Home Blog Page 224

Ethiopia | ኮማንድ ፖስት ማሳሰቢያ ሰጠ

0

ከሰሞኑ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዜጎችን የተረጋጋ ህይወት ለብጥብጥና ሁከት ለመዳረግ ያለመ መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገፆች አማካይነት መሰራጨቱን አስመልክቶ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ማሳሰቢያ መስጠቱን የደረሰን መረጃ ያመላክታል። ኮማንድ ፖስቱ ሆን ተብሎ ህገ ወጥ ቅስቀሳ በማድረግ የዜጎችን ሰላማዊ ህይወት ለማወክና ስጋት ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ያለምንም ስጋት መደበኛ ተግባሩን እንዲያከናውን ገልጿል። መንግስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት ሊደረጉ የማይገቡ ተግባራትን በማውጣት ዜጎች እንዲያውቁት ማድረጉ የተነሳ ሲሆን፥ መመሪያውን የተላለፈ ወይም የጣሰ ግለሰብ ላይ ኮማንድ ፖስቱ አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል መገለጹም ይታወሳል።

በመሆኑም የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ማስተጓጎልና ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብትን የሚገድቡ እንቅስቃሴዎች፣ የህዝብ መገልገያ ተቋማትን፣ የንግድ ስራዎች ወይም ሱቆችን፣ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማትን መዝጋት ወይም ምርትና አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረግ ኮማንድ ፖስቱ ባወጣው መመሪያ ተከልክሏል። ከዚህ ባለፈም ከስራ ቦታ ያለ በቂ ምክንያት መጥፋት ወይም ስራ ማቆምና ስራን መበደል፣ በህዝብና በመንግስት ተቋማት እንዲሁም በግል ንብረት ላይ በማንኛውም መንገድ ጉዳት ማድረስ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን በኮማንድ ፖስቱ ዝርዝር መመሪያ ላይ መስፈሩም የሚታወስ ነው። የህዝብና የዜጎች ሰላምና ጸጥታን ለማስከበር ሲባል ከኮማንድ ፖስቱ ፍቃድ ወይም እውቅና ውጭ ማናቸውንም ሰልፎችና የአደባባይ ስብሰባዎች ማድረግም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ የተከለከለ ነው ብሏል።

በትምህርት ቤቶችና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደቶችን የማወክ፣ አድማ ማድረግ፣ የትምህርት ተቋማትን መዝጋት፣ እንዲዘጉ ቅስቀሳ ማድረግ ወይም የትምህርት ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት ማድረስ የተከለከለ መሆኑን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር መመሪያ ተደንግጓል።

አድማና ህገ-ወጥ ተግባር መፈጸም ወይም እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ይፋዊም ሆነ ድብቅ ቅስቀሳ በማናቸውም በኩል ማድረግ ጽሁፍ ማዘጋጀት፣ ማተምና ማሰራጨት፣ ትዕይንት ማሳየት፣ በምልክት መግለጽ ወይም መልዕክትና በማናቸውም መንገድ መግለጽና ይፋ ማድረግ የተከለከለ መሆኑንም ተጠቅሷል። ፍቃድ ሳይኖር ማንኛውንም ህትመት ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባትና ወደ ውጭ ሃገር መላክ፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ፣ በጽሁፍ፣ በቴሌቪዥን በሬዲዮ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በሌሎች የግንኙነት ዘዴዎች መለዋወጥም የተከለከለ መሆኑ በመመሪያው ሰፍሯል። የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት፣ ዝውውርና ስርጭትን ማስተጓጎልም በጥብቅ የተከለከለ መሆኑም ይታወቃል።

