Home Blog Page 3

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ከአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ጋር ተወያዩ |BBC Amharic

0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ”ግንቡን እናፍርስ፤ ደልድዩንም እንገንባ” በሚል መሪ ቃል በአሜሪካ ጉዟቸውን በማገባደድ ላይ ናቸው። በቆይታቸው በአሜሪካና በኢትዮጵያ ተከፋፍለው የቆዩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶሶች ጋር በመገናኘት ሲኖዶሶቹ በመዋሃድ አንድ ሆነው እንዲሰሩ ማስማማት ችለዋል።

ባሳለፍነው አርብ ደግሞ በአሜሪካ ከሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ ፖርቲዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር። በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጥያቄዎች አቅርበው ጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሽ ሰጥተውባቸዋል።

ከዚህም ባለፈ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። ለአንድ ሰዓት ያህል የቆየው ውይይት የትውውቅና አንዳንድ መሠረታዊ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ ስምምነት የተደረሰበት እንደነበረ የግንባሩ የዓለም አቀፍ አመራር የዉጭ ግንኙነት ኃላፊና የንቅናቄዉ ምክር ቤት አባል አቶ ነአምን ዘለቀ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከዚህ አጭር ውይይት በኋላ ሌላ ሁለተኛ ዙር ንግግር እንደነበረም አቶ ነአምን ተናግረዋል።

ይኸውም ቅዳሜ ማታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ አርፈውበት ነበር በተባለው ‘ወተር ጌት’ ሆቴል 12ኛ ፎቅ ላይ የተካሄደው ነው። በዚህ ውይይት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ አምስት ከፍተኛ የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች የተገኙ ሲሆን ከመንግሥት ወገን አቶ ለማ መገርሳ ተገኝተዋል።

ከሁለት ሰዓት በላይ የዘለቀው ይህ ውይይት ወዳጅነትና መግባባት የሰፈነበት ነበር ብለዋል አቶ ነአምን ለቢቢሲ። ሆኖም የውይይቱን ዝርዝር ጉዳዮች ከመናገር ተቆጥበዋል።

አሁን በሃገሪቱ እየታየ ያለውን ለውጥ ግንቦት 7 እንደሚደግፈውና ኢትዮጵያን ወደ ሃቀኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ትብበር እንደሚያደርግ ገልጸዋል። በተጨማሪም ሀገር ቤት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አባላቱን ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የማምጣትና የማደራጀት ዕቅድ ላይም ሰፋ ያለ ውይይት መደረጉ ተመልክቷል።

ግንባሩ በሰላማዊ መንገድ ወደ ሃገር ቤት የሚገባበት፤ የመሪዎቹን የደህንነት ጉዳይ ዋስትና የሚያገኝበት ሁኔታዎች ላይ ውይይትም ተደርጓል። በተጨማሪም በኤርትራ በረሀ ላይ የሚገኙ የሠራዊቱ አባላት ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው የሚመለሱበትን ሁኔታም በቅድሚያ ማመቻቸት እንደሚያሻ ተናግረዋል። አቶ ነአምን በአጠቃላይ ውይይቱን “በጣም ውጤታማና በጣም ፍሬያማ” ሲሉ ነው የገለጹት።

በቀጣይ በአገሪቱ በሚደረገው ምርጫ ስለመሳተፍ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተነጋግረው እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ነአምን “እሱ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ አይደለም” ካሉ በኋላ “ለኛ ዋናው ነገር አሁን የተጀመረውን ለውጥ መደገፍና ዴሞክራሲያዊ ተቋማት እንዲገነቡ ማገዝ ነው” በማለት እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለሥልጣን መፎካከር አሁን አጀንዳቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል።

የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ወደ አገር ቤት የሚመለሱበት የጊዜ ሰሌዳ ተቀምጦ እንደሆነ ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ነአምን ጊዜውን በትክክል ማስቀመጥ ቢቸገሩም ምናልባት በሳምንታት ሊሆን እንደሚችል ጥቆማ ሰጥተዋል።

አርበኞች ግንቦት 7 ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በተደረጉ ጉዳዮች ዙርያና በመጪው የድርጅቱ እቅድ ላይ ዛሬ ማምሻውን ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። BBC Amharic

‹‹የ 12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፡፡›› የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

0

የ12ኛ ክፍል ውጤት ተለቀቀ፡፡

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን ሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ገልጧል፡፡

እንደ ኤጀንሲው ገለጻ ሁሉም ተማሪዎች በአጭር የጽሁፍ መልዕክት በሞባይላቸው ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡
በመሆኑም ውጤታቸው በአጭር የጽሁፍ መልዕክት እና በድረ ገጽ WWW.NAEAE.GOV.ET ብቻ እንደተለቀቅ ነው ያስታወቁት፡፡
ተማሪዎችም በውጤታቸው መሰረት የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን ማስተካከል እንደሚችሉ ዶክተር ዘሪሁን ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም መሰረት በማድረግም የማለፊያ ነጥቡ በቅርቡ እንደሚታወቅ አስታውቀዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አስማማው በቀለ

 

መርካቶ ያገለገሉ ጫማዎችን እንዴት ነው የምትቀበላቸው? Fana Television

0

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የተገቢነት ሙግት በሚያነሱ ሁለት ሲኖዶሶች ተከፍላ ስትወዘወዝ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ጊዜ ተቆጥሯል።

በመጀመሪያ በቀድሞው ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ ከእርሳቸው ኅልፈተ ህይወት በኋላ ደግሞ በብፁዕ አቡነ ማቲያስ በሚመራው እና መቀመጫውን አገር ውስጥ ባደረገው ሲኖዶስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ መርቆሪዮስም ፓትርያርኩ አድርጎ በሚቆጥረውና ሰርክ ‘ስደተኛው’ እየተባለ በሚጠራው ሲኖዶስ መካከል ሰላም አውርዶ እርቅ ለመፍጠር ተደጋጋሚ ሙከራዎች መደረጋቸው ባይቀርም እስካሁን ድረስ ስኬት ሲናፍቃቸው ቆይቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አንዲት ቤተ ክርስትያንን እና አማኞቿን እንወክላለን የሚሉትን ሁለቱን የእምነት አስተዳዳር መዋቅሮች ዓይን ለዓይን ከመተያየት ሲከለክል የቆየው ቁርሾ ተወግዶ ወደአንድነት እንዲመጡ ፍላጎታቸውን ከገለፁ በኋላ የተጀመረው እንቅስቃሴ ግን ፍሬ የያዘለት ይመስላል።

ከትናንት አመሻሹ አንስቶ ሲኖዶሶች እርቀ ሰላም ይዘገብ ይዟል። ውህደቱ ምን ፋይዳ እና ትርጉም አለው? ቀጣይ እርምጃዎችስ ምን ይሆናሉ ስንል የእምነቱን ሊቃውንት አነጋገረናል።

