Home Blog Page 2

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ |Reporter

0

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለዓርብ ነሐሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ፡፡ የዕለቱ አጀንዳ ቀጣዩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) አዲስ ካቢኔ ማፅደቅ ነው፡፡

አቶ ታከለ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ከተሾሙት ከወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስና ከሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ጋር በመሆን ቀጣዮቹን የካቢኔ አባላት ሲመለምሉ ቆይተዋል፡፡

ምንጮች እንደጠቆሙት ምክትል ከንቲባው አብዛኞቹን የቀድሞ ካቢኔ አባላት በአዲስ ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ምርጫ ባለመካሄዱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዕድሜ ማራዘሚያ የሰጠው የአዲስ አበባ ምክር ቤት፣ በቋሚ ኮሚቴዎቹ አማካይነት ከአዲሶቹ ካቢኔ አባላት ጋር ተጠያቂነትን በሚመለከት ስምምነት ለመፈራረም ራሱን የቻለ ዝግጅት እያካሄደ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር በጀመረው የተጠያቂነት አሠራር ቅርፅ በአዲስ አበባ ይኸው አሠራር የሚጀመር ሲሆን፣ የካቢኔ አባላት የሚመሯቸው ቢሮዎችም ሆኑ የከተማው ሥራ አስፈጻሚዎች በሙሉ ከቋሚ ኮሚቴዎች ጋር ስምምነት ይፈጽማሉ ተብሏል፡፡

ይህ ስምምነት የሚያጠነጥነው እያንዳንዱ መሥሪያ ቤት በዕቅድ የያዛቸውን ሥራዎች፣ የኦዲት ሪፖርቶችና የምክር ቤት አባላት የሰጧቸውን አስተያየቶች ተግባራዊ መደረጋቸውን መመርመር ነው፡፡

በዚህ መንገድ መሄድ ያልቻለ ሥራ አስፈጻሚ ተጠያቂ የሚሆንበት አሠራር ይዘረጋል ተብሏል፡፡ በስድስቱ የከተማው ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎችና በሥራ አስፈጻሚዎች መካከል ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ስምምነት ቀን ባይቆረጥለትም፣ አዲሶቹ የካቢኔ አባላት ኃላፊነታቸውን ከተረከቡ በኋላ የሚካሄድ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚካሄዱ የካፒታል ፕሮጀክቶችም ሆኑ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት የነዋሪዎችን ፍላጎት ከማርካት ይልቅ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የተንሰራፉባቸው መሆናቸው ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከለ ሥልጣን በተረከቡበት ወቅት የከተማውን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ ሥራዎች ይከናወናሉ ማለታቸው ይታወሳል፡፡ Reporter

የቻይና መንግስት 29 ኢትዮጵያውያን በቻይና በዶክተሬት ዲግሪ እንዲማሩ ነጻ የትምህርት ዕድል መስጠቱን አስታወቀ |EBC

0

Image may contain: 10 people, people smiling, people standing and indoor

አብዛኞቹ ተማሪዎች በማህበራዊና በተፈጥሮ ሳይንስ የዶክተሬት ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ ነፃ የትምህርት እድሉ የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር በዲፕሎማሲ፣ ባህልና በኢኮኖሚ ረገድ ያለውን መልካም አጋርነት ያሳያል ብለዋል።

በአገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት እንቀጥልበታለን ምክንያቱም በአገሪቱ ልዩነትን የሚፈጥሩ ሌሎች ጎበዝ ተማሪዎችን እንልካለንና ብለዋል።

ሚንስትር ዴኤታው የቻይና ህዝብና መንግስት በኢትዮጵያ ልማት በተለይም በትምህርት ዘርፍ እያደረገች ላለው ድጋፍም አመስግነዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂያን አገራቸው በትምህርት ዘርፍ የአፍሪካ አገራትን ለማገዝ ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል።

በትምህርት ዘርፍ የሚደረገው ድጋፍ ጠቃሚ እና ትርጉም ያለው ስራ መሆኑንም በመጠቆም።

የዕድሉ ተጠቃሚዎች በአገራቱ ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚረዱም ተናግረዋል።