ህግ አስከባሪ አካላትና የድርጅት ጥበቃዎች አስቸኳይ ጊዜ አዋጁና መመሪያውን ለማስፈጸም የራሳቸውንና የሰዎችን ህይወትና ንብረት በመጠበቅ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ሃይል ሊጠቀሙ እንደሚችሉም በመመሪያው ተጠቅሷል። በግልና የመንግስት ተቋማት ውስጥ አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝና ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ የህግ አስከባሪ አባላት በእነዚህ ተቋማት ውስጥ መግባት አስፈላጊ ከሆነም መቆየት እንደሚችሉ ዝርዝር መመሪያው ላይ በግልፅ ሰፍሯል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ለሚነዙ ውዥንብሮችና ቅስቀሳዎች ትኩረት ሳይሰጥ መደበኛ ህይወቱን እንዲመራና የዕለት ተዕለት ተግባሩን ያለስጋት እንዲያከናውን ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል።

ምንጭ፡ ኤፍ ቢ ሲ

Ethiopia |በመስሪያ ሰዓታቸው የሚዘጉት የከነማ መድሃኒት ቤቶች

0

Ethiopia |በመስሪያ ሰዓታቸው የሚዘጉት የከነማ መድሃኒት ቤቶች |Fana TV

ዮናታን ተስፋዬ ከእስር ተለቀቀ ፣ በአድማው ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ለመመጣት ተቸግሯል

0

የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዮናታን ተስፋዬ የእስር ጊዜውን ጨርሶ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት መፈታቱ እየተነገረ ነው። ይሁንና በኦሮሚያ ክልል እየተከናወነ ባለው የስራ ማቆም አድማ የመጓጓዣ አገልግሎት እንዲቋረጥ በማድረጉ፥ ወደ አዲስ አበባ መምጣት ያለመቻሉን እናቱ ወ/ሮ ሙጭት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቤተሰብ አባላቱም በዚሁ የመጓጓዣ አገልግሎት መቋረጥ ምክንያት ወደዝዋይ ሄደው ሊቀበሉት ያለመቻላቸውን ነው ወ/ሮ ሙጭት የሚያስረዱት።
BBC News Amharic

Sunday With EBS Mekuanent Melesse Live Performance

0

ድምፃዊ መኳንንት መልስ ቀሰው ነግሬደ (ጊዜው ጥሩ ነው) በእሁድን በኢቢኤስ/ Sunday With EBS Mekuanent Melesse Live Performance

Ethiopia: ፍልፍሉ ቺክ ቀጥሮ አስቂኝ ድራማ

0

Ethiopia: ፍልፍሉ ቺክ ቀጥሮ አስቂኝ ድራማ | ” Filfilu Chick Ketro” funny Ethiopian Drama

LTV | MUSIC – ከድምፃዊ ዲበ ኩሉ ታፈሰ ጋር

0

LTV | MUSIC – ከድምፃዊ ዲበ ኩሉ ታፈሰ ጋር / Entertaining Interview With Musician Dibekulu Tafese

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መፅደቅ በአገሪቷ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን እንደሚረዳ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተናገሩ

0

#EBC የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መፅደቅ በአገሪቷ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን እንደሚረዳ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተናገሩ፡፡

በድብቅ ቪድዮ እንዴት መቅረፅ እንችላለን ማንም ሳይባንንብን እንዴት?

0

በድብቅ ቪድዮ እንዴት መቅረፅ እንችላለን ማንም ሳይባንንብን እንዴት? ይህ አፕሊኬሽን ሲቀርፅ ምንም ነገር እንካን ምልክት አያሳይም እንዲሁም ማንኛውም አፕሊኬሽን እየተጠቀምን ዩቱብ እያየን ስልካችን እስክሪን ለራሱ ቢጠፋ መቅረፅ እንችላለን ትወዱታላቹ ከወደዳቹት ለሌላም ሼር ያድርጉ

Ethiopia:ግዜያችንን የሚቆጥብልን ለስልካችን አጠቃቀም ፈጣን የሚያደርግልን ምርጥ አፕ FastKey Launcher

0

Ethiopia:ግዜያችንን የሚቆጥብልን ለስልካችን አጠቃቀም ፈጣን የሚያደርግልን ምርጥ አፕ / FastKey Launcher

Ethiopia: አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ምላሽ ሰጡ

0

Ethiopia: አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ለፀደቀው ዐዋጅ የተሰጠው የድምፅ ስህተት ምላሽ ሰጡ