የቤተ ክርስትያኗ አመራር እንዴት ለሁለት ተከፈለ?
በ1983 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) የደርግን ስርዓት ጥሎ ስልጣን ላይ ሲወጣ፣በአራተኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ደስተኛ እንዳልነበር በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ማኅበረ ካህናት ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ ይናገራሉ።

“በቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ ልዩነት መፈጠር የተጀመረው ብፁዕ አቡነ መርቆሪዮስ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ተደርጎ ብፅዕ አቡነ ጳውሎስ በስፍራቸው እንዲተኩ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ነው፤” ይላሉ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ።

ቀሲስ ኤፍሬም እንደሚሉት አዲሱ መንግሥት የፖለቲካ ጉልበቱን በመጠቀም ፓትርያርኩ ከመንበራቸው እንዲነሱ በጉምቱ ባለስልጣናቱ ሳይቀር ጥረት አድርጓል።

በዚህ አስተያየታቸው የሚስማሙት የቀድሞው የማኅበረ ቅዱሳን አመራር ዲያቆን ዳንዔል ክብረት ናቸው።

እርሳቸው እንደሚሉት በወቅቱ ብፁዕ አቡነ መርቆሪዮስ መንግስታዊውን ጫና መቋቋም ካለመቻላቸውም ባሻገር፤ አንዳንድ የኃይማኖት አባቶች የእርሳቸው መንበራቸውን መልቀቅ ብቸኛው መፍትሄ ነው ማመናቸው አልቀረም።

የፓትርያሪኩን ከአገር መውጣት ተከትሎም ሌላ ምርጫ ተካሄደና ሌላ ፓትርያሪክ ተሾመ፤ አንዳንድ ጳጳሳት ስደተኛውን ፓትርያሪክ መከተልን መረጡ፤ ከጥቂት ዓመታት በኋላም በአገረ አሜሪካ ሌላ ሲኖዶስ መሰረቱ፤ ሌሎቹ ደግሞ አገር ውስጥ በነበረው ሲኖዶስ ለመቀጠል ወሰኑ።

“ከዚህም የተነሳ ቤተ ክርስትያኒቷ በሁለት ሲኖዶስ፣ በሁለት ፓትርያሪክ የምትመራ ሆነች” ይላሉ ዲያቆን ዳንዔል።

ለእርሳቸው ይህ ሂደት ሁለት የቤተ ክርስትያኒቷን አስተምህሮዎች የጣሰ ነው እንደሆነ ዲያቆን ዳንኤል ይናገራሉ። እንደ እርሳቸው አባባልም በመጀመሪያ “አንድ አባት ልጆቹን ትቶ መሄድ ተገቢ አይደለም፤” በመቀጠል “እኝህ አባት ከአገር ቢወጡም እርሳቸውን እና ሌሎቹን ከስደት ለመመለስ ጥረት መድረግ ሲገባው ሌላ አባት ተሾመ። ከበፊትም የሚመዘዝ ችግር ቢኖርም ይህንን ችግር በትዕግስት እና በብልሃት ማለፍ ቢቻል ኖሮ ይ. ነገር አይፈጠርም ነበር። የቤተክርስያኒቱ ስርዓት አንድ አባት በህይወት እያለ ሌላ አባት መሾም አይፈቅድምና።”

ክፍፍሉ ምን ዳፋ አስከተለ?
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን አሁንም ትልቋ የአገሪቱ የእምነት ተቋም ትሁን እንጅ የአማኞቿ ቁጥር ከአጠቃላዩ ምዕመን ያለው የመቶኛ ድርሻ እያሽቆለቆለ ነው የሚገኘው።

ለመጨረሻ ጊዜ በ1999 ዓ.ም በተደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ መሰረት ከአገሪቱ አጠቃላይ ህዝብ ከአርባ ሦስት በመቶ ከፍ የሚለው የእምነቱ ተከታይ ሲሆን፤ ቤተ ክርስትያኗ በ1977 ዓ.ም ቆጠራ ወቅት ከነበራት አገር አቀፍ የምዕመናን ድርሻ ግን ሃምሳ አራት በመቶ ገደማ ነበር።

ዲያቆን ዳንዔል ለዚህ አብዩ ተጠያቂ “የቤተ ክህነቱ መዳከም ነው” ይላሉ።

“ቤተ ክህነቱ ቤተ ክርስትያንዋን መሸከም ከሚችልበት አቅም በታች ነው። አሁን ላለው ቤተ ክህነት፣ አሁን ላለችው ኢትዮጵያ እና አሁን ላለው ትውልድ የሚመጥን አይደለም። ሁለቱም ቦታ፤ አሜሪካም ያለው እዚህም ያለው። ለዚህ የሚመጥን አቅም የለውም” ሲል ያብራራል።

ለቤተ ክህነቱ መዳከም ደግሞ የሲኖዶስ፣ የኃይማኖት መሪዎችን እና የአማኞችን መከፋፈል ተወቃሽ ያደርጋሉ።

ቤት ክህነቶች ዋና ተግባራቸውን “ውጊያ” ላይ በማድረጋቸው ምክንያት ተቀዳሚ ሥራቸው ሊሆን ይገባው የነበረው “ወንጌልን የማዳረስ ስራ፣ የሐዋርያዊነትን ስራና ምዕመናንን የመጠበቅን ስራ ተረስቷል” ይላሉ።

ቀሲስ ኤፍሬም በበኩላቸው የሁለት የተኮራርፉ አስተዳደሮች መኖር፣አንድ እምነት እና አንድ ስርዓት ያላቸው ምዕመናን እና ካህናት ለመራራቃቸው ምክንያት ከመሆኑም ባሻገር ይህም በፋንታው በርካታ ችግሮችን ወልዷል ይላሉ።

“ቤተ ክርስትያኗ በአጠቃላይ አሁን ላለባት ድክመት፣ ለምዕመናኗ ቁጥር መቀነስ፣ ለአስተዳደሯ መበላሸት፣ ሙስና እና ዝርፊያ [በጓዳዋ] ለመሰልጠናቸው፣ ሙያው እና ስነ ምግባሩ የሌላቸው ሰዎች በልዩ ልዩ መዋቅሮች ለመሰግሰጋቸው ሁሉ በር የከፈተው ይህ በአባቶች መካከል ያለው ልዩነት ነው” ሲሉ ይናገራሉ።

አሁንስ ከቤተ እምነት ላይ የቤተ መንግሥት ጥላ ተገፏል?