ምንጭ፡-EBC

ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ የ115 ሚሊዮን ፓውንድ ድጋፍ ለመስጠት ተስማማች | EBC

0

የብሪታንያ የአለም አቀፍ ልማት መምሪያ ከኢፌዲሪ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሁለት የተለያዩ የድጋፍ ስምምነቶችን በሁለቱ አገራት ስም አዲስ አበባ ላይ በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል፡፡

በመግባባያ ስምምነቱ መሰረት ከአጠቃላይ ስምምነቱ 80 ሚሊዮን ፓውንዱ ለስራ ዕድል ፈጣራ ፕሮግራም የሚውል ነው፡፡

ይህ መርሃ ግብር በተለይም ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በአገር ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ የውጭ አገራት ስደተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡

በዚህ መርሃ ግብር ይፈጠራል ተብሎ ከሚጠበቀው 100 ሺህ የስራ ዕድል ውስጥ 30 ሺህ ያህሉ ለስደተኞች ኮታ የተያዘ ነው፡፡

ሁለተኛው የ35 ሚሊዮን ፓውንድ ድጋፍ ደግሞ የኢትዮጵያን የታክስ ስርዓት ሽግግር መርሃ ግብር በማዘመን ስኬታማ ለማድርግ የሚው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ስምምነቱን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና የብርታኒያ አለም አቀፍ የልማት ኃላፊ የሆኑት ፔኒ ሞርዳውንት ተፈራርመዋል፡፡

ምንጭ፡ EBC

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የአማራ ክልል ትምህርት ቤቶች ይፋ ሆኑ| Amhara Mass Media

0

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የአማራ ክልል ትምህርት ቤቶች ይፋ ሆኑ፡፡
ባሕር ዳር፡ሐምሌ 24/2010 ዓ/ም(አብመድ)
• ደብረ ወርቅ-640
• ጣና ሀይቅ-625
• ባሕረ ጊዮርጊስ/ግንደወይን/-615
12ኛ ክፍል ከተፈተኑት ተማሪዎች ውስጥ 12 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት አስመዘግበዋል፡፡
ኦሮሚያ፣አማራ ክልልና አዲስ አበባ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ከአንድ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
ሰጠኝ እንግዳው ከአዲስ አበባ

በማርስ በፈሳሽ ውሀ የተሞላ ሀይቅ ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች እስታወቁ |Amhara Mass Media

0

ቀዩዋ ፕላኔት ተብላ በምትጠራዉ ማርስ በፈሳሽ ውሀ የተሞላ ሀይቅ ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች እንዳስታወቁ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

20 ኪሎ ሜትር ያህል ይሸፍናል የተባለው ሀይቅ በማርስ ደቡባዊ ዋልታ ቀዝቃዛ ክፍል ነው የተገኘው፡፡ ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በማርስ ከርሰ ምድር ለተወሰኑ ወቅቶች ብቻ የሚቆዩ እና የሚፈሱ አነስተኛ የውሀ አካላት መኖራቸወን ይፋ አድርገው ነበር፡፡

ሆኖም ማርስ የሳሳ ከባቢ አየር ስላላት በሚፈጠረው ከፍተኛ ቅዝቃዜ የውሀ አካላቱ በበረዶ ስለሚሸፈኑ ለመለየት አዳጋች ነበር፡፡
ይህኛውን ጥናት ለየት የሚያደርገው በፕላኔቷ ላይ በሁሉም ወቅቶች ሳይነጥፍ የሚቆይ ሀይቅ መኖሩን ማረጋገጥ መቻሉ ነው፡፡

ማርሲስ በተሰኘችው ሳተላይት አማካኝነት የተገኘው ሀይቅ በጣም ሰፊ የሚባል አለመሆኑን እና ጥልቀቱን በትክክል ማስቀመጥ እንዳልተቻለ ሲገመት ከአንድ ሜትር በላይ ሊሆን እንደሚችል ግን የጥናት ቡድኑ መሪ ፕሮፌሰር ሮበርቶ ኦርሴ ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ እንዳሉት በማርስ የተገኘዉ ሀይቅ በምድራችን ዋልታዎች ፣በከርሰ ምድር አለት ውስጥ እና በበረዶ ግግር መካከል እንደሚገኘው ከፊል በረዶ አይደለም፡፡

