠናቀቅ የቻለው፤ በርካታ የሰው ኃይል እና ባለሞያዎች ስለተሳተፉበት ነው፡፡
ሕንፃው ሙሉ በሙሉ በድንጋይ እና ሲሚንቶ የተሠራ ከመሆኑም በተጨማሪ የበረንዳው ቋሚ ከትልቅ ወጥ ድንጋይ የተሰራ ነው፡፡ በግንባታው ምንም አይነት ብረት ጥቅም ላይ አልዋለም። አካባቢው ከክልሉ ዋና ከተማ ጅግጅጋ በ295 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ይህ ታሪካዊ ህንፃ በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት አገልግሎት የማይሠጥ ሲሆን፤ ካለው ታሪካዊ ዳራ እና ዕድሜ አንፃር የሚመለከ ተው አካል የቅርስ ጥበቃና ከለላ ቢያደርግለት የቱሪስት መዳረሻ መሆን ይችላል።

በረሃን በጭፍን

ከተለመደው የሰዎች ተግባር ወጣ ያሉ ድርጊቶችን የሚፈፅሙ በርካታ ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በሚፈፅሟቸው ድርጊቶች ምክንያትም የብዙዎችን ቀልብ መሳባቸው አይቀርም፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች አስደናቂና ግራ የሚያጋቡ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ አንዳንዴም ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው በመሆኑ አድናቆቱ ይጠፋና መሳቀቅ ይመጣል፡፡ ይህን አስደናቂና ለየት ያሉ ተግባራትን የሚፈፅሙ ሰዎችን ስራ የሚመዘግብ የዓለም ድንቃድንቅ መዘገብ ተዘጋጅቷል፡፡ እነዚህ ሰዎች በዓለም ድንቃድንቅ ባህረ መዝገብ ከመስፈራቸውም ባሻገር ዝናና ገንዘብን አትርፈዋል፤ ሀገራቸውንም አስጠርተዋል፡፡ አልፎ አልፎም ቢሆን በሀገራችንም ጥቂት የማይባሉ ሰዎች አስገራሚ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ ለመታዘብ ችለናል፡፡
እንዲህ አይነቱን ድንቅ ተግባር በአብዛኛው የሚፈፅሙት ሙሉ አካል ያላቸው ቢሆኑም አንዳንዴ አካላቸውን ያጡ ሰዎች ይህንኑ አስደናቂ ተግባር መልሰው ሲፈፀሙ መመልከት የበለጠ ያስገርማል፡፡ ትናንት ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው የመዝናኛና አስገራሚ ዜናዎች ድረ-ገፅ ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው አካል ጉዳተኞችም ድንቃድንቅ ተግባሮችን ለመፈፀም ልባቸው ብርቱ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡

እንደዘገባው ከሆነ አልበርት ቴሲየር የተሰኘው ማየት የተሳነው ፈረንሳዊው መምህር 140 ኪሎሜትር የሚረዝመውን ‹‹ሳላር ዴ ኡዩኒ›› የተሰኘውን የዓለማችን ትልቁ ጨዋማ የቦሊቪያ በርሃን ለማቋረጥ ዝግጅቱን አጠናቋል ይለናል፡፡ ቴሲየር የዓይን ብርሃኑን ሙሉ በሙሉ ከማጣቱ በፊት በሀገሩ ፈረንሳይ ማየት የተሳናቸው ተማሪዎችን ረጃጅም ቦታዎች እንዲጓዙ ሲያስተምር መቆየቱ ይህን ግዙፍ በርሃ ለማቋረጥ እንዳነሳሳው ተናግሯል፡፡ ለዓመታትም በርካታ ልምምድ ሲያደርግ እንደቆየ ገልፀዋል፡፡
አካለ ሙሉ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ አካል ጉዳተኞችም አስደናቂ ነገሮችን ማድረግ እንደሚችሉ ለዓለም ማሳየት እንደፈለገና የሚጓዝበትን ርቀት ደህንነት ከሚቆጣጠሩ የእርዳታ ቡድን ውጭ በባለድምፅ ጂ ፒ ኤስ በመታገዝ ጉዞውን ለብቻው እንደሚያከናውንም ነው መምህሩ ያስታወቀው፡፡
ቴሲየር የበረሃ ጉዞውን ለአንድ ሳምንት እንደሚያከናውን በዘገባው የተጠቀሰ ሲሆን፤ አደለም ለእርሱ ሙሉ አካል ላለው ሰው እጅግ ፈታኝ የሆነውን ጨዋማ በረሃ በእግሩ በማቋረጥ በቀን 20 ኪሎሜትር እንደሚሸፍን ተስፋ ተደርጓል፡፡ ምንም እንኳን ‹‹ሳላር ዴ ኡዩኒ›› የተሰኘው ይህ በርሃ ከባህር ጠለል በላይ በ3 ሺ 650 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ከዜሮ በታች 3 ዲግሪ ሴልሺየስና ከዜሮ በላይ እስከ 20 ዲግሪ ሴሊሸየስ የሚደርሰው ተለዋዋጭ የሙቀት መጠን ፈረንሳዊውን ልበ ብርሃን ይፈትነዋል ተብሎ ተገምቷል፡፡
ይኽው ማየት የተሳነው መምህር ጉዞው የበለጠ አስቸጋሪ እንዲሆን ሊካ ከተሰኘቸው መንደር አንስቶ ኮሊቻኒ ወደተሰኘቸው መንደር 140 ኪሎሜትር የሚዘልቀውን በረሃማ መንገድ መምረጡም አካል ጉዳተኛ ሆኖ ምን ያህል ከተፈጥሮ ጋር ለመጋፈጥ ዝግጁ መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲል ዘገባው ይገልፃል፡፡ መምህሩ ለጉዞ የሚጠቅሙትን የታሸጉ ውሃዎች፣ የመተኛ ፍራሽና ሌሎች ቁሳቁሶችን የሚይዝ ሲሆን የጤና እክል ቢያጋጥመው ከኋለው የሚከተለው የግል ሃኪምና የእርዳታ ቡድን እንዳለ ተገልፀዋል፡፡
_ ቴሲየር ጉዞውን ሲያደርግ እርሱ በእጁ በሚይዘው የሳተላይት ሬዲዮ አማካኝንት ርዳታ እንዲደርግለት ለቡድኑ እስካልጠየቀ ድረስ ራቅ ብለው ብቻ እንዲከተሉትና ምንም አይነት እርዳታ እንዳይሰጡት ተናግሯል፡፡ በእጁ በያዘው ጂ ፒኤስ አማካኘነትም እርዳታ ፈልጎ በሳተላይት ሬዲዮ ቢያሳውቃቸው እርሱ ያለበ ቦታ ላይ በቀላሉ በመገኘት እንደሚችሉም አሳውቋል፡፡
‹‹ሳላር ዴ ኡዩኒ›› የተሰኘው የቦሊቪያ በርሃ ዋነኛ የቱሪስት መዳረሻና 10 ሺ 552 ስኩዌር ኪሎሜት የሚሸፍነው ቦታ ከ50 እስከ 70 በመቶ የሚደርሰውን የዓለማችን ሊቲየም የተሰኘው ማእድን ክምችት መገኛም እንደሆነ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡ Read More