ሲኖዶሶቹ አንዳቸው ሌላኛቸውን የእምነቱን ህግ እንደጣሱ ወይንም ኃይማኖታዊ ቅቡልነት እንደሌላቸው ያዩዋቸው የነበረ ለመሆኑ አንደኛው መገለጫ እርስ በራሳቸው መወጋገዛቸው ነው።

አሁን ይካሄድ በያዘው ሽምግልና ላይ በጋራ ሲፀልዩ መስተዋላቸው ይሄንን ውግዘት በይፋዊ ባይሆን በተግባር ቀድመው ለማንሳታቸው ምስክር ነው የሚሉት ቀሲስ ኤፍሬም ናቸው።

እርስ በእርስ የሚተያዩባቸው መንገዶች ምናልባትም በተደጋጋሚ የተደረጉትን የእርቅ ሙከራዎች የማክሰም ድርሻ ቢኖራቸውም፤ የአገሪቱ ፖለቲካዊ መልክ ጉልህ ሚና እንደነበረው ግን ሁለቱም ይስማማሉ።

የአሁኑ እርቀ ሰላም ስኬትንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስተዳደር አቋም ጋር የሚያያይዙት ብዙ ናቸው።

ቀሲስ ኤፍሬም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን በሌሎች የዓለም ክፍሎች ካሉ የክርስትና እምነቶች በተለየ መንግስታዊ ትስስር ከምስረታዋ አንስቶ እንዳላት ያስረዳሉ።

“በሌሎች አገራት በአብዛኛው እምነቱ በህዝቡ ዘንድ ከሰረፀ በኋላ መንግስታት እንደተቀበሉት ታሪክ የሚያስረዳ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ግን የሆነው በተቃራኒው መንግስት እምነቱን ተቀብሎ ነው ከዚያ ወደሕዝቡ ያሰረፀው። ስለዚህም ከዚያ የሚመዘዝ መንግስታዊ ቁርኝት አለ” ይላሉ።

በየዘመኑ የመጡ መንግስታት ቤተ ክርስትያኒቷን ዓላማቸውን ለማስፈፀሚያ ተጠቅመውባታል የሚሉት ቀሲስ እሸቴ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር መንግስት እና እምነትን ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የሚለያይ እርምጃ እንደሚወስድ ተስፋቸውን ይገልፃሉ።

ከዚህ በኋላስ?
ዲያቆን ዳንዔል የፖለቲካዊ ፍላጎት መጥፋት እንጅ ሲኖዶሶቹን በእርቅ ማጨባበጥ እስካሁንም የሚከብድ ነገር ሆኖ እንዳልነበር ያምናሉ።

ከዚህ ቀደም የተደረጉ የእርቅ ጥረቶች “ላለመሳካታቸው አንዱ እንቅፋት የአገሪቱ ፖለቲካ ነው” ይላሉ አክለው “ምክንያቱም ሁለቱም በየራሳቸው የሚደግፏቸው የፖለቲካ አዝማሚያዎች አሏቸው። የአገር ቤቱ ሲኖዶስ የአገር ቤቱን ፖለቲካ፣ የውጭው ሲኖዶስ ደግሞ የውጭውን ፖለቲካ ስለሚደግፉ እና በፖለቲካው ጫና ውስጥ በመውደቃቸው ነው።”

በውጭ አገር ያለው ሲኖዶስ በአማኞች ቁጥር ከተመዘነ ያለው አቅም በጣም ትንሽ ይሁን እንጅ በሚያንቀሳቅሰው የገንዘብ መጠን እና ባለው ተፅዕኖ ትከሻው የደረጀ ነው እንደ ዲያቆን ዳንዔል አስተያየት።

ከሁለቱ ፓትርያሪኮች መካከል የስልጣን መንበሩ ላይ መቀመጥ ያለበት የሚለው ጥያቄ ሌላኛው ማነቆ ሆኖ የቆየ ቢሆንም እርሱን አሁን መፍታት ብዙም አይገድም ይላሉ።

ብፁዕ አቡነ ማቲያስ የአስተዳደሩን ስራ እየሰሩ፤ አቡነ መርቆሪዮስን ደግሞ በመንበራቸው ሆነው ከአስተዳደሩ ስራ ግን ገለል እንዲሉ ስማቸውም በቅዳሴ እየተጠራ በሲኖዶሱም እየተገኙ እንዲቀጥሉ ማድረግ አማራጭ ሆኖ እንደሚታያቸው ይናገራሉ።

“አቡነ መርቆሪዮስን የአስተዳደር ስራ ላይ እንዲሳተፉ ቢደረግ ከጤናም ከዕድሜም፣ከአገሪቱ ከሃያ ዓመት በላይ ርቀው ከመቆየታቸውም አንፃር ሊቸገሩ ይችላሉ።” ይላሉ።

ቀሲስ ኤፍሬም በበኩላቸው በውጭ አገር ያሉት ፓትርያርክ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም አባቶችና ካህናት ወደአገር ቤት ተመለሰው በየአገር ስብከቱ እንዲመደቡና የአገልግሎት መዋሃድ እንዲፈጠር ይጠብቃሉ።

ከዚህም ባለፈ ተመሳሳይ ክፍፍል እንዳይፈጠር “ህጎች ይወጣሉ፣መመሪያዎች ይወጣሉ፤ በተለይ ከመንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት ምን ዓይነት መሆን እንዳለበት ቤተ ክርስትያን ህግ ታወጣለች ብለን ተስፋ እናደርጋለን።” ብለዋል።

የሐመሯ ወጣት፡ ከሞት አፋፍ ሕልምን ወደ መኖር |BBC Amharic

0

ስሜ ኢሪ ዲማኮ ቾርዲ ይባላል። ኢትዮጵያዊትና ፈረንሳዊት ነኝ። አሁን የምኖረው በሞንትሪያል ካናዳ ነው።

ዕድሜዬ አምስት እያለ ነው ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሐመር የወጣሁት። ለነገሩ ስለዕድሜዬን እርግጠኛ መሆን አልችልም። ምክንያቱም በደቡብ ኢትዮጵያ ዕድሜ አንቆጥርም ነበር።

ቤተሰቦቼ እረኞች ናቸው። እነሱም የአየር ፀባይ ለማወቅ ከዋክብትን በመቁጠር፣ ከብቶቻችውን በማንበብ የሚተዳደሩ ናቸው።

ከሞት መንጋጋ መሹለክ
የተወለድኩበትን ለቅቄ ለመሄድ የተገደድኩት ስለልጆች በነበረ እምነት ምክንያት ነበር። ‘ሚንጊ’ ይባላል።

በዚያ አካባቢ የአንድ ልጅ ጥርስ ሲነቅል በቅድሚያ የታችኛው ጥርስ ከተነቀለ የተረገመ ነው ተብሎ ይታመን ነበር። እንዲህ ዓይነቱ ልጅ በመንደሩ ቢቆይ ለቤተሰቡም ሆነ ለመንደሩ ክፉ ዕጣ ፈንታን ይጠራል ብለው ያስቡ ነበር። ይህ ዓይነቱ አጋጣሚ ሲከሰት ቤተሰቡ ሦስት አማራጮች አሉት።

አንደኛው ጠንቋይ ዘንድ ተሂዶ ኃጢያትን ማንጻት ሲሆን፤ ሁለተኛው እናት ልጇን ከመንደሩ አርቃ ወስዳ ጨክና መጣል ነው። ሦስትኛው አማራጭ ደግሞ የመንደሩ ነዋሪዎች ልጁን በደቦ እንዲገድሉ ማድረግ ነበር።