ይልቁንም በማርስ የተገኘው ሙሉ በሙሉ ፈሳሽ ሀይቅ ነዉ፡፡ ማርስ ህይወት ላላቸው አካላት መኖሪያነት ምቹ አለመሆኗ በጥናቶች ቢታወቅም ፈሳሽ የውሀ አካል መገኘቱ ህይወት ያላቸው ፍጡራንን ለማግኘት የሚደረገውን ጥናት ያግዛል ተብሏል፡፡

ለጊዜው ግን ጥናቱ በማርስ ህይወት ያላቸው አካላት መኖራቸውን የሚያሳይ ፍንጭ አለመገኘቱ ተገልጿል፡፡

የሀይቁን የውሀ ኬሚካላዊ ባህሪ እና የሙቀት መጠን ለመመርመር ከፍተኛ ቴክኖሎጂ እንዲሁም ገንዘብ ስለሚጠይቅ በዘርፉ ምርምሩን ለመቀጠል ችግር መፍጠሩ ተጠቁሟል፡፡
በቢንያም መስፍን

‹‹በድብቅ የዶላር ንግዱ እስከ 4መቶ ሺህ ገንዘብ ከሰርኩ ፡፡›› አንድ ግለሰብ ከባህር ዳር |Amahara Mass Media

0

‹‹በድብቅ የዶላር ንግዱ እስከ 4መቶ ሺህ ገንዘብ ከሰርኩ ፡፡›› አንድ ግለሰብ ከባህር ዳር

‹‹አሁን ላይ በቀን እስከ 100 ሺ ዶላር ባንኮቹ ላይ እየተመነዘረ ነው፡፡››በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባህር ዳር ዲስትሪክት

ባሕር ዳር፡ሐምሌ 24/2010 ዓ/ም(አብመድ) የጓዳ (ጥቁር) ዶላር ምንዛሬ ‹‹ቁሟል›› ሊባል የሚችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን የባህር ዳር ንግድ ባንክ ዲስትሪክት አስታወቀ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ ከቀረበበት ዕለት ጀምሮ ህብረተሰቡ ያስቀመጠውን ዶላር ወደ ባንክ በመውሰድ እየመነዘረ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባህርዳር ዲስትሪክት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ አለማየሁ እንደተናገሩት አሁን ላይ በጓዳ ገበያው እና በባንኮች መካከል ያለው የምንዛሬ መጠን ተመሳሳይ ነው፡፡

ህብረተሰቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ በመቀበል ወደ ባንኮች እየመጣ ነው ያሉት አቶ ዮሴፍ የጓዳ (ጥቁር) ገበያውም ቆሟል ሊባል በሚችልበት ደረጃ መድረሱን ነግረውናል፡፡
ዶላር ፣ፓውንድ፣ዩሮ ፣ድርሃም እና ሪያል ህብረተሰቡ በብዛት ወደ ባንኮቹ እየወሰደ እየመነዘራቸው ያሉት የገንዘብ ዓይነቶች ናቸው፡፡

አሁን ላይ በቀን እስከ 100 ሺ ዶላር በባንኮቹ እየተመነዘረ መሆኑን ያስረዱት ዋና ስራ አስኪያጁ ከዚህ በፊት በቀን ከአንድ ሺ በላይ የውጭ ሃገር ገንዘብ ወደ ባንኮቹ አይመጣም ነበር ብለዋል፡፡

ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አንድ የድብቅ (የጥቁር) ገበያ የዶላር ምንዛሬ ነጋዴ እንደነገረን ቀደም ብሎ ለዚሁ ገበያ በርከት ያለ ዶላር ገዝቶ ነበር፡፡ አሁን ግን ድብቅ የዶላር ምንዛሬ ዋጋ በመቀነሱ አራት መቶ ሺ ብር ከስሯል፡፡