Sheger Shelf – ሐምሌ 13፣2010 በአንዷለም ተስፋዬ

0

 

ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ በነበረ የድሬዳዋ ከተማ መገናኛ ብዙኃን የጋዜጠኞች ቡድን አባላት ላይ በተፈጸመ ድብደባ የቡድኑ ሾፌር አቶ ሱሌይማን አህመድ ከቀናት የሕክምና ክትትል በኋላ ሕይወታቸው ማለፉ ታወቀ፡፡

ቅዳሜ ሐምሌ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የተደረገውን የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን አቀባበል ሥነ ሥርዓት ለመዘገብ የጋዜጠኞች ቡድን ወደ አዲስ አበባ እየመጣ በነበረበት ወቅት ሚኤሶ ከተማ ላይ ሲደርሱ በተሰባሰቡ ወጣቶች የቡድኑ አባላት ጥቃት ደርሶባቸው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ጥቃቱን የፈጸሙት ግለሰቦች፣ ‹‹እናንተ (በተለይም ኦሮሚኛ ቋንቋ የሚችሉትን ጋዜጠኞች) ገንዘብ ተከፍሏችሁ እየሰለላችሁ ነው፤›› በሚል ሁሉንም የቡድኑ አባላት የጅምላ ጥቃት እንዳደረሱባቸውም ይታወሳል፡፡

በድብደባው ጭንቅላታቸውና ጎናቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩት አቶ ሱሌይማን፣ በድሬዳዋ ድል ጮራ ሆስፒታልና በሐረር ከተማ ሕይወት ፋና ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ ቢደረግላቸውም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም፡፡

አቶ ሱሌይማን ወደ አዲስ አበባ፣ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለመላክ ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣ በቤተሰቦቻቸው ጥያቄ ወደ ሐረር መላካቸውን ለሪፖርተር የገለጹት የድሬዳዋ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ሐሰን ኢጌ፣ በመጨረሻ ሐሙስ ሐምሌ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. 5፡00 ሰዓት አካባቢ ሕይወታቸው ሊያርፍ ችሏል ብለዋል፡፡

ጋዜጠኞቹ ላይ በደረሰው ጥቃት እስካሁን የፖሊስ ምርመራ አለመጀመሩንም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የ37 ዓመቱ አቶ ሱሌይማን የሦስት ልጆች አባት ሲሆኑ፣ ከነፍሰጡር ሚስታቸው አራተኛ ልጅ ይጠብቁ ነበር፡፡ አቶ ሱሌይማን በኤጀንሲው ከአምስት ዓመታት በላይ አገልግለዋል፡፡

#EBCበአዲስ አበባ ቦሌ ኢምፔሪያል አካባቢ እየተገነባ ያለው የብሄራዊ ስታድየም የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ

0

በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለው የብሔራዊ ስታድየም የመጀመሪያ ምእራፍ ግንባታ ተገባደደ።

የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፥ በቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ ኩባንያ እና የኤም ኤች ኢንጅነሪንግ አማካሪ ድርጅትነት እየተከናወነ ያለው የስታድየሙ ግንባታ የመጀመሪያ ዙር በመገባደድ ላይ ይገኛል።

የብሄራዊ ስታድየሙ የፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ጥበቡ ጎርፉ የመጀመሪያ ዙር ግንባታ ለማከናወን 2 ነጥብ 4 ቢልየን ብር በጀት ተመድቦለት በመገንባት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በአሁኑ ሰዓትም የመጀመሪያ ምዕራፍ የስታድየሙ ግንባታ 82% መድረሱን ነው ያመለከቱት።

ሚኒስቴሩ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታን በእቅዱ መሰረት ሰኔ ወር ላይ እንደሚያጠናቅቅ ቀደም ብሎ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግሮ ነበር።

አሁን ላይ ሁለተኛውን ምእራፍ ግንባታ ለማካሄድም አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አቶ ጥበቡ ጎርፉ ተናግረዋል።

አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ እየተገነባ ያለው ብሄራዊ ስታዲየም የመጀመሪያ ዙር ግንባታ ከተጠናቀቀ በኋላ በሁለተኛው ምእራፍ ስታዲየሙን ጣራ የማልበስ፣ ወንበር መግጠም፣ የካሜራ እና ሌሎች ዲጂታል ስርዓቶችን የመግጠም ስራ ይከናወናል።

በሶስተኛው ምእራፍ ደግሞ ከስታዲየሙ ውጭ ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ መዋኛ ገንዳ እና ሌሎች መዝናኛ ስፍራዎች ግንባታ ይካሄዳል።

በአደይ አበባ ቅርፅ እየተገነባ ያለውና 60 ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው ይህ ስታዲየም ግንባታው የተጀመረው ታህሳስ 26 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት ነው። FBC

የጃፓኑ አይሲዙ ሞተርስ በኢትዮጵያ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሊያቋቁም ነው |Reporter

0

የጃፓኑ አይሱዙ ሞተርስ ኩባንያ በሽያጭ ወኪሉ በኩል ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ የኩባንያው ተሽከርካሪዎች የሚገጣጠሙበት ፋብሪካ በኢትዮጵያ ሊተከል ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