በዚያን ወቅት አባቴ ሞቶ ነበር። እናቴ ደግሞ አራስ ነበረች። በእቅፏ ሁለት ልጆችን ይዛ ቀርታ ነበር። ልታድነኝ የአቅሟን ሞከረች። ጠንቋይ ዘንድ ወስዳኝ ስትመለስ የሚያምናት ሰው አልነበረም። በመጨረሻም የአንድ ሰዓት የእግር ጉዞ የሚያስኬድ ከተማ ይዛኝ ሄዳ ለሕጻናት ማሳደጊያ ሰጠችኝ። ያም ሆኖ እዚያ ብዙ አልቆየሁም።

አንድ አስተማሪ ከእናቷ ጋር ከሚኖሩበት ቤት ወሰደችኝ። ብዙ ነገሮች ትዝ አይሉኝም። የማስታውሰው ነገር ቢኖር ሁለት የአየርላንድ ሚሽነሪዎች ጋር መኖር እንደጀመርኩኝ ከዕለታት አንድ ቀን ያሳደገችኝ እናቴ ከአጎቴ ጋር መጥተው ሲወስዱኝ ነው።

ከደቡብ ወጥቼ አዲስ አበባ ስደርስ ሁለት ወራት ብቻ ነበር ያለፉት።

ከአዲሳ’ባ እስከ ካናዳ
17 ዓመት እስኪሞላኝ ድረስ አዲስ አበባ ኖርኩኝ። አባቴ ለሥራ ወደ ኮሎምቢያ ሲላክ ከእናቴ ጋር አብረነው ሄድን። የሁለተኝ ደረጃ ትምህርቴን ለማጠናቀቅ የቀረኝን የመጨረሻ ዓመት ኮሎምቢያ እንደጨረስኩኝ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን ለመጀመር ወደ ካናዳ አመራሁ።

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2011 ጀምሮ እስካሁን በካናዳ ነው ያለሁት።

በመሐሉ ወደ አገር ቤት ተመልሼ ነበር።

ከአገር ከወጣሁ ከአምስት ዓምታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ ለሦስት ወራት ያህል ተቀመጥኩኝ። በውስጤ ይመላለሱ የነበሩትን ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘትም ፍላጎት ነበረኝ። ባሳደጉኝም ቤተሰቦቼ እርዳታ ከዘመዶቼ ጋር ወደ ደቡብ አቀናን።

ስሜቶቼ፣ እንባዬ፣ጭንቀቱ፣ምሬቱና ግራ መጋባቱ ከሐሳቦቼ ጋር ተቀላቅለው እንደ መርፌ እዚያም እዚም ይወጋጉኝ ነበር።

ከረሳኋዋቸውም ሆነ ከማስታውሳቸው ሰዎች ጋር መገናኘቱ የደስታ ስሜት ፈጥሮብኝ ነበር። ተቆጥረው የማያልቁ ዘመዶቼን በማግኘቴና ከእህትና ከአክስቴ ልጆች ጋር ያለኝን መመሳሰል ሳየው በጣም ገረመኝ። አሁን ውስጤ ሰላም ስላገኘ መሄዴን እንደ ስጦታ እቆጥረዋለሁ። ሰላም በመፍጠሬም ሳልሸማቀቅና ሳላፍርበት ስለ ሕይወቴ ማውራት እችላለሁ።

መልካሙ ዜና አሁን በሐመር እንደዚህ ዓይነት እምነት ቀርቷል። እኔ ከመጨረሻዎቹ አንዷ ነበርኩ።

ከእናቴ ጋር ወደ አዲስ አበባ ያመጣኝ አጎቴ እንደነገረኝ ከሆነ መኪና ውስጥ የጂሚ ሄንድሪክስን ካሴት ሲያጫውት አብሬ ለመዝፈን ጊዜ እንዳልፈጀብኝ ያስታውሳል።

ቤት ውስጥ ሁልጊዜም እዘፍን ነበር። አባቴ ደግሞ የድምፅ ትምህርት እንድወስድ ያበረታታኝ ነበር፤ ገና በ11 ዓመቴ።

እራሴን እንዳውቅ ከረዱኝ ትምህርቶች አንዱ ሙዚቃ ነው። በተለይ የአተነፋፈስ ሥልት ሳጠና በጣም ተደንቄ ነበርና ምንጊዜም ቤት ስመለስ ቅልል ያለ ስሜትና ደስታ ይሰማኝ ነበር። ወላጆቼም ፒያኖ እንድማር ገፋፍተውኝ ለስምንት ዓመታት ተምሬያለሁ፤ ብዙም አልገፋሁበትም እንጂ።

ያም ሆኖ መዝፈንና ግጥም መጻፍ እወድ ስለነበር ከሙዚቃ አልተላቀቅኩም።

አሁን አብራኝ ከምትዘፍነው ጓደኛዬ ጋር የተዋወቅነው አንድ ሌላ ጓደኛዬ ባዘጋጀችው ምሽት ላይ ነበር። ከዚያን ጊዜ ወዲህ እነሆ አብረን እየሠራን እንገኛለን። እሷ ግማሽ ካናዳዊት፣ግማሽ ከቡርኪና ፋሶ ብትሆንም ያጋጣሚ ነገር ስማችን ተመሳሳይ ነው።

እሷ ካኢሪ ትባላለች። ስለዚህ የቡድናችንን ስም ካ-ኢሪ አልነው።በሙዚቃችን የአፍሪካን ሙዚቃ ስልት ከጃዝ፣ ከሂፕሆፕና ከኤሌክትሮኒክ ሙዚቃዎች ጋር እያዳቀልን ነው የምንጫወተው። የመጀመሪያውን ሥራችንን ከሁለት ሳምንታት በፊት በአልበም መልክ ለሕዝብ አቀረብን።

ሙዚቃ ሕይወቴ ሥራዬ ብዬ ሙዚቃ መጫወት ከጀመርኩኝ አራት ዓመታት አስቆጠርኩኝ። አምርሬ የያዝኩት ከዛሬ 6 ዓመት ጀምሮ ቢሆንም ግን ከሕጻንነቴ ጀምሮ ለሙዚቃ እንደተፈጠርኩኝ ይሰማኛል።

ሙዚቃ ለመሥራት የሚገፋፋኝ ዋናው ነገር ለነፍሴ የሚሰጠኝ ነጻነት ነው። ስዘፍን በሕይወት እንዳለሁ ይሰማኛል። ሁሉን ነገር ትቶ መላው መንፈሴ በሙዚቃው ውስጥ ይንሳፈፋል።

ብዙውን ጊዜ የምጽፈው ስለ ሰላምና ስለ ይቅር መባባል ነው። በውስጣቸውም መጥፎ ነገሮች ቢያጋጥሙም ሁልጊዜ እንደምንም ብዬ መጨረሻው ወደ ጥሩ ነገር እንዲያዘነብል አደርጋለሁ። በሙዚቃዬ ፍቅርን ማስተማርና ማንፅባረቅ ነው የምመኘው። በሕመም ውስጥ መዳን ይገኛልና።