የድብቅ ገበያው የምንዛሬ ዋጋ ከባንኮቹ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑም ህብረተሰቡ ወደ በባንኮች መገልገልን መርጧል ነው ያለው ወጣቱ፡፡

ዛሬ ሐምሌ 24/2010 ዓ.ም የአንድ ዶላር ዋጋ 27 ብር ከ26 ሳንቲም እየተመነዘረ ነው፡፡ እንደ አቶ ዓለማየሁ ገለጻ በባህር ዳር ዲስትሪክት ቅርንጫፍ ባሉ 81 ባንኮች በሁለት ሳምንታት ጊዜ ብቻ አንድ ሚሊየን 130 ሺ 845 ዶላር ከህብረተሰቡ ተሰብስቧል፡፡

የጓዳ የዶላር ምንዛሬ ህጋዊ ነጋዴዎችን ከመጉዳት ባለፈ ኑሮን በማስወደድ በእያንዳንዱ ሰው ህይዎት ላይ ከፍተኛ ችግር ይፈጥራል፡፡ በመሆኑም በድብቅ ገበያ መመንዘር ሃገራዊ ኪሳራ እንጂ ትርፍ እንደሌለው በመረዳት ህብረተሰቡ ወደ ህጋዊ ምንዛሬ መምጣቱን እንቀጥል ስራ አስኪያጁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ምስጋናው ብርሃኔ

አዲስ ነገር ሐምሌ 23 2010 / What’s New July 30 2018

0

የኤርትራና የጂቡቲ ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ለመሳተፍ ኢትዮጵያ ዝግጅነቷን ገለጸች።

ኢትዮጵያ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያሉ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ለመሳተፍ ዝግጁነቷን የገለጸችው የኤርትራና ሶማሊያ ጉዳይ የሚከታተለው ኮሚቴ ባለፉት ጊዚያት በኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ ጉብኝት ካደረገ በኋላ የ120 ቀናት ሪፖርቱን በትናንትናው ዕለት ለጸጥታው ምክር ቤት ባቀረበበት ውቅት ነው ተብሏል።

በዚህም ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ለ2 አስርት አመታት የዘለቀውን ቅራኔ በመፍታት በቀጠናው አካባቢ ሰላም እንዲሰፍን እየተሰራ ያለውን ተግባር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ክብር ሊሰጠው እንደሚገባ የጸጥታው ምክር ቤት ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በፈንጆቹ ሃምሌ 9 በሁለትዮሽ የሰላም አጋርነት ላይ ስምምነት መፈራረመቸውና በተመሳሳይ መልኩ የኤርትራና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት በሳለፍነው ቅዳሜ መፈራረማቸውን የኮሚቴው ሊቀመንበር የሆኑት አምባሳደር ኬራት ኡማሮቭ አድንቀዋል።

ከፈረንጆቹ መካቢት 14 አስከ ሃምሌ 30 ኮሚቴው ውጤታማ ስራ የሰራባቸው ጊዚያት ሲሆኑ፥ በኢትዮጵያ፣ ጂቡቲና ሶማሊያ ውይይቶች መካሄዳቸውንም ኮሚቴው አስታውቋል።

በቀጠናው ምልከታውን ያከሄደው ኮሚቴው አሚሶም ከሶመሊያ ከመውጣቱ በፊት ሶማሊያ የአካባቢውን ጸጥታና ደህንነት በረሷ አቅም ለመወጣት የሚያስችላት ደረጃ ላይ መድረስ እንዳለባት አመላክቷል።

አሁን ላይ ሶማሊያ የአካባቢውን የጸጥታና የደህንነት ጉዳይ በራሷ አቅም ለመቆጣጠር የምትችለበት ደረጃ ላይ ያለመድረሷ የተገለጸ ሲሆን፥ የአሚሶም ኃይል የቆይታ ጊዜውን እስከ ፈረንጆቹ ግንቦት 31፣ 2019 ማራዘሙ ነው የተገለጸው።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደ ተቀዳ አለሙ እንደገለጹት ላለፉት 20 ዓመታት በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከላል የዘለቀውን ቅራኔ በመፍታት አዲስ ምዕራፍ ተክፍቷል።

