SHARE

አጤ ቴውድሮስ በመቅደላ ሲወድቁ ከሁለተኛ ባለቤታቸው እቴጌ ጥሩወርቅ የሚወለደው ልዑል አለማየሁ እድሜው ስምንት ብቻ ነበር፡፡ራሳም ለጄኔራል ሜርዌዘር በላከው ወታደራዊ የሚስጥር መልዕክት የዘውዱን ወራሽ አግኝቼዋለሁ አለ፡፡ ልዑል አለማየሁም ከእናቱ እቴጌ ጥሩወርቅ ጋር በእንግሊዞች እጅ ወደቀ፡፡ጄኔራል ናፒር ከእቴጌ ጥሩወርቅ(የደጃች ውቤ ልጅ) ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት አጤ ቴውድሮስን በቅርበት ያውቃቸው ለነበረው እና አማርኛን አቀላጥፎ ለሚናገረው ካፒቴን ጄ.ሲ. ስፒዲ ተሰጠ፡፡ስለ ስፒዲ ብዙ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም ከአውስትራሊያ የናፒርን የመቅደላ ዘመቻ እንዲቀላቀል እንደተላከ ይነገራል፡፡ናፒርም አማርኛን አቀላጥፎ የሚናገር ሰው በማግኘቱ ደስተኛ ሳይሆን አይቀርም፡፡

አጤ ቴውድሮስ ልጃቸው እንግሊዝን እንዲጎበኝ ከፍተኛ ምኞት እንደነበራቸው የልዑል አለማየሁን ታሪክ የፃፉ እንግሊዛውያን ይናገራሉ፡፡እነ ናፒር ልዑል አለማየሁ ከእናቱ እቴጌ ጥሩወርቅ፤ከመምህሩ አለቃ ዛራት የእናቱ አጃቢ ገብረመድህን ጋር ሆኖ ከሃገሩ እንዲወጣ አደረጉ፡፡በመንገድ ላይ እናቱ እቴጌ ጥሩወርቅ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡በመጨረሻዋ የህይወታቸው ቅፅበት ግን ስፒዲ ልዑል አለማየሁን እንደ አባት ሆኖ እንዲያሳድገው ቃል አስገቡት፡፡በአጭር ጊዜ ልዑል አለማየሁ አባቱንም እናቱንም በሞት ተነጠቀ፡፡ወደማያውቀው ሀገርም እንዲሰደድ ሆነ፡፡የስዊዝ ካናልን እንደተሸገሩ የልዑል አለማየሁ መምህር እና አጃቢ ጠፉ፡፡ጄኔራል ናፒር ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ሳያደርግ አልቀረም፡፡ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አንድም የሚያውቀው ሰው በአጠገቡ ያልነበረው ልዑል አለማየሁ ከስፒዲ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መሰረተ፡፡ልዑሉ ከፍተኛ ሀዘን እና ጭንቀት ነበረበት፤ለመተኛት ይቸገራል፡፡ምናልባትም በመቅደላ የተመለከተው ሽብር የእናቱ እና አባቱ ሞት የፈጠረበት ሀዘንም እጅጉን ሳይከብደው አልቀረም፡፡ንግስት ቪክቶሪያ ስፒዲ ነገረኝ በማለት በለት ማስታወሻዋ ላይ “that the poor child has a recollection of the horrid massacre of captives by his father’s orders and having heard their shrieks” ስትል አስፍራለች፡፡

እንግሊዝ እንደ ደረሱ ስፒዲ ወደሚኖርበት ኢዝል ኦፍ ዊት ይዞት ሄደ፡፡ንግስት ቪክቶሪያ የልዑል አለማየሁን መያዝ ከሰማች ጀምሮ የተለየ ፍላጎት አሳድራነበር እና እንደ እናት እንክብካቤ እዲደረግለት ትዕዛዝ ሰጥታ ነበር፡፡ንግስት ቪክቶሪያ ኢትዮጵያዊውን ልዑል እጅግ ወዳው ስለነበር በተደጋጋሚ ወደ ቤተምንግስት ታስጠራው ነበር፡፡የግል ማስታወሻዋ ልዑሉን ማየት የፈጠረላትን ስሜት እንዲህ ይናገራል፡፡”just after lunch on saw the little Alamayou in his pictures in Abyssinian dress, gave the dear little boy a watch and chain.”