የተለያዩ የአርት ስልቶችን አቀላቅላለሁ። በማቀላቀሌም ችሎታዬንና ማንነቴን ማንፅባረቅ ችያልሁ። የማህበራዊ ድረ ገፆችን አጠቃቀም እየለመድኩ ቢሆንም በነሱ በኩል ግን ቢያንስ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ እመኛልሁ። ስለተለያዩ ሰዎችና ስለተለያዩ ብሔሮች የሚማሩበት እንዲሆን እፈልጋልሁ። ሰው ስለተፈጥሯዊ ይቅር መባባልና መዳን እንዲማሩ እፈልጋልሁ። ትንሽ ነኝ ብሎ የሚያስበውም ሰው ቢሆን ትልቅ ቦታ እንዳለው እንዲያውቁ ምኞቴ ነው።

ሕልምና ምኞቴ
ሕልሜ ሙዚቃዬን ለዓለም ማድረስ ነው። በዚህም ከማምንባቸው ነገሮች አንዱ የሆነውን ፍቅርን መቋደስ ነው። የተለያዩ ቋንቋዎች ተምሬ ደግሞ ዓለምን መዞር እመኛለሁ። ስለተለያዩ ባህሎች ማወቅ፣ ማንነቴን ማወቅ፣ እምነቴንና ደስታዬን ማሳደግም የምኞት ሰንዱቄ ውስጥ የሚገኙ ነገሮች ናቸው።

መቼም ቢሆን ማደግ ማቆም አልፈልግም። ምክንያቱም ይህች ምድር ማቆምያ የላትም። ዓለም ብዙ የምትሰጥን ነገር አለ። እኔም ያለኝን ከመስጠት ወደ ኋላ አልልም። መቼም!

እኔና ካኢሪ የተለያዩ መድረኮች ላይ ተጫውተናል። ያኤል ናይሚ ለተሰኘ ታዋቂ ዘፋኝ ኮንሰርት መክፈቻ፣ንዊ ዳፍሪክ ላይና ሌሎችም።

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ደግሞ ኖማድ በተሰኘው ታዋቂ የሴኔጋል ፌስቲቫል ላይ እንድንጫወት ተጋብዘናልና። ብዙ አጋጣሚዎች እየተከፈቱልን እንድሆነ ይሰማኛል። እኛም ያለንን ፍቅር ለዓለም ለማካፈል ዝግጁ ነን።

በአማርኛ፣ በእንግሊዘኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በቡርኪናፋሶ ቋንቋ (ሳሞ) እንዘፍናለን። ምን ይሄ ብቻ…አንዳንዴም እራሳችን በምንፈጥረው ቋንቋ ጭምር እንዘፍናለን። Read More

በደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት እሳት ተነሳ |BBC Amharic

0

ታራሚዎች ያስነሱትን አመፅ ተከትሎ የደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት ለእሳት አደጋ መዳረጉን የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር አስታወቀ።

የማረሚያ ቤቱ ምክትል መምሪያ ሃላፊ እና የታራሚዎች አያያዝና አስተዳደር ቡድን መሪ የሆኑት ምክትል ኮማንደር ባንቴ ጥበቡ ስለሁኔታው ለቢቢሲ ሲያብራሩ፤ አመፁ የተጀመረው ትናንት ምሽት የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህጉ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ የምህረት አዋጅን በተመለከተ በቴሌቭዥን የሰጡትን ዝርዝር ተከትሎ እንደሆነ ተናግረዋል።

ከምክትል ኮማንደር ባንቴ መረዳት እንደቻልነው ታራሚዎቹ በምህረት አዋጁ ተጠቃሚ አንሆንም የሚል ዕምነት አድሮባቸዋል።

ትናንት ምሽት ቁጣቸውን ሲያሰሙ የነበሩ ታራሚዎችን ማረጋጋት ተችሎ እንደነበር የተናገሩት ም/ ኮማንደሩ ”ዛሬ ጠዋት ግን የታራሚዎች ማደሪያ በር ከተከፈተ በኋላ ታራሚዎች በሮችን ገነጣጠሉ ከዚያም የመሳሪያ መጋዘን ቤቶችን ለመስበር ጥረት አድርገዋል” ሲሉ ስለተፈጠረው ሁኔታ አብራርተዋል።

ቆየት ብሎም በተቀሰቀሰ እሳት የማረሚያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና የማደሪያ ቤቶች በእሳት መያያዛቸውን ም/ኮማንደር ባንቴ ጥበቡ አክለው ነግረውናል።

ይህ ዜና እስከ ተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የእስረኞቹ አመፅ ጋብ ቢልም ቃጠሎውን ለማስቆም እንዳዳገተ ለማወቅ ችለናል። በሰው ህይወት ላይ ስለደረሰ ጉዳት ያገኘነው መረጃ የለም።

የደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት በተለያዩ ወንጀሎች ጥፋተኛ ናቸው የተባሉ እና ፍርዳቸውን የሚጠብቁ ከአንድ ሺ በላይ ታራሚዎችን እና ተጠርጣሪዎችን በውስጡ የያዘ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኤርትራ አቻው ጋር በነሐሴ ወር አጋማሽ አስመራ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ ነው | FBC

0

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 16 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኤርትራ አቻው ጋር በነሐሴ ወር አጋማሽ አስመራ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ ነው።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሁለቱን ሀገራት ወንድማማችነት ለማጠናከር አስመራ ከተማ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ባሳለፍነው ሳምንት ደብዳቤ መላኩ ይታወሳል።

የኤርትራ ብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ጥያቄውን መቀበሉን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ በመላክ ይሁንታውን ገልጿል።

ጨዋታውም የፊታችን ነሃሴ አጋማሽ ላይ አስመራ ከተማ የሚደረግ ሲሆን፥ የጨዋታው ትክክለኛ ቀን አዲሱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ የሚወሰን ይሆናል ተብሏል።

ፌዴሬሽኑም መሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ለመፈፀም እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑን ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በ1990 በተቀሰቀሰው የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ምክንያት የኢትዮጵያ ክለቦች እና ብሄራዊ ቡድኑ ከኤርትራ ክለቦች እና ብሔራዊ ቡድን ጋር ጨዋታ አድርገው አያውቁም።

አሁን በሁለቱ ሃገራት መካከል የነበረው ግንኙነት ወደ ሰላም በመመለሱ የኢትዮጵያ ክለቦች ከኤርትራ ክለቦች ጋር የእንጫወት ጥያቄ እያቀረቡ ይገኛል።

ፋሲል ከነማ ጥያቄ አቅርቦ ከኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መልካም ምላሽ ያገኘ ሲሆን፥ የትግራይ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮም በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ጨዋታዎችን ለማድረግ ጥያቄ ማቅረቡ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጳጉሜን ወር ከሴራሊዮን ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ

”አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ናት” ከንቲባ ታከለ ኡማ | Awaze News

0

አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በንቲ (ኢንጂነር) የድሃውን ማህረሰብ ፍላጎት ለሟሟላት ተግተው እንደሚሰሩ ለቢቢሲ ተናገሩ።

በሥራ ዘመናቸው የከተማዋ ነዋሪ ዋነኛ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት እጥረትን ጨምሮ፣ የውሃ እና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በመካከለኛ እና ዝቀተኛ ገቢ ለሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ለማዳረስ ሀሳብ መሰነቃቸውን አክለው ገልጸዋል።

የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ የሆኑት አቶ ታከለ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ስላልሆኑ በምክትል ከንቲባነት የተሾሙ ቢሆንም የከንቲባውን ሥራ እንደሚሰሩ ተገልጿል።

ሹመታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ የበርካቶች መነጋገሪያ ሆነውም ቆይተዋል። ሹመታቸውን የሚቃወሙ ወገኖች ከሚከራከሩባቸው ምከንያቶች መካከል፤ የከተማዋ ተወላጅ ስላልሆኑ ከተማዋን ለማስተዳደር የውክልና ጉድለት አለባቸው፣ ብሔር ዘመም አቋማቸው የበርካታ ብሔረሰቦች መናገሻ የሆነችው አዲስ አበባን ካለ አድልዎ ለመምራት ያላቸው አቋም አጠራጣሪ ነው የሚሉት ይገኙበታል።

በሌላ በኩል ሹመታቸውን የሚደግፉ ሰዎች የሥራ አፈጻጸም ችሎታቸው እንጂ ብሔራቸው ከጥያቄ ውስጥ መግባት የለበትም፣ ተሰናባቹን ከንቲባን ጨምሮ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች ለተከታታይ በርካታ ዓመታት ከተማዋን አስተዳድረዋል የኢንጂነር ታከለ ጉዳይም ከዚህ የተለየ አይሆንም ሲሉ ይከራከራሉ።

በእነዚህ ሀሳቦች ላይ ያላቸውን ምላሽ የተጠየቁት አዲሱ ከንቲባ ታከለ ኡማ ለተሰነዘሩት የድጋፍ እና የነቀፌታ አስተያየቶች አክብሮት እንዳላቸው ገልፀዋል።

”አዲስ አበባ የኢትዮጵያዊነታችን መገለጫ፣ የሁላችንም ከተማ ናት ብዬ አምናለሁ። ከኢትዮጵያዊነት አልፎም የአፍሪካዊነት መገለጫ ናት፤ ምክንያቱም የአፍሪካ ህብረት መቀመጫም ናትና። ይህ እምነቴ ዛሬ የመጣ ሳይሆን ከልጅነቴ ጀምሮ አብሮን ያደገ ነው” ብለዋል።

አዲሱ ከንቲባ ከአዲስ አበባ ብዙም ሳይርቁ መወለዳቸውና ማደጋቸው በከተማዎ ውስጥ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦችን ባህል እና ሥነ-ልቦናን እንዲረዱት እንዳገዛቸው ተናግረዋል። ለወደፊቱ የከተማዋን ነዋሪዎች በእኩል ዐይን የማስተዳደር፤ በተለይ ደግሞ የድሃውን ማህበረሰብ ፍላጎት ከምንጊዜም በላይ ለማሟላት የተቻላቸውን እንደሚያደርጉም አክለዋል።

አቶ ታከለ እስከ ከነቲባ ሆነው እሰከ ተሾሙበት ጊዜ የኦሮሚያ የትረስንፖርት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። ከዚያ ቀደምም የተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ከንቲባ ሆነው አገልግለዋል።

ከሦስት ዓመታት በፊት በመላው ኦሮሚያ ተቀጣጥሎ ለነበረው ተቃውሞ ዋነኛ መነሻ ተደርጎ የሚወሰደው የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን የተባለው የመንግሥት እቅድ ነበር። ዕቅዱ ለህዝብ ውይይት ሳይቀርብ የመንግሥት ሃላፊዎች በእቅዱ ላይ ተወያይተው ነበር።

አቶ ታከለም በኦሮሚያ ክልል ቴሌቪዥን በተላለፈ ውይይት ላይ ስለ እቅዱ የሰጡት አስተያየት የብዙዎችን ቀልብ የያዘ ነበር። አቶ ታከለ በሰጡት አስተያየት ”የአንድ ከተማ ፍላጎት ሳይሆን ይህ የማንነት ጥያቄ ነው። አዲስ አበባ እና በዙሪያዋ የመገኙ ከተሞችን ሊያሳድግ የሚችል ዕቅድ ሲታሰብ የኦሮሞን ማንነት፣ ፖለቲካ፣ ባህል እና ታሪክ ሊጎዳ በማይችል መልኩ መሆን አለበት። አርሶ አደሮችን እየገፋ የሚያድግ ኦሮሚያም ሆነ አዲስ አበባ እኔ በግሌ አልፈልግም” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር።

አቶ ታከለም ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ማስተር ፕላኑን አስመልክቶ የሰጡት አስተያየት የበርካቶች የተቃውሞ ምክንያት መሆን የለበትም ብለዋል።

”በወቅቱ የሰጠሁት አስተያየት በተለየ መልኩ መተርጎም የለበትም፣ የስጋት ምንጭም መሆን የለበትም” ይላሉ። ”አዲስ አበባ ብቻ ሳትሆን የትኛውም ከተማ ደሃውን ህብረተሰብ መግፋት የለበትም።”

አሁንም ቢሆን ”ጥቂት ግለሰቦች የአርሶ አደሩ መሬት ላይ ባለጸጋ ሆነው አርሶ አደሩንና የአርሶ አደሩን ልጅ ጥበቃ እና የጉልበት ሰራተኛ ሆኖ ማየት አልፈልግም። ይህ ደግሞ ኦሮሞን ብቻ የሚመለከት ብቻ ሳይሆን በከተማዋ እና በዙሪያዋ የሚኖሩትን ሁሉ የሚመለከት ነው” ብለዋል አቶ ታከለ።

ከሳምንታት በፊት ከንቲባ ድሪባ ኩማን የተኩት ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ 32ኛው ከንቲባ ናቸው።

ታከለ ኡማ ማን ናቸው?

