SHARE

አጫጭር ቀልዶች

ሚስት( ትደውልና) የማትረባ! ደደብ! የት አባክ ነው ያለከው?
-ባል፦ ፒያሳ ነኝ!
-ሚስት፦ እዛ ምን ትሰራለሀ?!
-ባል፦አንዴ ትዝ ካለሽ የሆነ ወርቅ ቤት አልጎበኘንም?
-ሚስት፦ አስታወስኩት ውዴ
ባል፦ የወርቅ ሀብል አይተሽ ወደድኩት ስትይ ገንዘብ ሳገኝ
እገዛልሻለው አላልኩም?
ሚስት፦አዎ የኔ ፍቅር.
ባል፦ ወርቅ ቤቱን አወቅሽው?
ሚስት፦አዎ ወለላዬ
ባል፦ከእሱ አጠገብ ያለው ግሮሰሪ ነኝ

የውሸታሞች ሙግት
አንደኛው ውሸታም፤
“የዛሬ 10 ዓመት አባቴ በህንድ ውቅያኖስ ላይ በመርከብ
ሲንሣፈፍ የእጅ ሰዓቱ ወድቆበት ከ10 ዓመት በኋላ ሲመለስ
በዋና ውኃ ውስጥ ገብቶ ሲፈልግ ሰዓቱ ምንም ሳይሆን
እየሠራ አገኘው ይለዋል”
ሁለተኛው ውሸታም፤
“ይገርምሃል የኔም አባት በዚሁ ውቅያኖስ ላይ ሲንሳፈፍ ወድቆ
ከ10 ዓመት በኋላ ምንም ሳይሆን በሕይወቱ ዋኝቶ
ወጣ፡፡”
አንደኛው ውሸታም፤
“እንዴት ያንተ አባት ሳይሞቱ ውኃ ውስጥ ሊኖሩ ቻለ፡፡ደግሞስ
ምን እየሠሩ ይሕን ያህል ዓመት ቆዩ” ብሎ ይጮህበታል፡፡
ሁለተኛው ውሸታም፤
“ውኃ ውስጥ እንኳን ሳይሆን አሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ነው
የቆዬው፣ ብቻ አንዳንድ ጊዜ ያንተን አባት ሰዓት እንዳይቆም
እየወጣ ይሞላ ነበር ሲል መለሰለት፡፡
————— ——
Round 2
አንደኛው ውሸታም፤
“የኔ አባት በርሻው ቦታ ላይ አውሮፕላን የሚያህል ጥቅል
ጐመን አምርቶ አንደኛ ወጣ፡፡
ሁለተኛው ውሸታም፤
“የኔም አባትኮ በጋራዣችን ውስጥ ትልቅ አፍሪካን የሚያህል
ብረት ድስት አምርቶ ተሸለመ፡፡”
አንደኛው ውሸታም፤
“እንዴት! አፍሪካን የሚያህል ብረት ድስት ምን ያደርግላቸዋል?
ብሎ ጠየቀው፡፡
ሁለተኛው ውሸታም፤
“ታዲያ! ያንተ አባት ጥቅል ጐመን በምን ይቀቀላል ሲል
መለሰለት፡፡”

እሷ: ስንጋባ ጫት መቃምህን ታቆማለህ.
እሱ: እሺ
እሷ: ሲጋራም ማጨስ አትችልም
እሱ: እሺ
እሷ: የሰካራም ሚስት እንድባልም አልፈልግም ስለዚህ
መጠጥም ማቆም አለብህ
እሱ: እሺ
እሷ: ኧ!!! …ሌላ ደሞ ምን ነበር?? አዎ! እያመሸህ መግባት
አትችልም
እሱ: እሺ
እሷ: እም…ሌላ? ሌላ? ምንድነው የረሳሁት??? ሌላ
የምትተወው ነገር ምን ነበር???
እሱ: አንቺን ማግባት

ሚስት አምሽታ ወደቤት እየገባች ነው …
ወድያው የመኝታ ቤቷን ከፍታ ስትገባ
አልጋዋ ላይ ሁለት የተኙ ሰዎችን
ትመለከታለች፤ አራት እግሮች ከብርድ ልብሱ
ስር ወተው ይታያሉ
ከዝያም ወድያውኑ አጠገቧ ያለውን ዱላ አንስታ
ከብርድ ልብሱ ውስጥ ያሉትን ሁለቱን ሰዎች
ባላት ኃይል መደብደብ ትጀምራለች ..ወድያው
መደብደቡን ታቆምና ወደ ሳሎን ቤት ስትሄድ
ባሏ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ጋዜጣ ያነብ ነበር
ከዝያም ባልየው ” hi darling…ቤተሰቦችሽ
መተዋሉ
የኛ መኝታ ቤት ተኝተዋል ሰላም አልሻቸው ..?
ሲላት ሚስት በድንጋጤ እራሷን ስታ ወደቀች ::
“የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አሉ”