የሁለቱን ሀገራት የግጭት ምዕራፍ ከመዝጋት ባለፈም ሀገራቱ ለሁለቱ ሀገራት የህዝብ ለህዘብ ህዝብ ግንኑነት መሻሻልና ቀጣይነት ቁርጠኛ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በዚህም ያለፉት 2 ሳምንታት ታሪካዊ መሆናቸውን የገለጹት አምባሳደር ተቀዳ ሁለቱ ሀገራት ለሰለማዊ ግንኙነታቸው የወሰዱት ቁርጠኝነት ለቀጠናው ሀገራት ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ ድርሻ ያለው ሲሆን፥ ለቀጠናው ሀገራትም በአርያነት የሚወሰድ ነው ብለዋል።

ለዚህም ከኢትዮጵያና ኤርትራ ሰላመዊ ግንኙነት በኋላ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሚስተር ሞሃመድ አብዱላሂ(ፋርማጆ) ከጥቂት ቀናት በፊት በኤረትራ ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው አንዱ ማሳያ መሆኑን ነው አምባሳደር ተቀዳ የተናገሩት።

ኢትዮጵያ የኤረትራና የጅቡቲ ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታና በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የበኩሏን ሚና እንደምትወጣም አስረድተዋል።

ለዚህም በማንኛውም መንገድ የሁለቱ ሀገራት ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ የሚፈታበትን ሁኔታ ለማገዝ ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ነው የተናገሩት። FBC

ሰመጉ የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል መብት ጥሰቶችን የሚመለከት ሪፖርት አወጣ |BBC Amharic

0

የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን የሚያሳይ ሪፖርት ይፋ አደረገ።

ተቋሙ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በሁለቱ ክልሎች መካከል በነበረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን እንደሚበልጥ ዋቢ ጠቅሷል።

ተቋሙ በልዩ መግለጫው ላይ ወደ 30 በሚጠጉ የሁለቱ ክልል አጎራባች ወረዳዎች በተደረገ ማጣራት ከ500 በላይ ዜጎች መገደላቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ለአካል ጉዳት እንደተዳረጉ አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ የአስገድዶ መድፈር እና ደብዛ የማጥፋት ወንጀሎች በሁለቱም ክልሎች መፈፀማቸውን ጠቁሟል።

ሰመጉ የተጎጂዎች ቁጥርና ጉዳት መጠኖችን በዘረዘረበት ባለ 55 ገፅ ልዩ ሪፖርቱ ፤ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ፣ለወደፊቱም እንዳይደገሙ የመከላከል ርምጃ እንዲወሰድ ፣ጉዳት የደረሰባቸው ካሳ እንዲከፈላቸውና ተጠያቂዎችም ለህግ እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርቧል። BBC Amharic

ማንነታቸው ያልታወቀ 40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ |BBC Amharic

0

ማንነታቸው ያልታወቀ 40 የታጠቁ ወታደሮችን ይዞ ትግራይ ክልል የገባ አንቶኖቭ አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ።

ምንጮች ለቢቢሲ እንደገለፁት በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት የታጠቁ ወታደሮች ተልዕኮና ማንነታቸው ባይታወቅም ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ አመልክተዋል።

ከሁለት ቀናት በፊት ከሱዳን በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ የተጠረጠረው አንቶኖቭ አውሮፕላንና አሳፍሯቸው የነበሩት 40 የታጠቁ ወታደሮች በመቀሌው የአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ መያዛቸውን የክልሉ ደህንነት ምንጮች በአካባቢው ለሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ገልፀዋል።

ምንጮቹ ጨምረው ወታደሮቹ አንቶኖቭ ተብሎ በሚታወቀው ግዙፍ አውሮፕላን በአሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ በድንገት ያረፉት በስህተት መሆኑን ገልፀው፤ የክልሉ ፖሊስ ጉዳዩን እየመረመረው እንደሚገኝ ተናግረዋል።