አቶ ታከለ 1976 ዓ.ም በምዕራብ ኦሮሚያ አምቦ አቅራቢያ ተወለዱ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በጎሮ ሶሌ እና ቶኬ ተምረዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጉደር እና አምቦ ተከታትለዋል።

የ12ኛ ክፍል ማልቀቂያ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመደቡ በኋላ በኬሚካል ኢንጂነሪንግ ተመረቁ። በ2000 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢ ምህንድስና (ኢንቫሮመንታል ኢንጂነሪንግ) ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

አቶ ታከለ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሳሉ ነቁ የፖለቲካ ተሳትፎ ነበራቸው። በተማሪነት ዘመናቸው በዶ/ር መረራ ጉዲና ይመራ የነበረው የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) ደጋፊ እንደነበሩ ይናገራሉ፤ በኋላም በ1999 ኦህዴድን ተቀላቅለዋል።

አቶ ታከለ የአዲስ አበባ ምክትል ከነቲባ ሆነው ከመሾማቸው በፊት በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች አገልግለዋል። ከእነዚህም መካከል የኦሮሚያ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ፣ የሱሉልታ ከተማ ከንቲባ እና የሆለታ ከተማ ከንቲባ ሆነው ማገልገላቸው ይጠቀሳሉ።

የሚያፋጁንን ሳይሆን የሚበጁንን ይዘን እንጓዝ | AddisZemen

0

በመደመር ዕሳቤ የተጀመረው የለውጥ ጉዞ የተለያዩ ስኬቶችን በማስመዝገብ አሁንም ቀጥሏል፡፡ ለ20 ዓመታት በቁርሾ ውስጥ የነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ ዳግም ግንኙነታቸውን እንዲያድሱ ከማድረግ በተጨማሪ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በማህበራዊ ዘርፎች አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡
ይህም ሆኖ ታዲያ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ጥቂቶች የለውጡን ጉዞ ለማደናቀፍ ሲጥሩ ተስተውሏል፡፡ ድርጊቱ የማያዋጣና የማይበጅ መሆኑን መንግሥት በተደጋጋሚ በማስገንዘብ ከዕኩይ ድርጊቱ ፊትና ጀርባ የቆሙ አካላት የሠላሙን ጎዳና እንዲከተሉ ጥሪ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ እውነታው ይህ ቢሆንም ታዲያ አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች የአገሪቱን ሠላምና መረጋጋት የሚያውኩ፣ህዝቡን ለስጋት የሚዳርጉ ግጭቶች እየተከሰቱ ነው፡፡ እነዚህን ዕኩይ ድርጊቶች ለመግታትና የድርጊቱን ተዋናዮች ሥርዓት ለማስያዝ መንግሥት ከሠላም ጥሪው ያለፈ እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅቷል፡፡ መንግሥት ሠላምን የማስከበር፣ የዜጎችን በሠላም የመንቀሳቀስ መብትን የማስጠበቅና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት፡፡
ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላትን ለህግ የማቅረብ፤ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን ለመከላከል፣ ለማርገብና ለማምከን የመከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና ተጠያቂዎቹንም ለፍርድ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ በተለይም በሶማሌና ኦሮሚያ ክልል የተከሰቱ ግጭቶችን ለመፍታት በተለያዩ ጊዜያት የተደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ ባለመቻሉ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ለመግባት ተገዷል፡፡ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮችም የፌዴራል የጸጥታ ኃይል ጣልቃ በመግባት የጸጥታ፣ የሠላምና መረጋጋት ሥራ እንዲሰራ፤ እንዲሁም የሕግ ማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተስማምተዋል። ለአፈጻጸሙም ቅንጅት በመፍጠር አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡
ሠላምን ለማስከበር የተደረሰው ስምምነት እንደ አገር ወሳኝና ተገቢ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ህዝብና አገርን ለስጋት የሚዳርጉና የሚጎዱ ግጭቶችን ማስቆም ጊዜ የማይሰጠውና ህገ መንግስታዊ ግዴታም ነው፡፡ ለሰው ህይወት መጥፋትና አካል መጉደል ፤ ለዜጎች መፈናቀልና ንብረት መውደም ምክንያት የሆነውን ግጭት ማስቆም አስፈላጊ ነው፡፡ የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ፤ ግጭትን የሚያባብሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፣ የተፈጠረውን ብሩህ ተስፋ ለማስቀጠል በፍቅርና አብሮነት ሕዝቡ እንዲተጋ፤ ከዚህ በተቃራኒው የሚፈጸሙ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን ለመከላከልም ይረዳል፡፡
ይህም ሆኖ ግን በዚህ ድርጊት የተሰለፉ አካላት የሠላሙን ጎዳና በመምረጥ ሂደቱን ለመለወጥና ለማስተካከል ቢተጉ አዋጭና ተመራጭ ነው፡፡ በግጭትና ሁከት የተሰለፋችሁ አካላት የያዛችሁት መንገድ አክሳሪና ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍላችሁ መሆኑን ተገንዝባችሁ ወደ ሠላሙ ጎዳና መቀላቀሉ ይበጃችኋል፡፡ ሠላምን በመጥላት አንዳችም ትርፍ እንደማይገኝ ካለፈው የጥፋት ታሪክ መማር ይቻላል፡፡ በግጭትና ሁከት ያተረፈም፤የተጠቀመም አካል የለም፤ወደ ፊትም አይኖርም፡፡ በግጭት ውስጥ ያለፉና በግጭት ውስጥ ያሉ የጎረቤትና የሩቅ አገራት ተሞክሮም ይህንኑ እውነታ ነው የሚያስረዳን፡፡ ስለሆነም ደማቁን የፍቅርና የይቅርታ ጥሪ በመቀበል በሠላሙ በር መመላለሱ ያዋጣል፡፡ መንግሥት የኃይል እርምጃ ለመውሰድ እስኪገደድ ድረስ ግጭትን በማራገብና በማቀጣጠል የጨለምተኝነት ጎዳና መጓዝ ውጤቱ ትልቅ ዋጋን ከማስከፈል የዘለለ አይሆንም፡፡ በግጭትና ሁከት ድርጊት በቅርበትም ይሁን በርቀት ከመሳተፍ መቆጠብ ይገባል፡፡
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ አክቲቪስቶች፣ጦማርያን አርቲስቶችና በተለያዩ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችም ግጭትን የሚቀሰቅሱ፣በዜጎች መካከል መቃቃርን የሚፈጥሩ ጽሑፎችና ኪነጥበባዊ ሥራዎችን ከማቅረብ መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡ የማይበጅ አመለካከትን በህዝብ ውስጥ ከመዝራት ስሜታዊ አባዜ መውጣት ያስፈልጋል፡፡ ህዝብን የሚያጣሉና የሚለያዩ የጥላቻ ጡቦችን ለመደርደር ከመሽቀዳደም ፣ የእርቅና የፍቅር ድልድዮችን ለመገንባት መጣደፍ ይሻላል፡፡
አገር ለልማት ስትተጋ የሁሉም ጥረትና የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡ በተለይም የአገሪቱን ኢኮኖሚ እየተፈታተነ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ የተጀመረውና አበረታች ውጤት እያስገኘ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ለማሳደግ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ግድ ይላል፡፡ በህገ ወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሬ ግብይት የሚያካሂዱና የሚያከማቹ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው ሊቆጠቡ ግድ ይላቸዋል፡፡ አገር በውጭ ምንዛሬ እጥረት እየታመሰች በየጓሮው የውጭ ምንዛሬ ንግድ ማጧጧፍ በአገርና በህዝብ ላይ መቆመር ነው፡፡ ስለሆነም የዚህ ተዋናዮች ህጋዊውን መስመር በመከተል በመንግሥት ለቀረበው ጥሪ ፈጣን ምላሽ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ኅብረተሰቡ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ግጭት ለማስነሳት የሚፈልጉ አካላትን ባለመተባበር ፊት ሊነሳቸውና ለሚመለከተው አካል በመጠቆም ህገ ወጥ ድርጊቱን ለማምከን የሚደረገውን ጥረት ማገዝ ይኖርበታል፡፡ ጊዜው አንድነት የሚሰበክበትና በተባበረ ክንድ ለለውጥና ልማት የሚተጋበት የመደመር ጉዞ እንጂ መከፋፈልና ጥላቻ የሚቀነቀኑበት አይደለም፡፡ ራስን ከህገ ወጥ ድርጊት በማራቅ ለአገር ሠላምና ልማት የሚበጁ ተግባራትን በማከናወን የዜግነት ግዴታን መወጣት ይገባል፡፡ ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ፤ኢኮኖሚያ ዕድገትን ለማፋጠን፤ የህዝቦችን አንድነት ለማጠናከር በሚረዱ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ያስፈልጋል፡፡ የሚያፋጁንን ሳይሆን የሚበጁንን፣የሚያለያዩንን ሳይሆን የሚያስተሳስሩንን፣የሚያራርቁንን ሳይሆን የሚያቀራርቡንን ጉዳዮች እያጎላን መጓዙ ነው የሚጠቅመን፡፡ Read More