ኢቶቹ ኮርፖሬሽን የአይሱዙ ሞተርስ ኩባንያ የሽያጭ ዘርፍን የሚመራ አጋር ኩባንያ ሲሆን፣ ለበርካታ ዓመታትም በኢትዮጵያ የንግድ ወኪል ቅርንጫፉን በመክፈት የአይሱዙ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ በማስመጣት ለገበያ ከሚያቀርቡ የአገር ውስጥ ወኪሎች ጋር እየሠራ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ የኢቶቹ ኮርፖሬሽን የአውቶሞቢል ዘርፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ከሳቴ ብርሃን መንግሥቴ ለሪፖርተር እንዳብራሩት፣ የአይሱዙ መኪኖች የሚገጣጠሙበት ፋብሪካ በቅርቡ ሥራ ይጀምራል፡፡

መገጣጠሚያ ፋብሪካው በአገር ወኪሎች አማይነት የሚገነባ ሲሆን፣ የፋብሪካው አምሳያ (ፕሮቶታይፕ) ዲዛይን ለአይሱዙ ወኪሎች ተልኮ ሥልጠናም ጭምር ስለመሰጠቱ ከአቶ ከሳቴ ብርሃን ለመረዳት ተችሏል፡፡ የመገጣጠሚያው ሙሉ የዲዛይን ዝግጅት በዚህ ዓመት እንደሚጠናቀቅም ተጠቅሷል፡፡ ይሁንና የሚተከለው ፋብሪካ አቅምና በዓመት ምን ያህል ይገጣጥማል የሚሉት ጉዳዮች ላይ ወደፊት ምላሽ እንደሚሰጥባቸው ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ዓመታዊ ሽያጩ ከ3,000 በላይ የሚገመተው የአይሱዙ ሞተርስ፣ ከዚህ ውስጥ በመደበኛው መንገድ ማለትም በኢቶቹ በኩል ሽያጫቸው የሚከናወነው ተሽከርካሪዎች ቁጥር 800 ገደማ ይገመታል ያሉት አቶ ከሳቴ ብርሃን፣ በየጊዜው ዕድገት የታየበት የአይሱዙ መኪኖች አቅርቦት በኢትዮጵያ መመዝገቡን ገልጸዋል፡፡

ኩባንያው በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት እንደገበያው ፍላጎት መጠን ማቅረብ እንዳልቻ የጠቀሱት ኃላፊው፣ በኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ አጋሩ ከነበረው ከጄነራል ሞተርስ ኮርፖሬሽን በተጨማሪ ካኪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያን ጨምሮ ሌላ ሦስተኛ ወኪል ኩባንያም የአይሱዙ ተሽከርካሪዎችን በኢትዮጵያ ለማከፋፈል ስምምነት መፈጸማቸውን አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኤፍኤስአር እንዲሁም ኤንፒአር የተሰኙትን የአይሱዙ ሞዴል የጭነት መኪኖች ለኢትዮጵያ ገበያ እያቀረበ የሚገኘው ኩባንያ፣ ወደፊት ኤፍቪአር 23 እንዲሁም ኤፍቪአር 33 የተባሉ አዳዲስ ሞዴሎችን ለማቅረብ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ እነዚህ የሥራ ተሽከርካሪዎች በተለይ የታሸገ ውኃ ለሚያመርቱና ለሌሎችም ተመራጭ ስለመሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪም የአይሱዙ ምርት የሆኑ አውቶቡሶችን ለኢትዮጵያ ገበያ ለማስተዋወቅ ፍላጎት ስለመኖሩም ተጠቅሷል፡፡

ላለፉት 50 ዓመታት በኢትዮጵያ የአይሱዙ ምርቶችን ሲያቀርብ የቆየው ኢቶቹ ኮርፖሬሽን፣ ከኢትዮጵያም ሰሊጥና ቡና በመላክ እየተሳተፈ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በተያያዘ ዜና ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀናት ውስጥ በተካሄደው የጃፓንና የኢትዮጵያ ኩባንያዎች የንግድ ግንኙነት ፎረም፣ አይሱዙን ጨምሮ አምስት የጃፓን ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ ግብርና ተጠቃሚ ያሏቸውን ምርቶች አስተዋውቀው ነበር፡፡ ቶፕኮን የሰኘው ኩባንያ ያቀረባቸው ቴክሎጂዎች በግብርናው መስክ ‹‹ፕሪሲሽን አግሪካልቸር›› እየተባሉ የሚታወቁና የዘመኑ ቴክኖሎጂ ዕድገት የደረሰባቸውን ደረጃዎች ያካተቱ ውጤቶች ነበሩ፡፡

‹‹ክሮፕስፔክ›› የተሰኘው የኩባንያው ቴክኖሎጂ፣ የማዳበሪያ አጠቃቀምን፣ የፀረ ተባይና የፀረ አረም አመጣጠንን፣ የውኃ ልኬትንና ሌሎችም ተጓዳኝ ግብዓቶችን በማመጣጠን ለሰብል ምርት እርሻ የሚያግዝ ቴክኖሎጂ ስለመሆኑ ተብራርቷል፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ በትራክተርና በሌሎችም የእርሻ መሣሪዎች ላይ ተገጥሞ የሚሠራ ነው፡፡ ማሩቤኒ የተሰኘው ሌላኛው የጃፓን ኩባንያም በኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ቆይታ ያለውና በንግድ ዘርፍ በተለይ በቡና ላኪነት እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን፣ በጃፓን ከማዳበሪያ አምራችነት ጀምሮ በልዩ ልዩ የኬሚካልና የፕላስቲክ አምራችነት የገዘፈ ስም አለው፡፡ ለአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ የተሻለ ጥቅም ሊሰጥ የሚችል ግሪን ሐውስ የፕላስቲክ ሼድ እንደሚያመርትና ይኼንኑ ምርትም ለኢትዮጵያ ገበያ ለማቅረብ እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡

ሌሎችም ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን ያስተዋወቁበትንና ከኢትዮጵያ ኩባንያዎች ጋር ሐሳብ የተለዋወጡበትን መድረክ ያዘጋጀው ጃፓን ኤክስተርናል ትሬድ ኦርጋኒዜሽን (ጄትሮ) የተሰኘው መንግሥታዊ ተቋም ነው፡፡ ይህ ተቋም በኢትዮጵያ ቢሮውን የከፈተው በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጥያቄ ሲሆን፣ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ የአቶ ኃይለ ማርያምን ጥያቄ በመቀበል ተቋሙ ቅርንጫፉን በኢትዮጵያ እንዲከፍት መፍቀዳቸውን ሪፖርተር መዘገቡ ይታወሳል፡፡