“የእስር ማዘዣ ወጥቶብኝ ነበር” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ |BBC Amharic

0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የሚገኙ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን በትልቅ መሰብሰቢያ ውስጥ አግኝተው ከነጋገሩ በኋላ በተዘጋጀ የእራትና የውይይት መረሃ ግብር ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ባለፉት አራት ዓመታት እንቅልፍ ተኝተው እንደማያውቁ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለፉ አስታውሰው በተለይ ከአራት ወራት በፊት የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው እንደነበር ተናግረዋል።

ከየትኛው ወገን እንደመጣ በግልፅ ባይናገሩም ከሀገር እንዲወጡ የሚያስገድዱ ጫናዎች እንደነበሩም ጠቁመዋል። “እኛም አንወጣም ብለን እዚያው የሚመጠውን ሁሉ ለመጋፈጥ ቆርጠን ቆይተናል ምክንያቱም ከሃገር የወጡ አልተመለሱም። ለዚህም ነው እዚህ ቦታ ላይ ሊደርስ የቻለው” ብለዋል።

በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከታዳሚው ለቀረቡላቸው የተለያዩ ወቅታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

የሶማሌ ክልልን በተመለከተ

በኢትዮጵያ ያሉት ሶማሌዎች ብቻ ሳይሆን ሞቃዲሾ ያለውም ጭምር ዴሞክራሲን እንዲተገብርና ከኢትዮጵያዊያንና በተለይ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ተሳስሮ መኖር አለበት ብለን በጽኑ እናምናለን በማለት ጀምረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ክልሉ መሪ ያስፈልገዋል፤ ክልሉ የልብ አንድነት ያስፈልዋል። ብዙዎቻችሁ ላታስተውሉት ትችላላችሁ ግን አፍሪካ በብዙ ጅብ መንግሥታት የተያዘች አህጉር ናት። እነዚህን መንግሥታት ከጎረቤት አስቀምጠን ኢትዮጵያ ላይ ዴሞክራሲ፤ ኢትዮጵያ ላይ ሰላም ማምጣት አይቻልም።

አፍሪካ የሚገባትን ክብር እንድታገኝ በጋራ መስራት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ በቂ ጭንቅላት አላት፤ 100 ሚሊዮን ምርጥ ጭንቅላት። ይህንን በማውጣት መስራት ያስፈልጋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም የሶማሌ ክልልን በተመለከተ በመንግስት በኩል ሪፎርም እየሰራ እንደሆነና ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ ጠይቀዋል።

በኦሮሞና በሶማሌ መካከል የተነሳውን ግጭት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ “ኦሮሞና ሶማሌ አንድ ቤተሰብ ናቸው፤ ስለዚህ ማንም ምንም አለ አብሮ ተጋግዞ መስራት ብቻ ነው የሚያዋጣው ብለዋል።”

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነትን በተመለከተ

”በመጀመሪያ ትኩረተ የሰጠነው ዋነኛው ነገር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር ላይ ነው። ለዚህም ነው በፍጥነት የአውሮፕላን ጉዞ ያስጀመርነው፤ የሚያገናኙንን መንገዶች እየጠገንን ያለነው። ስለዚህ ህዝቡ ተገናኝቶ ሰላሙን መመስረት ከቻለ መንግሥት ደግሞ ይከተላል ማለት ነው።”

”እንኳን ለመታረቅ ለመዋጋትም ከዚህ በፊት ውክልና አልሰጠንም። ስንዋጋም ሃገር የሚመራው ጠቅላይ ሚኒስትር ተዋጉ ሲል ተዋጋን እንጂ በውክልና አልተዋጋንም። የትግራይን ህዝብ ሳናካትት ምንም አይነት ለውጥም ሆነ እድገት ማሳካት አንችልም፤ አንፈልግምም።”