ሰበር ዜና!! ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ዋለ |EBC

0

ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከብሄራዊ መረጃና ደህነት፣ ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር ሆኖ ህብርተሰቡን ማዕከል ባደረገ መልኩ በተከሄደው የጥቂት ቀናት ዘመቻ ገንዘቡ ከአገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ጥቂት ቀናት በጥናት ላይ ተመርኩዞ በተካሄደው ዘመቻ ከ1ሺህ በላይ የነፍስ ወከፍና የቡድን ጦር መሳሪያ እንዲሁም 80 ሺህ የሽጉጥና ክላሽ ጥይቶች ወደ አገር ሊገቡ ሲል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

ከገንዘቡ በተጨማሪ በህገ ወጥ ድርጊቱ ላይ የተሳፉ ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገባቸው መሆኑንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአገር ሊወጣ ሲል፣ የጦር መሳሪያው ደግሞ ወደ አገር ሊገባ ሲል መያዙ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጫና ለመፍጠርና አገራዊ አለመረጋጋትን ለመፍጠር ያለመ የተቀናጀ ስራ መኖሩን ተገንዝቦ ፖሊስ ጥልቅ ምርመራ እያረገ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

አሁንም ከፖሊስ ጎን ሆኖ የተለመደ ትብብር ማድረጉን እንዲቀጥልም ኮሚሽነር ዘይኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከዚህ በኋላም በተመሳሳይ መልኩ በጥናት ላይ የተመሰረተ እርምጃ መወሰድ እንደሚቀጥልም ተመልክቷል፡፡

ሪፖርተር፡ ጥላሁን ካሳ

በምሥራቅ ወለጋ የአራት ቀን ሬሳ አስነሳለው ብሎ መቃብር ያስቆፈረው ‘ነብይ’ በቁጠጥጥር ሥር ዋለ |BBC Amharic

0

አቶ በላይ ቢፍቱ የሊሙ ወረዳ ገሊላ ከተማ ነዋሪ ነበሩ። ባሳለፈነው ሰኞ ነበር በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ያለፈው።

ቤተሰብ ሃዘን ተቀምጦ ሳለ ጌታያውቃል አየለ የሚባል ግለሰብ ለሟች ቤተሰቦች የመጸሃፍ ቅዱሱን አላዛር ታሪክ ከነገራቸው በኋላ ሟቹ በላይን እንደሚያስነሳ ይነግራቸዋል።

ከዚያም በላይን ከሞት እንደሚያስነሳ የቤተሰብ አባላቱን ካሳመነ በኋላ በላይ ወደተቀበረበት ወደ ሙሉ ወንጌል የመቃብር ስፍራ ይዟቸው ሄደ።

በቤተክረስቲያኗ ቅጥር ግቢ የነበሩት የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ሰራተኛ የሆኑት አቶ ዲንሳ ደበላ ”ከመቃብሩ ስፍራ በላይ ከሞት ይነሳል የሚል ተደጋጋሚ ድምጽ ሰምቼ ምን እየተከናወነ እነደሆነ ለማጣራት ወደ ስፍራው ሄድኩ” ይላሉ።

እሳቸው እንደሚሉት ድርጊቱ የቤተክረስቲያኒቷን ስርዓት እንደሚጻረረ በምንገር ድርጊቱ እንዲቆም ሲያሳስቡ ከግለሰቦቹ ጥቃት ሊሰነዘርባቸው ሲል ሸሽተዋል።

ከዚያም ጌታያውቃል የተባለው ግለሰብ መቃብሩን አስቆፍሮ የሬሳ ሳጥኑን ከከፈተ በኋላ በተደጋጋሚ ”በላይ ተነስ” እያለ ሲጮህ ነበር።

በዚህ ብቻ የልተቆጠበው ይህ ግለሰብ የሬሳ ሳጥኑ ላይ ተዘርግቶ በመተኛት ‘ተነስ’ እያለ በተደጋጋሚ ድምጹን አሰማ።

እራሱን ነብይ እያለ የሚጠራው ይህ ግለሰብ ከላይ የተጠቀሰን ድርጊት ሲፈጽም የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ በርካቶች ሲቀባበሉት ውለዋል።

በመጨረሻም መልስ ያጣው ግለሰብ ”ምንም ማድረግ አይቻልም” ብሎ ከመቃብሩ ጉድጓድ ውስጥ ወጥቶ ሊሄድ ሲል ጉዳይን በአትኩሮት ሲከታተሉ የነበሩ የአከባቢው ሰዎች እና የቤተሰብ አባላት በግለሰቡ ድርጊት በመበሳጨታቸው ሊደበድቡት ተነሱ ሲሉ አቶ ዲንሳ ነግረውናል።

ዘግይቶ በአካባቢው የተገኘው ፖሊስ አቶ ጌታያውቃልን ከመደብደብ አትረፎት በቁጥጥር ስር አውሎታል። ”አሁን በቁጥጥር ስር ይገኛል” ሲሉ የሊሙ ወረዳ የፖሊስ አባል የሆኑት ኮማንደር ታደሰ አማኑ ነግረውናል።

”ግለሰቡ የፈጸመውን ድርጊት እያጣራን ነው። ነብይ ነኝ የሚለው ይህ ሰው በአካባቢው ያሉ የየትኛውም የቤተክረስቲያን አባል እንዳልሆነ አረጋግጠናል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ይህ ግለሰብ የወረዳው ጤና ቢሮ ባልደረባ ስለመሆኑም ከምንጮቻችን መረዳት ችለናል።BBC Amharic