የጄትሮ ኢትዮጵያ ኃላፊ ታካኦ ሴኪ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኩባንያው በኢትዮጵያና በጃፓን ኩባንያዎችና ኢንቨስተሮች መካከል የኢንቨስትመንትና የንግድ መረጃዎችን ያሠራጫል፡፡ ከዚህ ባሻገርም የጃፓን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያዙ ድጋፎችን በመስጠት ያግዛል፡፡ በዚህ ሒደት ቶሞኒየስ የተሰኘው የጃፓን ኩባንያ በቦሌ ለሚ ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የራሱን ፓርክ ለመሥራት ከ30 ሔክታር በላይ መሬት መጠየቁንና ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ባለፈው ዓመት ስምምነት መፈረሙም ይታወሳል፡፡ ይህም ሆኖ የጃፓን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ያላቸው ተነሳሽነት ዝቅተኛ ስለመሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ለዚህ ዋናው ምክንያትም ባለሀብቶቹ ስለኢትዮጵያ ያላቸው ግንዛቤና መረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ እንደሆነ ይነገራል፡፡

መፍትሔ የሚሻው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ |Fana Television

0

ከቅርብ ወራት ወዲህ የኤሌክትሪክ ኃይል በድንገት ጠፍቶ ለቀናት በመቆየቱና የኃይል መቆራረጡ በመደጋገሙ መማረራቸውን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚጠፋና እንደሚቆራረጥ ያመነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ምክንያቶቹ ሁለት መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ነባሩን ኔትወርክ ወይም የኤሌክትሪክ መስመር ወደ አዲስ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር የመቀየር ሥራ እየተካሄደ ስለሆነ፣ በወቅቱ ከባድ ዝናብና ንፋስ ሳቢያ ያረጁ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች በመውደቃቸው መሆኑን አስረድቷል፡፡

በኤሌክትሪክ ኃይል መጥፋትና መቆራረጥ መማረራቸውን የገለጹት የየካ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች አቶ ትዕግሥቱ በቀለ፣ አቶ ተመስገን ጉርሜሳና ወ/ሮ ፀዳለ ገብራይ፣ በድንገት ተቋርጦ ከሁለት እስከ አምስት ቀናት ስለሚቆይ በፍሪጅ የሚቀመጡ መድኃኒቶች፣ የሕፃናት ምግቦችና የተለያዩ ነገሮች እንደሚበላሹ አስረድተዋል፡፡ በተለይ በጋራ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ውስጥ የሚኖሩ፣ ማንኛውንም ነገር የሚሠሩት በኤሌክትሪክ ኃይል በመሆኑ፣ ለቀናት ተቋርጦ ሲቆይ ከፍተኛ ችግር እየገጠማቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አቶ ወንድምየ ስለሺ የተባሉ የሆቴል ባለቤትም እንደገለጹት፣ በፍሪጅ የሚቀመጡና የሚበስሉ ምግቦችን ለደንበኞቻቸው እንደ ልብ ባለማቅረባቸው ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ በድንገት የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል በድንገት ሲለቀቅ ብዙ ንብረቶችን እያቃጠለባቸው መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ፀዳለ፣ የሚመለከተው ተቋም ቢያንስ ኃይል ሲለቅ እንኳን ተመጣጣኝ ቢያደርገው ወይም ለሕዝቡ በሚዲያ ቢያሳውቅ ከሁለቱ ጉዳቶች በአንዱ ሊድኑ ይችሉ እንደነበር አስታውቀዋል፡፡

በሁሉም ክፍላተ ከተሞች ተመሳሳይ ችግር መኖሩን ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡ በተለይ የሆቴል፣ የዳቦ ቤቶች፣ የአነስተኛ ማምረቻዎችና ሌሎችም በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ ነዋሪዎች ተመሳሳይ ችግር እየገጠማቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የሚመለከተው የመንግሥት አካልና ተቋም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ነዋሪዎች ያነሱትን ቅሬታ በሚመለከት ምላሽ እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው በቅርቡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የተመደቡት አቶ ሽፈራው ተሊላ፣ ነዋሪዎቹ ያነሱት ጥያቄ ትክክል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደገለጹት፣ ችግሩ እየተፈጠረ ያለው በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ አንደኛው ያረጁ የኤሌክትሪክ መስመሮች (ኔትወርክ) እየተቀየሩ በመሆኑ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ንፋስና ዝናብ ያረጁ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎችን እንዲወድቁ በማድረጉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሁሉንም ችግሮች ለመፍታት ተቋሙ ሌት ከቀን እየሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ ኔትወርኩን ለማሳደግና ችግሩን እስከ መጨረሻው ለመፍታትም ፓወር ቻይና የተባለው ኩባንያ የመስመር ዝርጋታውን በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን አቶ ሽፈራው ገልጸዋል፡፡ ኩባንያው ፕሮጀክቱን አጠናቆ የሚያስረክብበት ጊዜ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ እስካሁን አለማጠናቀቁንና ይኼንንም በሚመለከት ተቋሙ በቅርቡ ገምግሞ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡ Read More

ተዘግቶ ለ20 ዓመታት በቆየው የኤርትራ ኤምባሲ ውስጥ ምን ተገኘ?BBC Amharic

0

በ1990 የድንበር ጦርነቱ ሲቀሰቀስ አዲስ አበባ ውስጥ ለሁለት አስርታት ተዘግቶ ከቆየው የኤርትራ ኤምባሲ በሮች በኤርትራ ባለስልጣናት ሲከፈት ክፍሎች ውስጥ በአቧራ የተሸፈኑ መኪኖች፣ የቤት ውስጥ እቃዎች እና የተለያዩ መጠጦች ባሉበት ተገኝተዋል።

ጦርነቱ በ1992 ቢያበቃም ግንኙነታቸው ሻክሮ እስካሁን ድረስ ቆይቶ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ኤርትራ መጓዛቸውን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ነው ኤምባሲው መልሶ የተከፈተው።

እነዚህ ፎቶግራፎች የኤርትራ ኤምባሲ ዛሬ ሲከፈት በቢቢሲ የተነሱ ናቸው።

Andand negeroch – በኢትዮጵያ የሚገኙ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አቋምና አማራጭ