Love In A Digital Age
ጎግዬ አስጎግዬ ያን ሰሞን ያጣኋት
አወይ አጋጣሚ CHAT ላይ አገኘኋት
ADD ያረኳትን ልጅ አምናና ካቻምና
አየኋት FACEBOOK ላይ ያቻትና ያቻትና
ONLINE አየናት ሲሉኝ ትላንትና
FACEBOOK LOGIN ብዬ አጣኋት ሄድኩና
አገኛት እንደሆን TWITTER ላይ ሄድኩኝ
አይኔ እንደናፈቃት ሳላያት አደርኩኝ
YOUTUBE ገብቼ SEARCH አድርጌ አጣኋት
TODAY እንደ ድንገት FACEBOOK ላይ አየኋት
ጎግዬ አስጎግዬ ዛሬ አጊንቻታለሁ
CHAT አድርጊው በሏት እኔ እሻላታለሁ

አለቃ ገብረ ሃና ከዕለታት አንድ ቀን መንገድ እሄዳለሁ ብለ ይነሣሉ፡፡ “ማዘንጊያ” ይላሉ ሚስታቸውን “አቤት” ይላሉ ሚስት “መንገድ ልሄድ አስቤያለሁ” “ወዴት?” “ወደ ቆላ ወርጄ የታመመ ጠይቄ፣ የተጣላ አስታርቄ እመለሳለሁ!” “እንግዲያው ባዶ ሆድዎን አይሄዱም ቆይ ቁርስ ደርሷል፡፡” “ባዶ ሆዳችንን አደል የተፈጠርን? “ቢሆንም ወንድ ልጅ የሚገጥመው ስለማይታወቅ ባዶ ሆዱን አይወጣም” “ሴትስ የሚገጥማት ታጣለች ብለሽ ነው? ካልሽ እንግዲህ ቶሎ አቅርቢልኝና ፀሃዩ ሳይገርር ልነሳ” ወ/ሮ ማዘንጊያ ጉድ ጉድ ብለው ቁርስ አቀረቡና አብረ በልተው ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡ አለቃ ቆላ ወርደው የታመመ ጠይቀው የተጣሉትን ሁለት ሰዎች ሊያስ…ታርቁ ግቢያቸው ሲደርሱ ጭራሽ ተጋግለው ቡጢ ሊቀማመሱ ግራ ቀኝ ሲሉ ያያሉ፡፡ ሰዎቹ አንደኛው የተማረና አዋቂ የሚባል ሰው ነው፡፡ ሌላኛው ምንም ያልተማረ መሀይም ነው፡፡ መሀይሙ የተማረውን፡ “አንተ ደንቆሮ! ዶሮ ራስ!” ይለዋል፡፡ “አፍህን ዝጋ ነግሬሃለሁ!” ይላል የተማረው “ደንቆሮ! ደደብ! ቆርቆሮ!” ይላል መሀይሙ፡ “ምንም ልሁን አፍህን ካልዘጋህ ዋጋህን ታገኛለህ!” አለቃ፤ “ተው እንጂ ተው አይሆንም!” ይላሉ ሊገላግ መካከል ገብተው፡፡ መሀይሙ አሁንም “ደንቆሮ! አለቃ፤ ይሄኮ ደደብ ነው! ይላል፡፡ አለቃ፤ ሁለቱንም በተለያየ አቅጣጫ ገፍተይለያዩዋቸዋል፡፡ ይሄኔ አንድ መንገደኛ ድንገት ይደርሳል፡፡ አለቃ ያውቃቸዋል፡፡ ወደሳቸው ቀረብ ብሎ፤ አለቃ ምን እያደረጉ ነው?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ አለቃም፤ “ስድብ ቦታውን ስቶብኝ፤ ቦታ ቦታው እየመለስኩ ነው!” አሉ፡፡

የ80 ዓመት አዛውንት ለጠቅላላ የጤና ምርመራ (Checkup) ሆስፒታል ይሄዱና ሃኪማቸው “እንዴት ነው ጤንነትዎ?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡
ሽማግሌውም “በጣም ጤና ነኝ —እንደውም የ18 ዓመት ኮረዳ አግብቼልህ አርግዛልኛለች—-ልጅ ላገኝ ነው — መታደል ነው አይደል?” ይሉታል – ለሃኪሙ፡፡ ሀኪሙ ነገሩ አልተዋጠለትምና ትንሽ ሲያስብ ከቆየ በኋላ “አንድ ታሪክ አስታወሱኝ” በማለት ይነግራቸዋል፡፡
“አንድ እኔ የማውቀው አደን የሚወድ ሰውዬ ነበር፡፡ በቃ የአደን ነገር ጨርሶ አይሆንለትም፡፡