ካፒቴን ስፒዲ በህንድ ጦር ሰራዊት በሚያገለግልበት ወቅት ልዑል አለማየሁ አብሮት ተጉዟል፡፡በህንድ በነበረበት ወቅት ዋና ተምሮም ነበር፡፡እንደ ስፒዲ አባባል የባህር ዳርቻ የአየር ጠባይ ለልዑሉ የተመቸ በመሆኑ ደስተኛ እና ቀልጣፋም ሆነ፡፡ልዑል አለማየሁ በእንግሊዝ እንክብካቤ ቢበዛለትም ሙሉ ህይወቱን ደስተኛ ሆኖ የኖረ አይመስልም፡፡በተለያዩ ጊዜያት ከንግስቷ በመጡ ትዕዛዞች የመኖሪያ አካባቢው ይቀያየር ነበር፡፡

I hope you are quite well. I am sorry to say that Mr. Jex-Blake will not let me come to see the match. I have had a letter from Captain Speedy he says he went to India to some of the brave men from here and before he went to fight the Chinese, he asked the Raga of Caroot to ask them if they could have peace but they would not listen and so the Raga told CAPTAIN Speedy to go and take their forts and Captain Speedy and a hundred men went and took six of their forts and mud stockades and Captain Speedy said that the Chinese put sharp bamboo spikes and poisoned them and so the Malays were afraid to go near the forts, but the Indians did not care because they wore boots. What does Sir Stafford Northcote say about my going into the modern? I am going in for a junior race and I am getting on very well in my class.
I May get the prize I am working very hard. If I stay at Cheltenham I will get my promotion but I should like to know what Sir Stafford Northcote says about it.’
ከላይ ያነበብነው ከልዑል አለማየሁ ደብዳቤዎች አንዱን ነው

ልዑል አለማየሁ በእንግሊዝ በተማረባቸው ትምህርት ቤቶች የነበሩ መምህራን ሁሉ መልካም ወዳጆች ሆነውለታል፡፡እርሱ ግን ከትምህርት ይልቅ ለስፖርት የተሻለ ፍቅር ነበረው፡፡እግር ኳስ እና ራግቢም ይጫወት ነበር፡፡መምህራኑ ወታደራዊ ሳይንስ እንዲያጠናም ግፊት አድርገዋል፡፡እናም እ.ኤ.አ. በመስከረም 1878 ወደ ሳንድረስት ወታደራዊ ትምህርት ቤት ካለ ፈተና እንዲገባ ተደረገ፡፡በወታደራዊ ትምህርት ቤት ደስተኛም ሆነ ውጤታማ አልነበረም፡፡እናም ለእረፍት እንደወጣ አልተመለሰም፡፡አለማየሁ ከኢትዮጵያ ሁለት ደብዳቤዎች ደርሰውት ነበር፡፡አንዱ ከእናቱ እናት ወይም ከአያቱ ሲሆን የሁለተኛው ደብዳቤ ላኪ ማንነት አይታወቅም፡፡ሁለቱም ደብዳቤዎች የአለማየሁን መመለስ የሚናፍቁ ነበሩ፡፡

እ.ኤ.አ. በኖቬምበር 14 1879 በጥቂት ቀናት ህመም ከዚህ አለም በሞት ሲለይ እድሜው 19 ብቻ ነበር፡፡በንግስቷ ፈቃድ በዊንድሶር የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተመቅደስ የቀብር ስነስርዓቱ ተፈፀመ፡፡የኢትዮጵያ ሚሊኒየም ሲከበር የልዑል አለማየሁን አፅም ወደ ኢትዮጵያ ለማስመጣት ጥረት ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም ስኬታማ አልሆነም፡፡ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ የተወለደው ሚያዝያ 16, 1853 ነበር፡፡
የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ
‪#‎ሁኔአቢሲኒያ‬
ምንጭ አጤ ቴዎድሮስ በጳውሎስ ኞኞ፣ ሸገር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here