0

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ከፍ ባለ መድረክ ላይ አሰሙት የተባለው ንግግር ብዙዎችን አስደንቋል። ንግግራቸው አሁን አሜሪካ ውስጥ ሥልጣን ይዞ ያለውን መንግሥት በሾርኔ ወጋ ለማድረግ የተጠቀሙበት ነው እየተባለ ይገኛል።

15 ሺህ ያህል ሰው በታደመበትና የደቡብ አፍሪቃውን የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላን ለመዘከር በተዘጋጀው መድረክ ላይ ንግግር ያሰሙት ኦባማ የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መነጋገሪያም ሆነው ነበር።

እስቲ ኦባማ ካሰሙት ንግግር መካከል አምስት አበይት ነጥቦች መርጠን ወደእናንተ እናድርስ።

፩. እውነት የተቀደሰች ናት
«በእውነታ ልታምኑ ይገባል» አሉ ኦባማ፤ «እውነታውን መሠረት ያላደረገ ነገር ለትብብር አይገፋፋምና።»

«እኔ ይሄ አትሮነስ ነው ስል፤ ‘አይ አቶ ኦባማ ተሳስተዋል እንዴት ዝሆኑን አትሮነስ ይሉታል’ ካላችሁኝ ነገር ተበላሸ ማለት ነው።»

በተመሳሳይ ርዕስ ላይ የቆዩት ኦባማ በአየር ንብረት ለውጥ የማይስማሙ ሰዎች ጋር መስማማት ሊከብዳቸው እንደሚችል ጠቁመዋል።

ተቀማጩ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ሃገራቸውን ማግለላቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

፪. ስደተኞች ጥንካሬ ናቸው
ኦባማ ብዙ ስብጥር ያለው ማሕበረሰብ አቅሙ የዳበረና ስጦታ የታከለበት ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

«እስቲ የፈረንሳይ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድንን ተመለክቱት» ሲሉ ጎዜ የአዳራሹ ጣራ ጭብጨባ ሊሰጠነቅ ሆነ።

«የቡድኑ አባላት ስትመለከቷቸው ሁሉም ጎል (ምዕራብ አውሮጳዊ) አይመስሉም፤ ግን ፈረንሳውያን ናቸው።»

«ሆኖም አሁን ባለንበት ጊዜ እንኳን ዘርን መሠረት ያደረጉ ማግለሎች በሃገረ አሜሪካም ይሁን በደቡብ አፍሪቃ በሰፊው ይንፀባረቃሉ።»

፫. ቱጃሮች ከሌላው ተነጥለው የሚኖሩ ናቸው
ኦባማ «ዓለማችን ‘ልጥጥ’ ሃብታሞች ከደሃው ማሕበረሰብ ተነጥለው የተለየ ኑሮ የሚኖሩባት ናት» ሲሉም ተደምጠዋል።

«ቱጃሮቹ ሲያስቡ የሚውሉት የሚያድሩት ስለሚያስተዳድሩት ድርጅት እንጂ ስሌላ ነገር አይደለም፤ ከሚኖሩባት ሃገር ጋር ያላቸውም ቁርኝት እጅግ የላላ ነው። ለእነሱ አንድ ድርጅትን መዝጋት ማለት ከትርፍና ኪሳራ አንፃር የሚታእ አንጂ ሌላው ላይ ከሚኖረው ተፅዕኖ አኳያ አይደለም።»

፬. ድል ለዲሞክራሲ
«ፍራቻን፣ ቂም በቀልንና ማስወገድን እንደ ፖለቲካ መሣሪያ የሚጠቀሙ ፖለተከኞች አሁን ላይ ቁጥራቸው እጅግ እየላቀ መጥቷል» ሲሉ ኦባማ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል።

«ዴሞክራሲ ልሙጥሙጥ ነው» ያሉት ኦባማ «ሃሰት የተመላ ቃል የሚገቡ ፖለቲከኞች ደግሞ አምባገነኖች ናቸው» በማት ወርፈዋል።

«ጊዜው ከኛ በላይ ወዳሉት የምንጋጥጥበት ሳይሆን ወደታች ዝቅ ብለን የምንሠራበት ነው፤ ዲሞክራሲ ያለው እዚያ ነውና።»

«ከሕዝባዊ ፖለቲከኞች ተጠንቀቁ» ሲሉ ያስጠነቀቁት ኦባማ «ነፃ ዴሞክራሲ ለሰብዓዊው ፍጡር ቅድሚያ የሚሰጥ ነው» በማለት አክለዋል።

«አኔ በኔልሰን ማንዴላ ርዕይ አምናለሁ፤ በመሰል ሰዎች የሚመራ ዓለም የተሻለ እንደሆነም አስባለሁ።»

፭. ሁሌም ተስፋ እንሰንቅ
«በእምነታችሁ ፅኑ፤ ሁሌም ወደፊት ሂዱ፤ ማነፃችሁን አታቁሙ፤ ድምፃችሁን አሰሙ። ሁሉም ትውልድ ይህችን ዓለም የተሻለች የማድረግ ዕድል አለው» ኦባማ ንግግራቸውን ወደ መቋጨቱ ሲጠጉ የተናገሩት ነው።

በጭብጨባና ፉጨት አጅቦ ሲያዳምጣቸው ለነበረው ወጣት ለሚበዛው ታዳሚ «እንነሳ» የሚል ድምፅ አሰምተዋል።

«አንድ መሪ ብቻ አይበቃንም፤ እጅጉን የሚያስፈልገን የጋራ ትብብር ነው።»

«ማንዴላ ‘ወጣቶች የጭቆና ማማን ደርምሰው የነፃነት አርማን የመስቀል ኃይል አላቸው’ ብለውናል፤ ይህንን ተግባራዊ የማድረጊያው ጊዜ አሁን ነው።»

ኦባማ የማንዴላ 100ኛ ዓመት ክብረ በዓልን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሥነ-ሥርዓት ላይ ይህንን ንግግር ያሰሙት።

ኦባማም ሆነ ማንዴላ በሃገራቸው የመጀመሪያዎቹ ጥቁር ፕሬዝደንቶች ናቸው። BBC Amharic

ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች |BBC Amharic

0

የውጭ ምንዛሬ ችግር ያጋጠማት ኢትዮጵያ ለአንድ ዓመት የሚያስፈልጋትን ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ለማግኘት ጥያቄ ማቅረቧን የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋን በመጥቀስ ሮይተርስ ዘገበ። “ነዳጅ ለማስገባት እየተነጋገርን ነው። ዝርዝሮቹ ገና አላለቁም። በፕሮግራም የተያዘና መደበኛ የነዳጅ አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል ነው” ማለታቸውን ዘገባው ያመለክታል።

