SHARE

ቲለርሰን ከፕሬዝደንት ትራምፕ ጋር እጅግም እንደማይጣጣሙ በይፋ ሲነገር ቆይቷል። ይህ አለመግባባታቸዉም ወደ ግላዊ ጉዳይ ሳይቀር መዉረዱን ትራምፕ የጠቆሙበት ጊዜም አለ። ከማያግባቧቸዉ ነጥቦች መካከል ከኢራን ጋር የተደረሰዉ ስምምነት አንዱ ነዉ። ቲለርሰንም አልፈዉ ተርፈዉ ጅላጅል ሲሉ በሌሎች ባለስልጣናቶች ፊት ፕሬዝደንቱን ዘልፈዉ ያዉቃሉ።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸዉ የነበሩትን ሬክስ ቲለርሰንን አባረሩ።

ትራምፕ የቲለርሰንን ከኃላፊነታቸዉ መሰናበት በትዊተር መልዕክት ነዉ ይፋ ያደረጉት። ሕመም እንደተሰማቸዉ ገልጸዉ የአፍሪቃ ሃገራት ጉብኝታቸዉን አቋርጠዉ ወደሀገራቸዉ የተመለሱት ቲለርሰን ከፕሬዝደንት ትራምፕ ጋር እጅግም እንደማይጣጣሙ በይፋ ሲነገር ቆይቷል።

ይህ አለመግባባታቸዉም ወደ ግላዊ ጉዳይ ሳይቀር መዉረዱን ትራምፕ የጠቆሙበት ጊዜም አለ። ከማያግባቧቸዉ ነጥቦች መካከል ከኢራን ጋር የተደረሰዉ ስምምነት አንዱ ነዉ። ቲለርሰንም አልፈዉ ተርፈዉ ጅላጅል ሲሉ በሌሎች ባለስልጣናቶች ፊት ፕሬዝደንቱን ዘልፈዉ ያዉቃሉ። እንዲያም ሆኖ ግን ጉዳዩን አለባብሰዉ ለማለፍ ሲሞክሩ ታይተዋል። የዛሬዉ በድንገት ከኃላፊነታቸዉ የመባረራቸዉ ርምጃ ግን በሁለቱ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል ያለዉ ችግር ሥር የሰደደ መሆኑን አመላክቷል። ትራምፕ ቲለርሰንን አባርሬያለሁ ባሉበት የትዊተር መልዕክት ተተኪያቸዉ የሚሆኑት የሀገሪቱ የስለላ ተቋም ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ እንደሚሆኑም ገልጸዋል። የቲለርሰንን ድንገት መባረር አስመልክቶ ከዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን ናይታኤል ወልዴን በስልክ አነጋግረነዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here