“ከትግራይ ህዝብ ውጪ ኢትዮጵያን የመቀየር ሃሳብ የለንም። ህዝቡ ያሳዝነናል፤ ህዝቡ ይቆረቁረናል። የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይ ጉዳይ ግድ አይሰጠውም ማለት አንችልም ምክንያቱም በባድመ ጦርነት ከማንም በላይ የሞቱት የኦሮሚያ ልጆች ናቸው።”

የሰላሙ ጉዳይ ለህዝባችን ስለሚጠቅም፣ የኤርትራ ህዝብ የሰላም ህዝብ ስለሆነ፣ የትግራይ ህዝብ ደግሞ የሚጠቀመው ከዚህ ሰላም ስለሆነ ሌላውን ትተን አንድ ሆነን እንስራ የሚለውን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ፀጉረ ልውጦች እነማን ናቸው?

“ፀጉረ ልውጦች የተወሰኑ የአንድ ብሄር ተወላጆች ናቸው ብሎ ማሰብ በመሰረቱ የተሳሳተ ነው” በማለት የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የትግራይ ህዝብ ኦሮሚያ ወይም አማራ ክልል ውስጥ ፀጉረ ልውጥ ሊሆን አይችልም።”

“ኦሮሚያ ውስጥ ትግሬም ይሁን አማራ፤ ወላይታም ይሁን ጉራጌ፤ ህዝቡ ማንንም አቅፎ ለማኖር ፈቃደኛ ነው። እንደውም እኔና የወከልኩት ኦህዴድ ብዙ ችግር አለብን። የኦሮሞ ህዝብ ግን አቃፊ ነው። በእኛ መነጽር፤ በእኛ ልክ ህዝቡን አትለኩት። ህዝቡ እንደእኛ አይደለም፤ ህዝቡ ከእኛ የላቀ ብስለት ያለው ነው።”

“ፀጉረ ልውጥ ያልኩት በፍጹም አንድን ቡድን በሚገልጽ መልኩ ሳይሆን፤ የሚሰማሩ ሃይሎች ስለነበሩ መረጃው ስላለኝ ነው እንጂ የሆነ ቡድን ፀጉረ ልውጥ ሌላኛው ደግሞ ንጹህ ለማለት አይደለም። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ውጥረት ማንኛውም ነገር ለፖለቲካዊ ጥቅም ሊውል ይችላል።”

ባለፉት 27 ዓመታት የተሰራው ጥፋት ወይስ ልማት?

ያለፉት 27 ዓመታ ብዙ ቆሻሻ ነገር የተሰራበት ዘመን ነው። ልማት ማለት አስፓልት፤ ልማት ማለት ኮንዶሚኒየም የሚመስላቸው ሰዎች አሉ። መሰረተ ልማት ያለ ውስጣዊ ሥርዓት ምንም ጥቅም የለውም። ምክንያቱም እርስ በእርሱ የማይነጋገር ህዝብ፤ እርስ በእርሱ የማይግባባ ህዝብ ፈጥረን ስናበቃ አስፓልት ሰርተንልሃል የምንል ከሆነ ተገቢ አይደለም።

ኢትዮጵያ ውስጥ ለተገኘው ልማት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተገኘው ሰላም ባለቤቱ ህዝብ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ለጠፋው ጥፋት ግን ተጠያቂው መንግሥት ነው። ጥሩ ነገር ሲሰራ ሃላፊነት የምንወስድ፤ ጥፋት ሲጠፋ ደግሞ የምንሸሽ አክራሪዎች አይደለንም እኛ፤ መንግሥት ነን። እስከ ዛሬ ለጠፉ ጥፋቶች በሙሉ ኢህአዴግ እንደ መንግሥት ሃላፊነቱን ወስዶ ህዝቡንም ይቅርታ ጠይቋል።

ይሄ ሁሉ ግን በይቅርታ ብቻ የሚያልፍ አይደለም። ባለፉት 27 ዓመታት ለገረፍናችሁ፣ ላባረርናችሁ፣ ላስቸገርናችሁ ሰዎች እኔ እንደ ኢህአዴግ ከልብ ይቅርታ እጠይቃችኋለው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። BBC Amharic