በዶላር እጥረትና የመንገድ መሠረተ-ልማት ችግር ምክንያት እስከ 1 ነጥብ 6 ሚልዮን ቶን የሚገመት ንብረት በጂቡቱ ወደብ ተከማችቶ እንደሚገኝ ዘገባው ጨምሮ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር ውስጥ እንደምትገኝ በመግለጽ ሰሞኑን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የውጭ ሃገር ገንዘብ በእጃቸው የሚገኝ ዜጎች በባንኮች እንዲመነዝሩ ጥሪ ማቅረባቸው ኣስታውሷል።

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ 100 ቀናት ውስጥ ዶላር በጥቁር ገበያ ለምን ቀነሰ?

ዶላርና ብር ለዘመናት እንደተኳረፉ አሉ። ከሰሞኑ ያሳዩት መቀራረብ ግን ማንም የጠበቀው አልነበረም። ከሳምንት በፊት አንድ ዶላር በ36 ብር ይመነዘር ነበር፤ በጥቁር ገበያ። በዚህ ሳምንት አንድ ዶላር ተመኑ ወደ 31 ብር ወርዷል። በሰባት ቀናት የአምስት ብር ቅናሽ እጅግም ያልተለደመ ነው። ይህ ለምን ሆነ?

የውጭ ምንዛሬ ወትሮም የአንድን አገር ኢኮኖሚያዊ ጤና የሚያሳብቅ የትኩሳት መለኪያ ብልቃጥ ‘ቴርሞሜትር’ ነው። በተለይም ጥቁር ገበያ ከመንግሥት ቁጥጥር ያፈነገጠ፣ በገበያ ፍላጎት የሚመራ በመሆኑ የተሻለውና የሚታመነው የትኩሳት መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። ታዲያ የታመመው ምጣኔ ሐብታችን ትኩሳቱ እየበረደለት ይሆን?

ቢቢሲ በዚህ ድንገተኛ የጥቁር ገበያ ዶላር ተመን ማሽቆልቆል ዙርያ የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎችን አወያይቷል።

የዋጋ ከፍና ዝቅ መሬት ላይ ባለ ነገር ብቻ አይከሰትም። በተለይም የምንዛሬ ምጣኔ አንዳች ኮሽታ በተሰማ ቁጥር ሊናጥ የሚችል ድንጉጥ ገበያ ነው። ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ከዚሁ ጋር የሚያያዝ ምሳሌን ያነሳሉ።

“የአሜሪካ “ትሬዠሪው” በሚሰበሰብበት ጊዜ ማርኬቱ ገና ስብሰባው ሊካሄድ ነው ሲባል ነው መናወጥ የሚጀምረው”

በተመሳሳይ ከሰሞኑ በድኀረ ዐብይ የተሰሙ፣ የታዩ፣ የተገመቱና የተከሰቱ ዐበይት ክንውኖች የጥቁር ገበያውን ዶላር አደብ ሳያስገዙት አልቀሩም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የውጭ ምንዛሬ ጥሪ ለዳያስፖራው በይፋ ማቅረባቸው፣ በሶማሌ ክልል ነዳጅ የማውጣቱ ዜና፣ በአገሪቱ አንጻራዊ ሰላም እየሰፈነ መምጣቱ ከሚጠቀሱት ክስተቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

አፍሪካ በየዓመቱ ከምታገኘው ሁሉን አቀፍ እርዳታ 10 እጥፍ የሚበልጠው በኀቡእ የሚሸሽ ነው። ኢትዮጵያም የዚሁ አካል ናት። ቢሊየን ዶላሮች በሕገ ወጥ መንገድ በየዓመቱ ያፈተልካሉ።

በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረው አለመረጋጋት ብዙ ዜጎች ገንዘባቸውን በዶላር ቀይረው ወደ ውጭ ያሸሹ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በመንግሥት ሹሞች የሚፈጸም ሌብነትና ዝርፍያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘ሌቦች’ የሚሏቸውን ጨምሮ ጥቁር ገበያውን ሲያንሩት እንደነበር ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ይገምታሉ።

እነዚህ ዘራፊዎች የአገሬውን ገንዘብ ወደ ባንክ ወስደው ለማስቀመጥ አይችሉም። ጥያቄ ስለሚፈጥርባቸው። ስለዚህ የዘረፉትን ወደ ዶላር በመቀየር ማሸሽን ይመርጣሉ።

አገር በስፋት ስትዘረፍና ብራቸውን ወደ ዶላር መቀየር የሚፈልጉ ዘራፊዎች ቁጥር ሲጨምር የጥቁር ገበያ የምንዛሬ ዋጋ በዚያው መጠን ይመነደጋል።

በብር የሚከፈላቸው የውጭ ተቋራጮች – ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ለጥቁር ገበያ ዋጋ መናር ሌላ ምክንያት ይመስለኛል የሚሉት አገር ውስጥ ትልልቅ ግንባታ ለማካሄድ የሚጫረቱ የቻይና ኩባንያዎችን ነው።

እነዚህ ኩባንያዎች ጨረታ የሚገቡት በብር እንዲከፈላቸው በመዋዋል ነው። ነገር ግን በቢሊዮን ብር ከተከፈላቸው በኋላ ብሩን ወደ ዶላር ቀይረው ከአገር ያስወጡታል። ይህን ግብይት የሚያደርጉት ደግሞ በጥቁሩ የዶላር ጉሊት ነው።

ዶክተር ቆስጠንጢኖስ እንደምሳሌ የሚያነሱት ሰሞኑን ድንበር አካባቢ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዶላር በትራክ ተጭኖ ሊወጣ ሲል መያዙን ነው። ይህ ዓይነቱ የድንበር ቁጥጥር የጥቁር ገበያ የዶላር ግዢ ፍላጎቱን የቀነሰ ይመስለኛል ይላሉ። ምክንያቱም ኩባንያዎቹ የሕግ ተጠያቂነት ስለሚያስፈራቸው።

የቀድሞው የንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ክቡር ገና ግን በዶክተር ቆስጠንጢኖስ ሃሳብ የሚስማሙት በግማሹ ነው።

