SHARE

የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን የሚያሳይ ሪፖርት ይፋ አደረገ።

ተቋሙ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በሁለቱ ክልሎች መካከል በነበረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን እንደሚበልጥ ዋቢ ጠቅሷል።

ተቋሙ በልዩ መግለጫው ላይ ወደ 30 በሚጠጉ የሁለቱ ክልል አጎራባች ወረዳዎች በተደረገ ማጣራት ከ500 በላይ ዜጎች መገደላቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ለአካል ጉዳት እንደተዳረጉ አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ የአስገድዶ መድፈር እና ደብዛ የማጥፋት ወንጀሎች በሁለቱም ክልሎች መፈፀማቸውን ጠቁሟል።

ሰመጉ የተጎጂዎች ቁጥርና ጉዳት መጠኖችን በዘረዘረበት ባለ 55 ገፅ ልዩ ሪፖርቱ ፤ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ፣ለወደፊቱም እንዳይደገሙ የመከላከል ርምጃ እንዲወሰድ ፣ጉዳት የደረሰባቸው ካሳ እንዲከፈላቸውና ተጠያቂዎችም ለህግ እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርቧል። BBC Amharic

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here