አንድ ቀን ለአደን ሲወጣ ታዲያ ጠብመንጃውን አነሳሁ ብሎ ዣንጥላውን ይዞ ይወጣል፡፡ ገና ጫካ ውስጥ እንደገባም ከየት መጣ ሳይባል አንድ የተበሳጨ ድብ ፊትለፊቱ ገጭ ይልበታል፡፡ ከመቀፅበት ዣንጥላውን እንደጠመንጃ አስተካክሎ ድቡ ላይ ያነጣጥርበትና እጀታውን ይጫነዋል—-ድቡ ወዲያው መሬት ላይ ጠብ ይላል” አላቸው ሃኪሙ፡፡
ሽማግሌውም “ይሄማ ሊሆን አይችልም! ድቡ ላይ የተኮሰው ሌላ ሰው መሆን አለበት!” አሉ – ጮክ ብለው፡፡
ሀኪሙም “የእርስዎም ነገር እኮ እንደዚያ መስሎኝ ነው” አላቸው፡፡

“የባል ኑዛዜ”

ባል ጣዕረ-ሞት ይዞት እያጣጣረ ሳለ ሚስቱን ያስጠራና “እንግዲህ እኔ መሞቴ ነው፤ አንቺ ግን ያለ ባል መቅረት የለብሽም፤ እንዲያውም ያንን ኩራባቸውን አግቢ” ይላታል። በዚህ አባባል የተናደደችው ሚስት “አንተን ይማርልኝ እንጂ እኔ አሁን ስለ ባል አላስብም! ደግሞ ባገባስ እንዴት ያንተን ዋነኛ ጠላት ኩራባቸውን አግቢ ትለኛለህ?” ስትል ትጠይቀዋለች። በዚህ ጊዜ ጣር የያዘው ባል እያቃሰተ መለስ ብሎ “አንቺ ደሞ አይገባሽም እንዴ? ጠላቴ መሆኑንማ መች አጣሁት? ልክ እንደ እኔ አንገብግበሽ እንድትገድይልኝ ነው እንጂ! አላት ይባላል። ኑዛዜ ይልሃል ይህ ነው! ከእንዲህ አይነቱ ኑዛዜ ይሰውራችሁ ይሰውረን አሜን አሜን በሉ።

አንድ ሰካራም ለሚስቱ ይደውልና “መኪናዬን
መርካቶ አቁሜ ፣ ሌቦቹ አወላልቀው
ወሰዱት” አላት… “ምን ማለትህ ነው?”..
“በቃ ምንም አልተረፋቸውም! መሪው ፣
ሬዲዮኑ ፣ ምን አለፋሽ? ፊት ለፊት ያለው
ቦርዱን ጭምር ነው የዘረፉኝ።
እነዚህ ቅማላሞች! ፍሬኑና የቤንዚን
መስጫው እንኳን አልቀራቸውም”…
“እሰሰሰሰይ! ደግ አደረጉ! እየሰከሩ ማምሸት
ይቅርብህ ብዬህ አልነበረም!” ስትል ፤ ከት
ብሎ መሳቅ ጀመረ። “ምን ያስቅሃል?”…
“ይቅርታ! ለካ በኋላ በር ገብቼ ነው”

ልጅቷ በማታ ወደ ልጁጋ ትደውላለች

”እባክህ ሰሞኑን አንድ እረፍትና እንቅልፍ የነሳኝን ነገር ልጠይቅህ
ምናልባት ጥያቄው ሊከብድህ ይችላል(ልጁ ደንግጧል!!!) ምናልባት ደግሞ ከዚህ በኃላ ስለኔ የተለየ አመለካከት ሊኖርህ ይችላል::ነገር ግን
በቃ ምንም ማድረግ አልችልም አንተ ምን እንደሚሰማህ ማወቅ ስለምፈልግ ነው..(……..ፊቱ ላብ በላብ)በጣም ለረጅም ጊዜ ለመጠየቅ ፈርቼ በውስጤ አምቄው ኖሪያለው አሁን ግን ይበቃኛል..በቃ ከራስህ አንደበት ማወቅ አለብኝ እኔ ከዚ በላይ መጎዳት የለብኝም..(ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ነው) ብቻ አንተ ምንም ይህል ከባድ ቢሆን እውነቱን
ንገረኝ እኔ ምፈልገው ግልፅ እንድትሆንልኝ ብቻ ነው..

Read More

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here