“የጠረፍ ቁጥጥር ሲኖር (የዶላር) ገበያውን ቀነስ አያደርገውም አልልም። ተጽእኖ ይኖረዋል። ሆኖም የጠረፍ መዘጋት በዚህ ዓይነት ዶላሩን በአንድ ጊዜ ዝቅ ያደርገዋል ብዬ አላስብም…።”

ከዚያ ይልቅ ይላሉ አቶ ክቡር፣ የአገሪቱ እጣ ፈንታ አሳስቦት፣ ግሽበት አሳስቦት፣ ገንዘቤ ከሚሟሟ ብሎ ብሩን በዶላር የሚያስቀምጠው ሰው ቁጥር በሂደት እየቀነሰ መምጣቱ የዶላሩን የጥቁር ገበያ ተመን እንዲወርድ አንድ ምክንያት ሆኗል።

“ፖለቲካ ላይ ተስፋ ሲታይ የብር ፈላጊ ይጨምራል።”

ለአቶ ክቡር ከሁሉም በላይ ሰሞነኛው ፖለቲካ ለዶላሩ መውረድ ሚና ተጫውቷል። “…የፖለቲካ ችግር እንደሚቀንስ የሚያሳዩ ምልክቶችን አየ፤ የዶላሩ ግዢ ሩጫውን ቀነሰ” ካሉ በኋላ በእንደዚህ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ትርፍ ከፍሎ ዶላር የመግዛት ፍላጎት እየጠፋ እንደሚመጣ ያትታሉ።

ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በበኩላቸው የውጭ ኩባንያዎች አገር ውስጥ የሚያገኙትን ብር በጥቁር ገበያ ስለሚመነዝሩት የዶላር ፍላጎት በጥቁር ገበያ ንሮ እንዲቆይ እንዳደረገው አይጠራጠሩም።

“…በቻይና ኩባንያዎች ለምሳሌ ትልልቅ ሕንጻዎች እየተሠሩ ነው። እነዚህ ኩባንያዎች በብር ነው ጨረታ የሚገቡት። በብር ጨረታ ሲገቡ በብር ነው የሚከፈላቸው፥ በዶላር አይደለም። ስለዚህ የሚከፈላቸውን ብር የማውጫ ዘዴ ይፈልጋሉ። ይህን ፍላጎታቸውን የሚያሟላላቸው ጥቁር ገበያው ነው። በጥቁር ገበያው ብራቸውን ወደ ዶላር ቀይረው በትራክ ወደ ጅቡቲ ወስደው ጅቡቲ ባንክ ተቀምጦ ሕጋዊ ገንዘብ ያደርጉታል።”

“ዶላሩን ይዤ ብቆይ ይሻላል በሚል ፍላጎት አድጎ ነበር” አቶ ክቡር ገና
ወደ ጥቁር ገበያ የሚተመው ደንበኛ መልከ ብዙ ነው። ለስብሰባ፣ ለትምህርት፣ ለሽርሽርና ለሕክምና ወደ ውጭ የሚሄድ ሰዎች ባንኮቻቸው ዶላር ሊያቀርቡላቸው ስለማይችሉ ወደ ጥቁር ገበያ ያቀናሉ።

በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ያገኙ ሹመኞችም ወደ ጥቁር ገበያ ይሄዳሉ። የግል ባንኮቻቸው እጅ አልፈታ ያላቸው አስመጪ ነጋዴዎች ወደ ጥቁር ገበያ ይሄዳሉ። ይሄ ሁሉ የጥቁር ገበያው ደንበኛ ነው።

ሌሎች ዜጎች ደግሞ ብራቸውን በዶላር በማኖር የብር ግሽበትን ለመከላከል ይሞክራሉ። ይህ ሁኔታ ዶላር በጥቁር ገበያ ያለውን ዋጋ ከፍ ሳያደርገው አልቀረም።

የጥቁር ገበያው ደንበኛ እንዲህ መብዛት ደግሞ በተዘዋዋሪ የዶላሩን ተፈላጊነት ያንረዋል።

አቶ ክቡር እንደሚሉት ኢ-መደበኛው የዶላር ገበያ በፖሊሲ ሳይሆን በገበያ ፍላጎት የሚመራ ነው። ስለዚህ ፍላጎት ሲጨምር ዋጋው ይጨምራል።

ታዲያ አሁን የዶላር ፍላጎት ቀንሶ ነው ጥቁር የዶላር ተመን የቀነሰው? ሊያውም ፋብሪካዎች በምንዛሬ እጦት በሚዘገቡት ወቅት?

አቶ ክቡር ገናም ይሁኑ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ይህንን ጥያቄ በቀጥታ አይመልሱም።

አቶ ክቡር መደበኛው የዶላር ትመና ምጣኔ ሃብቱን የሚመሩት ተቋማት (ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ) በአንድም ሆነ በሌላ ዘዴ የገንዘብ ልውውጡን መጠን፣ ፍጥነትና ሁኔታ እንደሚወስኑ ካብራሩ በኋላ የኢ-መደበኛው የገበያ ባህርያት በአጭሩ ያወሱና አሁን ዶላር በጥቁር ገበያ ለምን ቀነሰ ለሚለው አንኳር ጥያቄ የሚመስላቸውን ያስቀምጣሉ።

አንዱ ወደ ታክስ ሥርዓት ውስጥ ያልገቡ ኩባንያዎች ወደ ጥቁር ገበያ መሄድ ማቆማቸው ነው።

“ወትሮም በመደበኛ ግብይት የቆዩ፣ የታክስ ሥርዓት ውስጥ የቆዩ ኩባንያዎች ወደ ኢ-መደበኛ የዶላር ገበያ አይሄዱም። ወደ ኢ-መደበኛው የሚሄዱት አዳዲሶች ናቸው። በተለያየ ምክንያት።” ካሉ በኋላ “መጪውን ጊዜ በማስላት ዶላር ገበያው ውስጥ ያልነበሩ ሰዎች ገበያ ውስጥ ገቡ። እነሱ የፈሩት ፖለቲካዊ ሁኔታ እየተቀየረ ሲመጣ ከገበያው ወጡ፤ ይህ የጥቁር ገበያውን አረጋጋው ” ሲሉ ግምታቸውን ያስረዳሉ፣ አቶ ክቡር።

ከጥቂት ዓመታት በፊት አገሪቱ አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ እንደነበረች የሚያወሱት ሁለቱም የምጣኔ ሐብት ባለሞያዎች ይህንንም ተከትሎ ነገሮች እስኪጠሩ ድረስ ገንዘቡን በዶላር ማስቀመጥ፣ ወይም ማሸሽ፣ ወይም ዶላሩን ይዤ ብቆይ ይሻላል የሚል ፍላጎት አድጎ እንደነበር ያስታውሳሉ።

ይህ ሁኔታ በአንጻራዊ መልክ እየተለወጠ መምጣቱ ደግሞ የጥቁር ገበያን የዶላር ፍላጎት አረጋግቶታል።

የዐብይ አሕመድ ያለፉት ወራት እንቅስቃሴዎች በዶላር መቀነስ ያለውን ሚና የተጠየቁት አቶ ክቡር ገና በበኩላቸው፣

“በንግግርም ይሁን ‘በጀስቸር’ ዜጎች ያ የፖለቲካ ፍርሃት ሲቀንስላቸው፣ የፖለቲካው ውጥረት ተንፈስ ሲል የምንዛሬ ሩጫው ይገታል። ይህ ብዙውን ጊዜ ከተስፋ ጋር የሚሄድ ነገር ነው። አገር ሲረጋጋ የብር ፈላጊው እየጨመረ፣ በኢ-መደበኛ መንገድ የዶላር ፍላጎቱ እየረገበ ይሄዳል። ያንን ዶላር በብዙ ትርፍ ገዝቶ የማስቀመጥ ፍላጎቱ እየቀነሰ ሲመጣ ደግሞ የምንዛሬ መጠኑ ወደ መደበኛው ተመን እየተጠጋ ይመጣል።” ይላሉ።

ዶላር በቀጣይ ይቀንሳል ወይስ ይጨምራል?
የውጭ ንግድ ሲፋፋም፣ የአገር ውስጥ ምጣኔ ሐብት ጤና ሲጠበቅ፣ ኢኮኖሚው ለገበያ ክፍት ሲሆን፣ አግባብ ያላቸው የ”ሞኒቴሪ”ና የ”ፊስካል” ፖሊሲ ሲተገበር፣ የፋይናንስ አስተዳደሩ ሲዘምን ጥቁር ገበያ እየቀጨጨ በመጨረሻም አስፈላጊ ወደ ማይሆንበት ደረጃ ይደርሳል።

ይህ ዓለማቀፋዊ የምጣኔ ሐብት ሐተታ ነው። ይህ ሁኔታ ግን እንደየ አገሩ መልክና አስተዳደር ገጽታው ይለያያል።

ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ይህ ችግር የሚፈታው ገበያን በማፍታታት ነው ብለው በጽኑ ያምናሉ። “አሁን ያሉት የአገር ውስጥ ባንኮች ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ለማምጣት የሚያስቸል አቅሙም ጉልበቱም የላቸውም።”

ዶላር አሁንም ቢሆን ከእርዳታ፣ ከብድር፣ ከዳያስፖራና ከውጭ ንግድ ምንጮች ነው የሚገኘው። “የውጭ ባንኮች ቢገቡ ግን የራሳቸውን ካፒታል ይዘው ስለሚመጡ የምንዛሬ መንበሽበሽ ሊያመጡ ይቻላቸዋል” ይላሉ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ። ከዚሁ ጋር አብሮ የፋይናንስ አስተዳደሩ እንዲታሰብበት ይፈልጋሉ።

ዶክተር ቆስጠንጢኖስ አገሪቱ በሯን እንድትከፋፍት በሚያሳስቡበት መጠን ወጪዎቿን እንድትቀንስ ይወተውታሉ።

ጥቁር ገበያ የሚደራው ከመንግሥት የተዘረፈ ገንዘብ ከአገር ለማሸሽ ሲሞከር ነው። አሁን መንግሥት የራሱን ወጪ እየቀነሰ ሲሄድና ኢኮኖሚውን ክፍት ሲያደርገው ሁኔታዎች እንደሚለወጡ ያስባሉ።

“በፓርቲ የተያዙ ድርጅቶች አሉ፥ በመንግስት የተያዙ አሉ፥ እነዚህ ሁሉ ኢኮኖሚውን ሲያምሱት ምስቅልቅሉ የወጣ የፋይናንስ ሥርዓት ነው የተፈጠረው። መሠረታዊው መልስ የሚሆነው የፋይናንስ ሥርዓቱን ማስተካከል ነው።” ይላሉ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ።

እንደ ስኳር ፋብሪካና ማዳበሪያ ፋብሪካ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ያባከኑት ገንዘብ እንደማሳያ በማንሳት ጭምር።

አቶ ክቡር ገና በበኩላቸው አሁን ያለው የጥቁር ገበያ ዋጋ አገሪቱ ውስጥ ተቃውሞ ከመነሳቱ በፊት ከነበረው የምንዛሬ ዋጋ መቀራረቡን ያወሱና በአገሪቱ የተሻለ መረጋጋት እየተፈጠረ ስለመምጣቱ አመላካች እንደሆነ ያትታሉ።

መንግሥት በዳያስፖራ ሃዋላ ላይ ከፍ ያለ ተስፋን ማሳደሩ ግን ብዙም ምቾት አይሰጣቸውም። ከዚያ ይልቅ መንግሥት አገር ውስጥ ምጣኔ ሐብቱን የሚያነቃቃ እርምጃ እንዲወስድ ነው ፍላጎታቸው።

“የጥቁር ገበያው ዶላር ከብር ጋር የሚያሳዩት የምንዛሬ ምጣኔ መጠጋጋቱ እስከየት ይዘልቃል?” ተብሎ የተጠየቁት አቶ ክቡር ፍላጎት እየጨመረ ስለሚሄድ በአጭር ጊዜ ውስጥ 28/29 ድረስ ይወርዳል ብለው እንደማያስቡ ያስረዳሉ።

ከ30 እስከ 32 ድረስ እየዋለለ እንደሚቆይም ግን ይተነብያሉ። ለዚህ ትንበያ ያደረሳቸው ደግሞ በኢኮኖሚው ውስጥ ምንም አዲስ የተጨመረ ነገር አለመኖሩ ነው።

“እኔ እንደሚገባኝ ከዛሬ ሁለት-ሦስት ዓመት በፊት የነበርነበት ቦታ እየተመለስን እንደሆነ ነው።”